2022-07-21 00:03:07
ሀሳብህን፣ ምኞትህን፣ ፍላጎትህን፣ ዕቅድህን እና አላማህን ወደ ተግባር የምትለውጥበት ወይም በአካል እና በገንዘብ የምትገልጥበት የአእምሮ ኃይል እምነት ነው፡፡
እምነት በሳይንስ ህጎች ሊገለፁ የማይችሉ የሁሉም “ተአምራቶች” እና የሁሉም ምሥጢራት መሰረት ነው!
እምነት ብቸኛው የውድቀት ማርከሻ ነው!
እምነት ከጸሎት ጋር ሲቀላቀል፣ ከሁለንተና ጥበብ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት የሚፈጥር ንጥረ ነገር “ኬሚካል” ነው፡፡
እምነት በውስኑ የሰው አእምሮ የተፈጠረን ተራ የሃሳብ ሞገድ ወደ መንፈሳዊ ተመጣጣኙ የሚቀይር ንጥረ ነገር ነው፡፡
እምነት የሁለንተና ጥበብ ሰማያዊ ኃይል በሰው የሚገለፅበት እና ጥቅም ላይ የሚውልበት ብቸኛው ወኪል ነው፡፡
እምነት ሁለንተና ጥበብን እንዲቀበል አእምሮህን በማስተማር የምታሳድገው የአእምሮ ገፅታ ወይም የአስተሳሰብ እና የአመለካከት ሁኔታ ነው፡፡
እምነት ከሀሳብ ጋር ሲቀላቀል፣ ድብቁ አእምሮ ንዝረቱን ያገኛል፤ ወደ መንፈሳዊ ተመጣጣኙም ይቀይረዋል፤ ከዚያም ወደ ሁለንተና ጥበብ ያስተላልፈዋል፡፡
ማድረግ እንደምትችል ካመንክ ታደርገዋለህ፡፡
ምንጭ:- Think and Grow Rich by Napoleon Hill
"እምነት አላማችን የሚገነባበት መሰረት ነው። የምንፈልገው ነገር ምንም ይሁን ምን እምነት ከሌለን ነዳጅ የሌለው መኪናን ለመንዳት እንደመሞከር ይሆንብናል።"
--- ናፖሊዮን ሂል
"አንድ እምነት ያለው ሰው ፍላጎት ብቻ ካላቸው 99 ሰዎች እኩል አቅም አለው"
---ጆን ስቱአርት ሚል
‹‹ እምነት ማለት ምንም እንኳን ሙሉው የሕይወት መሰላል ባይታይህም የመሠላሉን የመጀመሪያውን እርካብ መርገጥ ነው፡፡ ››
ማርቲን ሉተር
2.0K viewsyohannes Mezgebu, 21:03