Get Mystery Box with random crypto!

“በኢትዮጵያና ኤርትራ የሰብአዊ መብት አያያዙ እንደከፋ ነው” - ዩኤስ የዩናዩትድ ስቴትስ የው | YeneTube

“በኢትዮጵያና ኤርትራ የሰብአዊ መብት አያያዙ እንደከፋ ነው” - ዩኤስ

የዩናዩትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሀገራትን የሰብአዊ መብቶች አያያዝ በተመለከተ የሚያወጣውን ዓመታዊ ሪፖርት በትላንትናው ዕለት ይፋ አድርጓል።ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ትላንት ሚያዚያ 14/2016 ዓ.ም ባወጣው የሃገራትን የሰብአዊ መብቶች አያያዝ በሚተነትነው ሰፊ የአውሮፓያኑ የ2023 ዓመታዊ ሪፖርቱ፤ ፣የኢትዮጵያ መንግሥት ወይም የመንግሥት ወኪሎች፣ ከሕግ ውጪ የዘፈቀደ ግድያ መፈፀማቸውን፣ በርካታ የሃገር ውስጥና የውጪ ሃገራት የሰብአዊ መብት ቡድኖች ሪፖርት ጠቅሶ ይፋ አድርጓል።ግድያዎቹ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል እየተካሄዱ ባሉ ግጭቶች እንዲሁም ትግራይን ጨምሮ በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች የተፈጸሙ እንደሆነ አስታውቋል።

የክልል ፖሊስ አባላትም ፣ ከመጠን ያለፈ እና ሕይወት የቀጠፈ ኃይል መጠቀማቸውን የጠቀሰው ሪፖርቱ፣ ለማሳያም፣ “በየካቲት ወር በወልቂጤ ከተማ የውሃ አገልግሎት እንዲመለስ በሰልፍ ለመጠየቅ በወጡ ነዋሪዎች ላይ በተወሰደው ርምጃ ሦስት ሰዎች ሲሞቱ 30 የሚሆኑት ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል” ብሏል።

በሌሎችም አካባባዎች የተፈጸሙ ግድያዎችን ያካተተው ሪፖርት፣ የፌዴራሉ ፖሊስ ምርመራ ቢሮ በፖሊስ ኃይሎች የሚፈጸሙ ግድያዎችን በተመለከተ የሚያደርጋቸው ምርመራዎች ውስን መሆናቸውን እና የሚሰጠውን ቅጣት በተመለከተም በሚስጥር እንደሚይዝ ጠቁሟል።በግዳጅ መሰወርን አስመልክቶም፣ መንግሥትን የሚነቅፉ የፖለቲካ አስተያየት የሚሰጡ ግለሰቦች፣ የቀድሞ ጦር አባላት፣ የምርመራ ጋዜጠኞች፣ የማኅበራዊ ሚዲያ አንቂዎች መሰወራቸውን አትቷል።

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ: https://amharic.voanews.com/a/7582081.html

@YeneTube @FikerAssefa