Get Mystery Box with random crypto!

ውብ ቀን! 'የሚያስፈራኝ ደሃነትና የመንገድ መፍረስ አይደለም፡፡ የሥጋና የአጥንቴ | የእውቀት-አቡጊዳ ✏️💧💦❀✿

ውብ ቀን!


"የሚያስፈራኝ ደሃነትና የመንገድ መፍረስ አይደለም፡፡ የሥጋና የአጥንቴ መድከም አይደለም፡፡
(ማናችንም ላናመልጥ)

የዕቃ መወደድ አይደለም፡፡
(እግዜር የከፈተውን አፍ ሳይዘጋው ካደረማ፤ እግዜሩም እግዜር እኔም ሰው አይደለሁም)

ሰው ይቀየመኛል አይቀየመኝም አይደለም፡፡
(ብለፋም አልችልበትም)

ፀጉሬ አማረ አላማረ አይደለም፡፡
(ካልሆነ መላጨት አለ እኮ)

ነፍሴ ሲዖል ገባች አልገባች አይደለም፡፡
(የእግዜር ፍርድ ነው ይሄ)

የልቤ ነገር ነው!
በሕይወት ቆሜ የምወዳቸው እየከሰሙብኝ ቂም አማሮኝ፣ ልቤ በተስፋ መቁረጥ እንዳይቆስል ነው፡፡"

፠፠፠
አዳም