Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ ቴሌኮም የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባን አስጀመረ! ኢትዮ ቴሌኮም በሀገር አቀፍ ደረጃ | YeneTube

ኢትዮ ቴሌኮም የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባን አስጀመረ!

ኢትዮ ቴሌኮም በሀገር አቀፍ ደረጃ የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባን በዛሬው ዕለት አስጀመረ፡፡በማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ በወር በአማካይ 1 ሚሊየን ዜጎችን በመመዝገብ እስከ 2018 ዓ.ም ለ90 ሚሊየን ዜጎች አገልግሎቱን ለመስጠት መታቀዱ ተመላክቷል፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ፤ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ አስቻይ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ ተዓማኒነት ያለው የማንነት መለያ ዲጂታል መታወቂያ ነው ብለዋል።ዲጂታል መታወቂያ አካታች ዲጂታል ኢኮኖሚን ለመገንባትና ዜጎች በኢኮኖሚው ዕኩል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዕድል ይፈጥራል ነው ያሉት፡፡

የብሔራዊ ዲጅታል መታወቂያ ምዝገባው አዲስ አበባን ጨምሮ በ29 ከተሞች ዛሬ በይፋ የተጀመረ ሲሆን፥ ዜጎች ባሉበት ቦታ ሆነው በቴሌብር ሱፐርአፕ መመዝገብ ይችላሉ መባሉን ፋና ዘግቧል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa