Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ ከተማ በተወሰኑ አካባቢዎች እየተከናወኑ በሚገኙ የኮሪደር ልማት ሥራዎች ምክንያት ዝግ | YeneTube

በአዲስ አበባ ከተማ በተወሰኑ አካባቢዎች እየተከናወኑ በሚገኙ የኮሪደር ልማት ሥራዎች ምክንያት ዝግ ሆነው የቆዩ መንገዶች ለተሽከርካሪ ክፍት መደረጋቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

በዚህም መሰረት፡-

•  ከደጃች ውቤ በአፍንጮ በር ወደ ራስ መኮንን ድልድይ

•  ከባሻወልዴ ችሎት በቱሪስት ሆቴል ራስ መኮንን ድልድይ አፍንጮ በር

•  ከዳኑ ሆስፒታል እስከ ቱሪስት ሆቴል በመውጣት ወደ ራስ መኮንን ድልድይ አፍንጮ በር

•  ከአራዳ መስተዳደር ወደ ዳኑ ሆስፒታል መውረጃ በአንድ አቅጣጫ ብቻ አሽከርካሪዎች መጠቀም እንደሚችሉ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ እየተከናወኑ ባሉ የልማት ሥራዎች ምክንያት ለአጭር ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ በጥብቅ መከልከሉን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa