Get Mystery Box with random crypto!

በቀጣዩ የፈረንጆቹ 2025 ዓመት፤ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ 6.5 በመቶ ያድጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ዓለም | YeneTube

በቀጣዩ የፈረንጆቹ 2025 ዓመት፤ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ 6.5 በመቶ ያድጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ይፋ አደረገ።

IMF ዛሬ ማክሰኞ ሚያዝያ 8፤ 2016 ይፋ ያደረገው ትንበያ፤ ከዘንድሮው አኳያ ሲነጻጸር የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በሚቀጥለው ዓመት አነስተኛ መነቃቃት እንደሚታይበት የሚጠቁም ነው።

በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት፤ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ6.2 በመቶ ያድጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ድርጅቱ ባለፈው ዓመት ባወጣው ተመሳሳይ ትንበያ ይፋ አድርጎ ነበር። የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ትንበያ የኢትዮጵያ መንግስት ከሚጠብቀው ዝቅ ያለ ነው። በኢትዮጵያ መንግስት ትንበያ መሰረት፤ በ2016 ዓ.ም. የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በ7.9 በመቶ ያድጋል ተብሎ ይጠበቃል። 

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
@YeneTube @FikerAssefa