Get Mystery Box with random crypto!

ኦሮሚያ ኢንሹራንስ ለ 122 ሺህ አርሶአደሮች 39 ሚሊዮን ብር የሰብል መድህን ካሳ ሊከፍል መሆኑ | YeneTube

ኦሮሚያ ኢንሹራንስ ለ 122 ሺህ አርሶአደሮች 39 ሚሊዮን ብር የሰብል መድህን ካሳ ሊከፍል መሆኑ ተገለፀ!

በግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ፣ በአለም ምግብ ፕሮግራም እና በፑላ አድቫይዘር ጥምረት ተጀምሯል የተባለውና በሀገሪቱ ትልቁ ነዉ የተባለው የሰብል መድህን ፕሮግራም የክፍ ስርአት መተግበር መጀመሩ ተነግሯል።

በኢትዮጵያ የሰብል መድህን ታሪክ ዉስጥ ትልቁ መሆኑ በተነገረለት ፕሮግራም የኦሮሚያ ኢንሹራንስ ኩባንያ የመድህን ሰጪ እና የካሳ ከፋይ ተቋም በመሆን ለትግበራዉ 39 ሚሊዮን ብር መመደብ ካፒታል ሰምቷል።

የመጀመሪያው ምዕራፍ እንደሆነ በተገለጸው ቢዚህ ስርዓት በአማራ ክልል የሚገኙ አነስተኛ አርሶአደሮች ተጠቃሚ መሆናቸው የተነገረ ሲሆን በቀጣይ በተለያዩ ክልሎች ለሚገኙ ለ 7.5 ሚሊዮን አርሶአደሮች ተደራሽ ይደረጋል ተብሏል።

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa