Get Mystery Box with random crypto!

በ59 ሃገራት የሚገኙ ከ282 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ለከፋ ረሃብ መጋለጣቸውን የመንግስታት ድርጅት ሪ | YeneTube

በ59 ሃገራት የሚገኙ ከ282 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ለከፋ ረሃብ መጋለጣቸውን የመንግስታት ድርጅት ሪፖርት አመለከተ።

የዓለማቀፉ ድርጅት ሪፖርት እንዳለው በአስከፊ ጦርነት ውስጥ የምትገኘው የጋዛ ሰርጥ በርካታ ቁጥር ያለው ተጋላጮችን በመያዝ ትመራለች። ከጎርጎርሳውያኑ 2022 ወዲህ 24 ሚሊዮን ተጨማሪ ሰዎች ለከፋ የምግብ እጥረት እና ለረሃብ መጋለጣቸውን ያመለከተው መረጃው ከጋዛ ጦርነት በተጨማሪ የሱዳን የእርስ በእርስ ጦርነት ሚሊዮኖች እርዳታ ጠባቂ አልያም በረሃብ አፋፍ ላይ ያሉ ናቸው ብሏል። በየዓለም የምግብ እርሻ ፕሮግራም ሪፖርት እንደሚያሳየው በአምስት ሃገራት ውስጥ የሚገኙ እና ቁጥራቸው ከ705 ሺ በላይ የሆኑ ሰዎች ደረጃ አምስት ወይም ለከፋ ረሃብ የተጋለጡ ናቸው።

ከእነዚህ ውስጥ 80 በመቶውን ቁጥር የሚሸፍነው በጋዛው ጦርነት አስከፊውን ጊዜ በማሳለፍ ላይ የሚገኙት ፍልስጥኤማውያን ናቸው።ደቡብ ሱዳን ፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ሶማሊያ እና ማሊ እያንዳንዳቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ለረሃብ የተጋለጡ ዜጎች እና ስደተኞች በመያዝ ይከተላሉ።በሀገራቱ እና በአካባቢያቸው እየተደረጉ ያሉ ግጭቶች እና ጦርነቶች እስካልቆሙ ድረስ ችግሩ እየከፋ ሊሄድ እንደሚችል ዓለማቀፉ ድርጅት አሳስቧል።

ከዚህ በተጨማሪ በያዝነው የጎርጎርሳውያኑ 2024 መጀመሪያ ላይ ኤል ኒኖ ያስከተለው የአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ደረጃ የደረሰበት ወቅት እንደነበር ያስታወሰው ድርጅቱ የጎርፍ መጥለቅለቅን ጨምሮ በአንዳንድ የምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ ሀገራት የዝናብ እጥረትን በማስከተል ችግሩን ከድጡ ወደ ማጡ እንዳያደርገው ያሰጋኛል ብሏል።መንግስታት እና ለጋሾች በረሃብ ምክንያት «የጅምላ የሰውን ልጅ ውድቀት ለመታደግ» ርብርብ እንዲደረግ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬሽ ጥሪ አቅርበዋል።

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa