Get Mystery Box with random crypto!

የእውቀት-አቡጊዳ ✏️💧💦❀✿

የቴሌግራም ቻናል አርማ yewqetabugida67 — የእውቀት-አቡጊዳ ✏️💧💦❀✿
የቴሌግራም ቻናል አርማ yewqetabugida67 — የእውቀት-አቡጊዳ ✏️💧💦❀✿
የሰርጥ አድራሻ: @yewqetabugida67
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.86K
የሰርጥ መግለጫ

_____________✔✿❀✔__________

✍... እንኳን ደህና መጣችሁ
"ኑ እናንብብ አብረን በእውቀት ከፍታ እናብብ!"
_____________✔❀✿✔___________
መልካም መስራት ክፉ ከማሰብ ይልቅ የበለጠ ደስ ይላል፡፡
✍ ለማንኛውም፦
✔ መልዕክት
✔ጥቆማና ቅሬታ @Ayuma

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-01 20:35:27 ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ትላንትና የድርጅቱ ሰራተኞቹን ሰብስቦ የማነቃቂያ ንግግር አደረገ በንግግሩም ደጋግሞ የተጠቀመው ቃል የማይቻል ነገር የለም #ይቻላል ብሎ ንግግሩ ቋጨ፡፡ በመጨረሻም ጥያቄ ያለው ሲል በመስሪያ ቤቱ አዝግ በሚል ቅጽል ስም የሚጠራ ሰራተኛ እጁን አወጣ ኃይሌም እድሉን ሰጠው፦ "አመሰግናለሁ ሻለቃ እንደው ደፈርከኝ አትበለኝና ብሎ በንግግርህ ደጋግመህ ይቻላል ይቻላል ስትለን ነበር ግን ከምር ሁሉ ነገር ይቻላል???? " ሲል ኃይሌም ቀበል አርጎ "ከሞከርክ ሁሉም ይቻላል" አለው፡፡ ሰራተኛው ግን አልተዋጠለትም እንግዳው ሁሉም የሚቻል ከሆነ አንድ ነገር አድርግልኝ እኔ አልቻል ስላለኝ ነው ሲል ፣
ሻለቃ ኃይሌም፦ ኮስተር ብሎ ምንድነው እሱ አለው??
ሠራተኛው ፦ "ይቻላል የሚለው ቃል ይበልጥ እንዲገባን እዚህ ግድግዳ ላይ ውኃን በፕላስተር አጣብቀህ/አንጠልጥለህ ይዘህ አሳየን"ሲል
ሻለቃ ኃይሌ፦ ከመልሱ በፊት "እኔ ምለው አንተ የእኔ ሠራተኛ ነህን ??? አላለም ፡፡
መልካም የእሁድ ቀትር
Join & shsre @yewqetabugida67
651 viewsAyum@, 17:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 10:06:41
884 viewsAyum@, 07:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-31 18:08:44 አበቦች ሲፈኩ እንደሚደርቁ ያውቃሉ፣ ግን እደርቃለሁ ብለው ሳይፈኩ አይቀሩም፡፡

ሰውም ሟች ነው ግን ሟች ነኝ ብሎ መተው የለበትም፡፡ ሁሉም ሰው በየመስኩ ያብብ፡፡
ወዳጄ ይህቺ አለም ትልቅ ዳመራ ናት አንተ በዳመራው ስር ያለህ አንድ ችቦ ነህ አንተ ስትጠፋ የዳመራው ብርሀን ይቀንሳል፡፡ የቻልከውን ያህል ብራ አንተ ከነገሮች በላይ ነህ፡፡ በነገሮች አትረበሽ፡፡

አየህ አንፖል ተቃጠለ ተብሎ ቤት አይቀየርም፡፡ አንፖል ተቃጥሏል ብሎ
ቤት የሚቀይር ሞኝ ነው፡፡ አንተም አንዱ የህይወቴ ጉዳይ አልተሳካም ብለህ ራስህን ለማጥፋት አትሞክር፡፡ ይልቅስ አምፖልህን ቀይር ችግርህን ተጋፈጠው፡፡

ጭንቀትህን አስጨንቀው፡፡ "ካህሊል ጅብራል እንዲህ ይላል ህይወት ልክ እንደ ክራር ጨዋታ ነው፡፡ አጨዋወቱን ያወቀ ጥሩ ሙዚቃ ይሰማል
ያላወቀ ደግሞ ዝብርቅርቅ ጩኸቷን ለመስማት ይገደዳል፡፡ "

አሁንም እልሀለው ህይወት በደመነፍስ አትሄድም ስልቷን እወቀው፡፡ በህይወትህ ትላንት ያለፈውን መጥፎ ታሪክህን መቀየር ማስተካከል መሰረዝ አትችልም፡፡ የምትችለው አምኖ መቀበልና ለተሻለ ነገ መስራት ብቻ ነው፡፡

"መቀየር የማንችለውን ነገር መቀበል ማለት ተስፋ መቁረጥ ማለት ሳይሆን አቅማችንን የምንችለው ነገር ላይ ማዋል ማለት ነው::" በፍፁም ተስፋ አትቁረጥ ግን አቅምህን የምትችለው ነገር ላይ አውለው

ጋሽ ስብሀት ገ/እግዝያብሄር"
1.5K viewsAyum@, edited  15:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-31 18:08:14
ውብ ቀን!


"የሚያስፈራኝ ደሃነትና የመንገድ መፍረስ አይደለም፡፡ የሥጋና የአጥንቴ መድከም አይደለም፡፡
(ማናችንም ላናመልጥ)

የዕቃ መወደድ አይደለም፡፡
(እግዜር የከፈተውን አፍ ሳይዘጋው ካደረማ፤ እግዜሩም እግዜር እኔም ሰው አይደለሁም)

ሰው ይቀየመኛል አይቀየመኝም አይደለም፡፡
(ብለፋም አልችልበትም)

ፀጉሬ አማረ አላማረ አይደለም፡፡
(ካልሆነ መላጨት አለ እኮ)

ነፍሴ ሲዖል ገባች አልገባች አይደለም፡፡
(የእግዜር ፍርድ ነው ይሄ)

የልቤ ነገር ነው!
በሕይወት ቆሜ የምወዳቸው እየከሰሙብኝ ቂም አማሮኝ፣ ልቤ በተስፋ መቁረጥ እንዳይቆስል ነው፡፡"

፠፠፠
አዳም
1.0K viewsAyum@, edited  15:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-31 18:07:40
ለቅዳሚታችን!



"በዓለም ላይ ያለኝ አንድ ወዳጅ ልብስ ሰፊ ነው! " አለ ሰውዬው።

ምነው ሲባል፣ "በትላንቱ አይለካኝም"

@Yewqetabugida67
834 viewsAyum@, edited  15:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-26 09:45:11 #በዓለም_ላይ_3_ዐይነት_ሰዎች_አሉ!

1, የተቀመጡ ሰዎች
2, የተሰረቁ ሰዎች
3, ባለ ራዕይ ሰዎች

#የተቀመጡ_ሰዎች

የሚባሉት ህይወትን በ TV ነው የሚያዩት፣ ትችትን ፣ ነቀፌታን ፣ተግዳሮት የማይፈልጉ ፣ አሸናፊነትንም ሆነ ሀላፊነትን አይወዱም ባአጠቃላይ [Challenge Life] አይፈልጉም።

#የተሰረቁ_ሰዎች

ሌላዉን መስሎ መኖር ምኞታቸው ነው። የራሳቸው የሆነ አቋምም ሆነ ማንነት የላቸውም። የተሰረቀ ሰው ራሱን ከሌላ ጋር እያወዳደረ ነው የሚኖረው።

#ባለራዕይ_ሰዎች

ነፃ እና ተፈጥሯዊ ሰዎች ናቸው። የበታችነት ስሜት አይሰማቸውም!! መተባበር፣ ፍቅር እና ማህበራዊ ተቆርቋሪነት መገለጫቸው ነው።እነዚህ ሰዎች በቅድሚያ፦
ማህበረሰቡን
ሲቀጥል ቤተሰባቸው
በመጨረሻ ራሳቸዉን የሚያስከትሉ ናቸው።

እንዲህ አይነት ሰው ካርታውን ያለማጭበርበር የሚጫወት እንጂ የሚያሸንፍ አይደለም።

ሁሉም ጥሩ ይሆናል ዋናው ነገር ሰላምና ጤና

@Yewqetabugida67
907 viewsAyum@, 06:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-12 22:58:16
ባለ ጊዜ ጉልበተኛ አልጠግብ ባይ ስትሆንና ቀን ሲጥልህ መራመድ ሲያቅትህ

@Yewqetabugida67
1.7K viewsAyum@, 19:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-09 11:00:30
1.1K viewsAyum@, 08:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-07 16:55:54 ✤ሰው እንጂ እግዚአብሔር አልረሳኝም✤ መርሣት የባህሪውም አይደለምና፦
በጸሎት ኃይል የሚያምን አምኖም የሚተጋ አንድ ፅኑዕ ክርስቲያን ነበር፡፡ ይህም ክርስቲያን ጥሪት የሌለው ደኃ ፣የሚበላውን የሚቸገር ረሃብተኛ ፣ልብሱ በላዩ ላይ አልቆ የታረዘ ምስኪን ነው፡፡ ከእለታት አንድ ቀን በጸሎት ሕይወቱ የነበረውን ትጋት በቅርብ ሆኖ ይታዘብ የነበረው ወዳጁ እንዲህ አለው ‹ቢያንስ ለረሃብህ ማስታገሻ ቁራሽ ዳቦ እንኳን ማስገኘት ካልቻለ የመጸለይህ ትርጉም ምንድር ነው? በቃ ፈጣሪህ አልሰማህም ማለት ነው!› ሲል ተስፋ በሚያስቆርጥ ቃል ተናገረው፡፡ ያ ምስኪን ክርስቲያን ግን እንዲህ ሲል መለሰለት ተሣስተሃል ‹እግዚአብሔርማ አልረሳኝም! ለአንዱ ሰው ከዕለት እንጀራው የበለጠ አትርፎ በመስጠት ለእኔ እንዲያካፍለኝ ነግሮት ነበር፡፡ ነገር ግን ይህን አደራ የተቀበለው ሰው ዘነጋኝ፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ሳይሆን ይህ ሰው ረስቶኛል!!!›
ክርስቲያኖች ለምን አንዳንዶች ከዕለት የሚተርፍ ብዙ እንጀራ ሲያገኙ፤ አንዳንዶች ደግሞ ለዕለት እንኳን የሚሆን ቁራሽ እንጀራ ያጣሉ? መቼም ‹ለሰው ፊት የማያዳላ› እግዚአብሔር አድልዎ ኖሮበት ነው አትሉም?! (ሐዋ. 10፥34) ይህስ የሆነው እንደ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርት አትርፈው ያገኙት ምንም የሌላቸውን በመርዳት እና በመመገብ በባሕርይው መግቦትን ገንዘብ ያደረገውን አምላክ በጸጋ እንዲመስሉትና በፈጠራቸው ሰዎች መካከል ያለውን ትስስር የበለጠ ለማጠናከር ነው፡፡
ስለዚህ ‹የዕለት እንጀራችንን ስጠን ለዛሬ› ብለን የለመንነው አምላክ ከዕለት እንጀራችን አትርፎ የሚሰጠን ይህን አምላካዊ አደራ እንድንወጣም ስለሚፈልግ እንደሆነ ብንረዳው እንዴት መታደል ነበር!!!
★በዚህ ዓለም በዚህ ዘመን ሰው ዝም ብሎ ራሱ ተስፋ ቆርጦ ሰውን ተስፋ ቢስ የሚያደርግ ሙሉ ነው፡፡ ነገር ግን ወዳጄ ምንም ጊዜ ምንም ይሁን ምን ሰውን ያለቦታው የሚያውሉ ያላዩትን የሚናገሩ ዝም ብለው ስም የሚያወጡ በመሰለኝ የሚናገሩ አሉና እንዳትሰማ ፦
" #ሰው ሲጨርስ እግዚአብሔር እንደገና ይጀምራል፤ #ፈጣሪ ሰው አይደለማ " ፡፡ ተስፋ ሕይወት ነው ተስፋ ጠል ነው ተስፋ አያልቅም ጅረት ነው ....
ደስ የሚል የተስፋ ቀን ይሁንልን ፡፡
#የእውቀት አቡጊዳ

@Yewqetabugida67
1.6K viewsAyum@, edited  13:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ