Get Mystery Box with random crypto!

እስራኤል “ትክክለኛው ሰዓት ላይ” ለኢራን ጥቃት የአጸፋ ምላሽ እሰጣለሁ አለች! እስራኤል ልክ እ | YeneTube

እስራኤል “ትክክለኛው ሰዓት ላይ” ለኢራን ጥቃት የአጸፋ ምላሽ እሰጣለሁ አለች!

እስራኤል ልክ እንደ ኢራን ሁሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና ሚሳኤሎችን በመተኮስ ‘ትክክለኛው ሰዓት ላይ’ የበቀል እርምጃ እውስዳለሁ አለች።ዓለም አቀፉ ማሕብረሰብ በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ውጥረት ከሚያባብስ እርምጃ እንዲቆጠቡ አገራት ቢያሳስቡም እስራኤል ግን ትክክል ሆኖ ሳገኘው የአጸፋ እርምጃ እውስዳለሁ ብላለች።

ኢራን ለመጀመሪያ ጊዜ በእስራኤል ላይ በፈጸመችው ቀጥተኛ መጠነ ሰፊ ጥቃት ከ300 በላይ ሚሳኤል እና ድሮኖች ወደ እስራኤል ማስወንጨፏ ይታወሳል።ከ300 በላይ የሚሆኑት ሚሳኤሎች እና ድሮኖች ከኢራን፣ ኢራቅ እና ከየመን ወደ እስራኤል የተተኮሱ ቢሆንም አብዛኞቹ ጉዳት ሳያደርሱ በእስራኤል፣ በአሜሪካ እና በወዳጆቿ አማካይነት እንዲከሽፉ ተደርገዋል።

ከኢራን የተወነጨፉ ሚሳኤሎችን በማምከን ድጋፍ ስታደርግ የነበረችው አሜሪካ እስራኤል የበቀል እርምጃ ብትወስድ ተሳታፊ አልሆንም ስትል አስታውቃለች።አምስት አባላት ያሉት የእስራኤል የጦር ካቢኔ እና የአገሪቱ ፓርላማ አባል ቤኒ ጋንትዝ ትክክለኛው ሰዓት ላይ ኢራን ለፈጸመችው ተግባር እስራኤል ዋጋ ታስከፍላታለች ብለዋል።

[BBC]
@YeneTube @FikerAssefa