Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ አሁን ላይ ያሏት የሚሊየነሮች ቁጥር በአጠቃላይ 2,700 መድረሱን በዘርፉ ላይ የተደረገ | YeneTube

ኢትዮጵያ አሁን ላይ ያሏት የሚሊየነሮች ቁጥር በአጠቃላይ 2,700 መድረሱን በዘርፉ ላይ የተደረገ አንድ ሪፖርት አመላከተ

ኢትዮጵያ በአሁን ጊዜ ወደ 2,700 የሚጠጉ ሚሊየነሮች እንዳሏት የገለፀዉ ይህ የአፍሪካ ሀብት ሪፖርት ሀገሪቷ በዚህ የስነ ህዝብ እድገት ዉስጥ ጠንካራ እንድገት እንደሚኖረዉ ትንበያውን አስቀምጧል።

በ 2024 የወጣዉ የአፍሪካ ሀብት ሪፖርት ዘጠኛ እትሙ ላይ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አዳዲስ ገበያዎችን የሚይዘው የአህጉሪቱ ሚሊየነር ህዝቧ በሚቀጥሉት አስርት አመታት ዉስጥ በ 65% ከፍ ሊል እንደሚችል ግምቱን አስቀምጧል ።

አሁን ላይ በአፍሪካ ያለዉ አጠቃላይ የኢንቨስትመንት ሀብት 2.5 ትሪሊዮን ዶላር መድረሱ የተነገረ ሲሆን ኢትዮጵያ በዚህ ኢኮኖሚ እድገት ዉስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጓ ነዉ ይህ ሀተታ የሚያመላክተዉ።

Via:- Capital
@Yenetube @Fikerassefa