Get Mystery Box with random crypto!

በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ተከስቷል በተባለ የኮሌራ በሽታ ከአራት መቶ የማያንሱ ተማሪዎች መያዛቸውን በዩ | YeneTube

በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ተከስቷል በተባለ የኮሌራ በሽታ ከአራት መቶ የማያንሱ ተማሪዎች መያዛቸውን በዩኒቨርሲቲው ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ተማሪዎች ተናገሩ።

ከተከሰተ አንድ ሳምንት ግድም ሆኖታል ስለተባለው ኮሌራም ሆነ በበሽታው ሳቢያ ስለደረሰ ጉዳት ከዩኒቨርሲቲውም ሆነ ከክልሉ ጤና ቢሮ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ ባለመሳካቱ ሀሳባቸውን ማካተት አልተቻለም።ይሁን እንጂ አስተያየት የሰጡ ተማሪዎች በበሽታው ተይዘው ህክምና ሲደረግላቸው ነበሩ ከተባሉ መካከል አንዳንዶቹ እያገገሙ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በዩኒቨርሲቲው ተከሰተ ስለተባለው ወረርሽኝ ለተማሪዎች በይፋ የተገለጸ ነገር የለም ። ይሁንና የበሽታዉ መንስኤ በአንድ በኩል "በውኃ ብክለት" በሌላ በኩል "የግል ንፅህና ባለመጠበቅ" የመጣ ነው የሚል አስተያየቶች ተሰምተዋል።በዚህም ምክንያት ተማሪዎች ወደ መመገቢያ አዳራሾች ሲገቡ ለጥንቃቄ እንዲታጠቡ ሲደረግ ነበር ተብሏል።

ከተከሰተ አንድ ሳምንት ግድም ሆኖታል ስለተባለው ኮሌራም ሆነ በበሽታው ሳቢያ ስለደረሰ ጉዳት ከዩኒቨርሲቲውም ሆነ ከክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ሰዓት የሞባይል ስልክ ባለመነሳቱ እና ባለመስራቱ ሳቢያ ሀሳባቸውን ማካተት አልተቻለም።በሶማሌ ክልል መቀመጫ ጅግጅጋ ከተማ የሚገኘው ይኸው ዩኒቨርሲቲ ከቀናት በኃላ የተማሪዎች ምረቃ መርሀ ግብር ያከናዉናል ተብሎ ይጠበቃል።

Via DW
@YeneTube @FikerAssefa