Get Mystery Box with random crypto!

አበቦች ሲፈኩ እንደሚደርቁ ያውቃሉ፣ ግን እደርቃለሁ ብለው ሳይፈኩ አይቀሩም፡፡ ሰውም ሟች ነው | የእውቀት-አቡጊዳ ✏️💧💦❀✿

አበቦች ሲፈኩ እንደሚደርቁ ያውቃሉ፣ ግን እደርቃለሁ ብለው ሳይፈኩ አይቀሩም፡፡

ሰውም ሟች ነው ግን ሟች ነኝ ብሎ መተው የለበትም፡፡ ሁሉም ሰው በየመስኩ ያብብ፡፡
ወዳጄ ይህቺ አለም ትልቅ ዳመራ ናት አንተ በዳመራው ስር ያለህ አንድ ችቦ ነህ አንተ ስትጠፋ የዳመራው ብርሀን ይቀንሳል፡፡ የቻልከውን ያህል ብራ አንተ ከነገሮች በላይ ነህ፡፡ በነገሮች አትረበሽ፡፡

አየህ አንፖል ተቃጠለ ተብሎ ቤት አይቀየርም፡፡ አንፖል ተቃጥሏል ብሎ
ቤት የሚቀይር ሞኝ ነው፡፡ አንተም አንዱ የህይወቴ ጉዳይ አልተሳካም ብለህ ራስህን ለማጥፋት አትሞክር፡፡ ይልቅስ አምፖልህን ቀይር ችግርህን ተጋፈጠው፡፡

ጭንቀትህን አስጨንቀው፡፡ "ካህሊል ጅብራል እንዲህ ይላል ህይወት ልክ እንደ ክራር ጨዋታ ነው፡፡ አጨዋወቱን ያወቀ ጥሩ ሙዚቃ ይሰማል
ያላወቀ ደግሞ ዝብርቅርቅ ጩኸቷን ለመስማት ይገደዳል፡፡ "

አሁንም እልሀለው ህይወት በደመነፍስ አትሄድም ስልቷን እወቀው፡፡ በህይወትህ ትላንት ያለፈውን መጥፎ ታሪክህን መቀየር ማስተካከል መሰረዝ አትችልም፡፡ የምትችለው አምኖ መቀበልና ለተሻለ ነገ መስራት ብቻ ነው፡፡

"መቀየር የማንችለውን ነገር መቀበል ማለት ተስፋ መቁረጥ ማለት ሳይሆን አቅማችንን የምንችለው ነገር ላይ ማዋል ማለት ነው::" በፍፁም ተስፋ አትቁረጥ ግን አቅምህን የምትችለው ነገር ላይ አውለው

ጋሽ ስብሀት ገ/እግዝያብሄር"