Get Mystery Box with random crypto!

የእውቀት-አቡጊዳ ✏️💧💦❀✿

የቴሌግራም ቻናል አርማ yewqetabugida67 — የእውቀት-አቡጊዳ ✏️💧💦❀✿
የቴሌግራም ቻናል አርማ yewqetabugida67 — የእውቀት-አቡጊዳ ✏️💧💦❀✿
የሰርጥ አድራሻ: @yewqetabugida67
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.86K
የሰርጥ መግለጫ

_____________✔✿❀✔__________

✍... እንኳን ደህና መጣችሁ
"ኑ እናንብብ አብረን በእውቀት ከፍታ እናብብ!"
_____________✔❀✿✔___________
መልካም መስራት ክፉ ከማሰብ ይልቅ የበለጠ ደስ ይላል፡፡
✍ ለማንኛውም፦
✔ መልዕክት
✔ጥቆማና ቅሬታ @Ayuma

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-03-07 08:51:05
887 viewsAyum@, 05:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-07 08:24:27 . #ድንቅ_እናት

ባለቤቷ ከሞተ በኋላ ልብሱን ቁም ሳጥን ውስጥ አንጠልጥላው በየጊዜው ገንዘብ ታስቀምጥበታለች ። ልጆቿ ለተለያየ ጉዳይ ወጪ ሲጠይቋት ሂዱ ቁም ሳጥን ውስጥ
ከአባታችሁ ደረት ኪስ ውሰዱ ትላቸዋለች "
እነሱም የሚያስፈልጋቸውን ብቻ ቆጥረው ከአባታቸው ኪስ ይወስዳሉ ከዕለታት አንድ ቀን ልጆቹ እናታቸውን ለምን እንደዚህ እንደምታረግ ሲጠይቋት የአባታችሁ ሩህሩህነትና ለጋስነት እንድታውቁትና አባታችሁ እዛም ሆኖ ለእናንተ እንደሚጨነቅ እንድታውቁ (አባት የሞተበት ) ነን ብላችሁም እንዳታስቡ ለማስታወስ ነው!::

#አስተዋይ_እናት_ትምህርት_ቤት_ናት_የምንለው_ለዚህ_ነው!::


@Yewqetabugida67
829 viewsAyum@, 05:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-06 12:32:04
#እኛ_አበሾች_ስንተባበር

@Yewqetabugida67
2.0K viewsAyum@, edited  09:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-31 16:12:12
#ሁሉም_የሞላለት_ስለሌለ_ሁሉም_የጎደለበትም_የለም

በአንድ የቻይና የገጠር መንደር የሚኖሩ አንድ ጎልማሳ ሰው ነበሩ
ሁሌም ታዲያ ማልደው በመነሳት ውሃ ሊቀዱ ወንዝ ይወርዳሉ፣ሆኖም ያሉዋቸው ሁለት ከሸክላ የተሰሩ የውሀ ማሰሮዋች ሲሆኑ
አንደኛው አዲስ ሲሆን ሌላኛው ግን ሰባራ ነው በዚህ ምክንያት
ውሃ ቀድተው ቤት ሲደርሱ አዲሱ ሙሉ ውሃውን እነደያዘ ቤት ሲደርስ ሰንጥቅ ያለበት አሮጌው ግን ግማሹን አፍሶ ግማሹን ደግሞ ይዞ ነው የሚገኝው በዚህ ምክንያት የሚያፈሰው አሮጌ
ማሰሮ ሁሌም እኚህ ሰውዬ ለምን እንደማያድሱት እያጉተመተመ
ከጓደኛው በማነሱ እየተሸማቀ ይኖር ነበር ::

አንድ ቀን የራሱ ተፈጥሮው በጣም ስላስጠላው ይህ እንዲሆን ለምን እንደፈቀዱ አፍ አውጥቶ ጌታውን በምሬት ጠየቀ :: አዛውንቱ ሰውዬም ሲመልሱለት ” ተፈጥሮህን ለምን ታማራለህ የምንሄድበትን መንገድ ተመልክተኸው ታውቃለህ በአንተ አቅጣጫ ያለው መሬት ሁሌም ለምለም ነው በሚያምሩ አበቦች የተሸፈነ ነው በጓደኛህ በኩል ያለው ግን ደረቅና አቧራማ ነው ይሄ አንተ በማፍሰስህ ምክንያት የመጣ ነው እነዚህ አበቦች ለአካባቢው ጌጦች የሳሎን ማድመቂያ ናቸው ህይወትን ያድሳሉ ::
በዚህ አለም ሁላችንም ብንሆን ከጉደለት ጋር ነው የተፈጠረነው አንዳችን ለአንዳችን እናስፈልጋለን ዋናው ነገር ከሌላው በማነፃፀር የራስን ተፈጥሮ በመጥፎ መሳልና ማማረር ተገቢ አይደለም ከዛ ተፈጥሮ የሚገኝን በጎ ነገር ማየትና ያንን ማድነቅ ያስፈልጋል “ ብለው መለሱለት ።

ሞራል : — ሁሌም ቢሆን አንዳችን ለአንዳችን እናስፈልጋለን ራስን ዝቅ አድርጎ ተፈጥሮን ማማረር ተገቢ አይደለም ።
#ሁሉም_ሙሉ_የሆነለት_የለም_ሁሉም_ደግሞ_የጎደለበት_የለም_ሙሉውን_በጎዶሎ_ጎዶሎውን_እየሞሉ_መኖ

#የበለጠ_ያግኙ
@Yewqetabugida67
1.6K viewsAyum@, 13:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-19 17:38:22 #ምክር_ለወዳጅ


በወጣትነት ሁሉም ነገር ትክክል ነው ከሚል መመሪያ ውጣ፤ ሁሉንም ካላየሁ አላምንም አትበል። ሰምቶ ማመን፣ ከተጎዱት መማር አስተዋይነት መሆኑን አትርሳ። የሰማንያ ዓመት ዕውቀትን ለመገብየት ግድ ሰማንያ ዓመት መኖር የለብህም። ሰማንያ ዓመት ከኖሩት በትሕትና መጠየቅ ይገባሃል።

ምክርን ብትሰማ በነጻ ትማራለህ። ምክርን አልሰማ ብትል ግን በዋጋ እንደምትማር እወቀው! በዋጋ መማር ግን አድካሚ ደግሞም የሚያስመርር ነው። ብልህ ከሆንክ በሰው ከደረሰው ትማራለህ፤ ሞኝ ከሆንህ ግን በራስህ ሲደርስ ትማራለህ።

የታየህን አሳይ፣ ያልታየህን አጥራው። በደንብ ያልተረዳኸውን አታስተምረው። ያልቀመስከውን ለሰው አትጋብዝ። የሰማኸውን ሁሉ አትመን። ያየኸውን ሁሉ ስጡኝ፣ የተናገርከውን ሁሉ ፈፅሙ አትበል። የሰጠኽውን እርሳ እንጂ አታውራ። ፍፃሜውን ሳታይ ምስጋና አታብዛ። ቀኑ
ሳይመሽ ቀኑ ጥሩ ነው አትበል።

ዓይንህ የፊቱን ቢያይ፤ ልብህ የኋላውን ያስብ። ነገ ላይ እንድትደርስ፤ የትናንቱን አትርሳ። የምትሄድበት እናዳይጠፋህ የመጣህበትን አትዘንጋ።

የአባቶችህን መልካም ሥራ አብነት አድርግ። ካሳለፉት ሕይወት ተማር እንጂ አወዳሽና ወቃሽ አትሁን። ሌሎች መሆን ያለባቸውን ስታውቅ አንተ መሆን ያለብህ እንዳይጠፋህ ተጠንቀቅ። ደግሞም አንተም በታሪክ ፊት መሆንህን እወቀው።

ክፋት አይሙቅህ፣ መልካም ነገርም ብርድ ብርድ አይበልህ። ለክፋት አቅም ካለህ ለበጎ ነገርም አቅም አለህና ተግባርህ የምርጫ ውጤት ነውና አስብበት።

ገንዘብ የሚመልሰው የገንዘብን ጥያቄ ብቻ ነውና ሁሉንም ነገር ገንዘብ ያስገኝልኛል ብለህ አታስብ። ላለው አትሩጥ፣ ምጽዋትህና ተግባርህ በአቅምህ መጠን ይሁን እንጂ ከአቅምህ አትነስ። ድሃም ሆነህ ተበድረህ ስጦታ አትስጥ። በጣም ካልቸገረህ ለቅንጦት አትበደር። ያንተን ድርሻ ከጨረስህ ያልተጨረሰ የሌሎችን ድርሻ ፈፅምላቸው።

ለሀብታም አትሳቅ፣ የደሀ ጉልበት አይለፍብህ፣ ያለ ሰው ሰው አልሆንክምና ሰው አትጥላ፣ የወጣህበትን መሰላል አትገፍትር፣ ለመውረድም ያስፈልግሃልና፣ ያየኽውን ሴት ሁሉ የመውደድ ጠባይህ ካለቀቀህ ትዳር አትያዝ፣ ካልጋበዙህ በቀር አማካሪ አትሁን፣ ባልጠሩህ ሥፍራ አቤት አትበል፣ ካልሾሙህ መሪ አትሁን፣ ጉድለት በሌለበት ቦታ ጊዜህን አታባክን፣ የሰው ፊት ጥገኛ ሁነህ ሲስቁልህ የምትስቅ ሲቆጡህ የምታለቅስ አትሁን፣ ነገርህን በልክ፣ ቃልህን በጣዕም፣ ድምፅህን በዝግታ ፈፅመው።

እውር እንዳይሉህ ያልታየኽን አያለሁ አትበል። ጨካኝ እንዳይሉህ ያልተሰማህን ጩኸት እሰማለሁ አትበል። ንፉግ እንዳይሉህ ያለ አቅምህ እረዳለሁ አትበል። ነገር አይገባውም እንዳይሉህ ያልገባህን እንደገባህ አድርገህ አትለፍ። አንድ በጎ ዕውቀት ሳትጨብጥ የዋልክበትን ቀን እንደ ኖርክበት አትቁጠረው፣ ስለዚህ መፅሐፍትን አንብብ፣ አዋቂዎችን ጠይቅ፣ ሁሉን ሳትንቅ ስማ።

ሥልጣን ሲሰጥህ መሪ እንጂ አለቃ አትሁን፤ ከፊት እየቀደምህ አስከትል እንጂ ከኋላ ሆነህ አትቅደም።

በዓላማ ኑር፤ እንቅፋቶች የሚያጸኑህ እንጂ ተግባርህን የሚያስተውህ አይሁኑ። ሕይወት ትምህርት ቤት መሆኑና ባለማወቅ ብዙ ትህምርቶች እንዳያመልጡህ ተጠንቀቅ።

የመከራ ቀን ወዳጆችህን አትርሳ፤ የዛሬ ሰው ብቻ አትሁን ነገ ከመምጣቱ በፊት ቀድመህ አስብ ።

@Yewqetabugida67
4.7K viewsAyum@, 14:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-18 09:19:54
You will always have more of what you complain about, and more of what you appreciate. The principle behind this is, whatever you focus on increases.

I know you want more, but be grateful for the ones you have. Learn to appreciate the things you have before it becomes what you had.

Don't wait to have everything you desire before you become grateful for what you have, rather be grateful for what you have so you can have everything you desire.

ከሌለን ከጎደለን ነገር ይልቅ ያለን ነገር ይበልጣል። "ከምንማረርባቸው ነገሮች ይልቅ..ልናመሰግንባቸው የሚገባን ብዙ መልካም ነገሮች አሉ።

ምናልባት የምትፈልገው ስፍራ ላይ አልተቀመጥክ ወይንም የምትመኘውን ነገር አላገኘህ ይሆናል፡ ይሁን እንጂ ከብዙዎች በላይ ደስተኛ ነህ። ስለዚህም ፈጣሪህን ባለህ ነገር አመስግን። በሰላም ውሎ በሰላም ማደር እጅግ ትልቅ ነገር ነው።አዲስ ቀን አዲስ ህይወት ነው።

አንተ ለብቻህ የሆነብህ ነገር የለም። አንተ ጋር የጎደለህን ሌላው ጋር ስታይ 'ሁሉ የሞላለት' መስሎህ ነው። ባወቅኸው ልክ የሰውን ህይወት አትመዝን፣ የራስህንም አታቃል።

ስለዚህ በምንም አይነት የህይወት ትግል ውስጥ ብትሆን በመኖርህ ብቻ ደስታን ምርጫህ አድርግ። ሰላምንም ውደዳት።

ሁልጊዜም በፈጣሪህ ደስ ይበልህ!

#ወዳጄ ባለህ ደስ እንዲልህ እስኪነገርህ አትጠብቅ።

@Yewqetabugida67
4.3K viewsAyum@, edited  06:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-11 11:35:13
እነሆ አዲስ ዓመት ባተ።

እንኳን ለ2014 ዓ.ም. አዲስ ዓመት አደረሰን!

አዲሱ ዓመት በማህበረሰባችን ውስጥ እውቀት ዘልቆ ጥበብ ሰርጾ ፍቅርና ሰላም ናኝቶ፣ ኑሯችንን ክፉና ደግን በማገናዘብና መልካሙን በመምረጥ የምንመራበት ዘመን እንዲሆን እንመኛለን።

በአዲሱ ዓመት ውሸት ጠፍቶ፤ ሀቅ ጎምርቶ፣ ጥበብና ፍቅር ደርጅቶ፣ ሰላም ፍሬ አፍርቶ የምናይበት ዓመት ይሁንልን።

ፈጣሪ ከሀሜትና አሉባልታ ርቀን፣ ግራና ቀኙን እያገናዘብን በይቅርታና በትዕግስት የምንኖርበትን ጥበብ ይስጠን! ዘመኑ የሰላምና የመግባባት ዘመን እንዲሆን እንመኛለን።

ፈጣሪ ሀገራችንን ከክፉ ይጠብቃት!
መልካም አዲስ ዓመት!

@Yewqetabugida67
1.8K viewsAyum@, edited  08:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-11 07:32:47
2.2K viewsAyum@, 04:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ