Get Mystery Box with random crypto!

በቱርክ ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ ከ1000 በላይ ሰዎችን ገደለ! ቱርክ ከሶሪያ በምትዋሰንበት በደ | YeneTube

በቱርክ ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ ከ1000 በላይ ሰዎችን ገደለ!

ቱርክ ከሶሪያ በምትዋሰንበት በደቡብ ምሥራቋ ጋዚያንቴፕ የተከሰተ ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ከፍተኛ ሞት እና የንብረት ውድመት አስከተለ።የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ጥናት እንዳለው ጋዚያንቴፕ ከተማ ያጋጠመው የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክተር ስኬል 7.8 ሆኖ ተመዝግቧል።የቱርክ ባለሥልጣናት እስካሁን በአደጋው 912 ሰዎች መሞታቸውን ያረጋገጡ ሲሆን በርካታ ሕንጻዎች ፈራርሰዋል።

በሶሪያ ደግሞ ከ700 በላይ ሰዎች መሞታቸውን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።ሕንጻዎች ተደርምሰውባቸው መውጣት ያቃጣቸው በርካታ ሰዎች አሉ እየተባለ ነው።ይህም በሰዎች ላይ የደረሰውን የጉዳት መጠን በትክክል ማወቅ እንዳይቻል አድርጓል ተብሏል።የመሬት መንቀጥቀጡ ስሜት በሌሎች የቱርክ ከተሞች እና በአካባቢው ባሉ አገራት ጭምር ተሰምቷል።

@YeneTube @FikerAssefa