Get Mystery Box with random crypto!

የዒድ አል ፈጥር በዓል ጨረቃ ሰኞ ማታ ከታየች ማክሰኞ ካልታየች ደግሞ ረቡዕ ይከበራል! የዘንድሮ | YeneTube

የዒድ አል ፈጥር በዓል ጨረቃ ሰኞ ማታ ከታየች ማክሰኞ ካልታየች ደግሞ ረቡዕ ይከበራል!

የዘንድሮው የዒድ አል ፈጥር በዓል ጨረቃ በመጪው ሰኞ ማታ ከታየች ማክሰኞ ካልታየች ደግሞ ረቡዕ አንደሚከበር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታውቋል።ምክር ቤቱ 1 ሺህ 445ኛው ዓመተ ሒጅራ የዒድ አል ፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫውም ፥ የዒድ አል ፈጥር በዓል ጨረቃ ሰኞ ማታ ከታየች ማክሰኞ ሚያዚያ 1 ቀን 2016 ካልታየች ደግሞ ረቡዕ ሚያዚያ 2 ቀን 2016 ዓ.ም አንደሚከበር አስታውቋል።ሕዝበ ሙስሊሙ የዒድ አልፈጥር በዓልን ሲያከብር በጾም ወቅት ሲያደርግ እንደነበረው እርስ በርስ በመደጋገፍና ለተቸገሩ ወገኖች በማካፈል ሊሆን እንደሚገባም አሳስቧል፡፡

Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa