Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጵያ የሚታየው የኤሌክትሪክ ሀይል እጥረት የተፈራረምኩትን ስምምነት በድጋሚ እንዳጤነው እየገፋ | YeneTube

በኢትዮጵያ የሚታየው የኤሌክትሪክ ሀይል እጥረት የተፈራረምኩትን ስምምነት በድጋሚ እንዳጤነው እየገፋፋኝ ነው ስትል ኬንያ ገለጸች!

ኬንያ ከሁለት አመት በፊት ከኢትዮጵያ ጋር ለ25 አመታት የሚቆይ በኤሌክትሪክ ሽያጭ ዙሪያ የተፈራረምኩትን ስምምነት እንደገና ላጤነው ተገድጃለሁ ስትል ገለጸች። ለዚህም እንደምክንያትነት የጠቀሰችው በኢትዮጵያ ያለው የኤሌክትሪክ አቅርቦት ችግር እየተባባሰ በመሆኑ እና ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ ስለሚገኝ፣ ለእኔ በሚቀርበው የኤሌክትሪክ ሀይል ላይ ችግር መፍጠሩ አይቀርም በሚል ስጋት ስላደረብኝ ነው ብላለች።

የኬንያ የኢነርጂ እና ፔትሮሊየም ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ሃላፊ ዳንኤል ኪፕቶ እንደገለጹለት ስምምነታችንን በመከለስ በቋሚነት ሊቀርብልን ስለሚችለው የሀይል መጠን መፈራረም አለብን፣ እስካሁን የሚቀርብልን የኤሌክትሪክ ሀይል አነስተኛ ነው ሲሉ መናገራቸውም ተካቷል።

Via Addis Standard
@YeneTube @FikerAssefa