Get Mystery Box with random crypto!

ኤክሳይዝ ታክስ በሚከፈልባቸዉ እንደ አልኮል መጠጦች ፣ ሲጋራ እና የታሸገ ዉሃ ላይ ላይ ቴምብር እ | YeneTube

ኤክሳይዝ ታክስ በሚከፈልባቸዉ እንደ አልኮል መጠጦች ፣ ሲጋራ እና የታሸገ ዉሃ ላይ ላይ ቴምብር እንዲለጠፍ የሚያስገድደዉ መመሪያ ወጣ!

የገንዘብ ሚኒስትር የኤክሳይዝ ቴምብር አስተዳዳር ስርዓትን ለመወሰን የሚያስችለውን መመሪያ ከሰሞኑ አዉጥቷል።በዚህ መመሪያዉ የኤክሳይዝ ታክስ በሚከፈልባቸዉ እቃዎች ማለትም የአልኮል መጠጦች፤ አልኮልና እና አልኮል አልባ ቢራ፤  ሲጋራ፤ ሲጋሪልስ፤ ትምባሆ ፣ የታሸገ ውሃና ሌሎች ኤክሳይዝ ታክስ በሚከፈልባቸዉ ዕቃዎች ላይ ተግበራዊ ይደርጋል።

የኤክሳይዝ ቴምብር  በወረቀት፤ በዲጂታል ወይም ሚኒስቴሩ በሚወስነው መልክ የተዘጋጀና የኤክሳይዝ ታክስ በሚከፈልባቸው እቃዎች ላይ የሚታተም ወይም የሚለጠፍ ቴምብር ማለት እንደሆነ በዝርዝር ያስቀምጣል።

የገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣዉ በዚህ መመሪያ የኤክሳይዝ ታክስ በሚከፈልባቸው እቃዎች አቅርቦት ሰንሰለት ውስጥ ተሳታፊ የሆነ ማናቸውም ላኪ በእጁ የሚገኙትን የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸው እና የኤክሳይዝ ቴምብር ያልተለጠፈባቸው ወይም ምልክት ያልተደረገባቸዉን ዕቃዎችን
ለገበያ ማዋል አይችልም።

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa