Get Mystery Box with random crypto!

ታዋቂው አቡነ ማር ማሪ ኢማኑዔል በቀጥታ የሚተላለፍ ትምህርት እየሰጡ ሳሉ በስለት ተወጉ! በአውስ | YeneTube

ታዋቂው አቡነ ማር ማሪ ኢማኑዔል በቀጥታ የሚተላለፍ ትምህርት እየሰጡ ሳሉ በስለት ተወጉ!

በአውስትራሊያ ሲድኒ በቀጥታ በኢንተርኔት እየተላለፈ የነበረ መንፈሳዊ ትምህርት እየሰጡ የነበሩት አቡን እና ሌሎች ምዕመናን በስለት ተወጉ።ይህ የሆነው ዋኬሌ በሚገኘው ክራይስት ዘ ጉድ ሼፐርድ በተሰኘው ቤተ-ክርስቲያን በአውስትራሊያ ሰዓት በቆጣጠር ዛሬ ሰኞ አመሻሽ ላይ በነበረ ሥነ-ሥርዓት ነው።

በስለት ጥቃት ከተፈጸመባቸው መካከል የሆኑት አቡነ ማር ማሪ በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ በእንግሊዝኛ በሚያርቧቸው መንፈሳዊት ትምህርቶቻቸው ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በብዙዎች ዘንድ ተደማጭ ናቸው።ጥቃቱን ተከትሎ በርካታ ሰዎች በስለት ተወግተዋል የሚል ሪፖርት የደረሰው ፖሊስ ወደ ሥፍራው ተሰማርቶ ሁኔታውን ያጣራ ሲሆን፣ የሰዎች ሕይወትን ለአደጋ የሚዳርግ ጉዳት አልደረሰም ብሏል።

ፖሊስ አክሎ እንደገለጠው አንድ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ውሎ አድራሻው ወዳልተገለጠ ሥፍራ ተወስዷል።ከጥቃቱ በኋላ በርካታ ሰዎች የተሰባሰቡ ሲሆን ቢቢሲ ያላጣራቸው የማኅበራዊ ሚድያ ቪድዮዎች እንደሚያሳዩት አንዳንድ ሰዎች በሕንፃው እና በአደጋ ጊዜ ሠራተኞች መኪናዎችን ላይ ጥቃት አድርሰዋል።ሥፍራው በከፍተኛ ሁኔታ እየተጠበቀ እንደሆነ የገለጠው ፖሊስ ሰዎች ወደዚያ አካባቢ እንዳይሄዱ አሳስቧል።

የአካባቢው ፖሊስ ጥቃት የደረሰባቸው አቡን ስማቸው ማር ማሪ ኢማኑዔል እንደሆነ አሳውቋል። የኢስተርን ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያንም ከፖሊስ ዘገባ በኋላ የሃይማኖት አባቱን ማንነት ይፋ አድርጓል።ቤተ-ክርስቲያኗ በሰጠችው መግለጫ አባ ኢሳክ የተባሉ ቄስም ጉዳት እንደደረሰባቸው አሳውቋል። ሁለቱም የሃይማኖት አባቶች ለሕክምና ወደ ሆስፒታል ተልከዋል።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa