Get Mystery Box with random crypto!

በነዳጅ የሚሰሩ እና ሙሉ በሙሉ በዉጪ ተገጣጥመው ወደ ሃገር ዉስጥ የሚገብ የግል ተሽከርካሪዎች ላይ | YeneTube

በነዳጅ የሚሰሩ እና ሙሉ በሙሉ በዉጪ ተገጣጥመው ወደ ሃገር ዉስጥ የሚገብ የግል ተሽከርካሪዎች ላይ የዉጪ ምንዛሬ እቀባ መጣሉ ተነገረ!

በነዳጅ የሚሰሩ እና ሙሉ በሙሉ በዉጪ የተገጣጠሙ አዉቶሞቢሎች ( የግል አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካዎች)  ወደ ሃገር ዉስጥ እንዳይገብ የዉጪ ምንዛሬ እቀባ መጣሉን ጉሙሩክ ኮሚሽን አስታዉቋል።

የኮሚሽኑ የታሪፍ ምደባ እና የስሪት ሃገር አወሳስን ዳይሬክተር አቶ ካሳዬ አየለ እንደተናገሩት አቀባዉ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ እና በሃይብሪድ/በኤሌክትሪክ እና በነዳጅ/ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች ወደ ሃገር ውስጥ እንዲገቡ ለማበረታት ነዉ ማለታቸውን ካፒታል ሰምቷል።

እቀባው ቀጣይነት እንደሚኖረው የተነገረ ሲሆን በነዳጅ የሚሠሩ አውቶሞቢል ተሽከርካሪዎችን ወደ ሃገር ውስጥ የሚያስገቡ አስመጪዎችም ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ማሳሰቢያ ተሰጥቷቸዋል።

የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር ከሳምንታት በፊት በነዳጅ የሚሰሩ ተሽከርካሪዎችን ማገዱን ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባላት ሲያስታውቅ የገንዘብ ሚኒስቴር በበኩሉ ግን እገዳው ተግባራዊ እንደማይደረግና በዕቅድ ደረጃ ያለ መሆኑን ማስታወቁ ይታወሳል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa