Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን “መንግስት ለህገ ወጥ ስብስቦች ላደረገው ድጋፍ” በይ | YeneTube

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን “መንግስት ለህገ ወጥ ስብስቦች ላደረገው ድጋፍ” በይፋ ይቅርታ ይጠይቅ አለች!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን “መንግስት ሕገ ወጥ ስብስቦች እየፈጸሙ ላሉት ድርጊት የሰጠውን ድጋፍ እና እገዛ በይፋ ቤተ ክርስቲያንን ይቅርታ በመጠየቅ እንዲያቆም” አሳሰበች።መንግስት መግለጫ ባወጣበት እለት በሻሸመኔ ከተማ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች የተፈጸመውን ድርጊት አለማውገዙ የመንግስትን ሚና ያሳያል ስትል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ገለፀች።

ቤተ ክርስትያኗ በመንግስት ኮምኒኬሽን አገልግሎት ባወጣው መግለጫ ዙሪያ ዛሬ ምላሽ የሰጠች ሲሆን “በሻሸመኔ ከተማ በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች የተፈፀመውን ሕገ ወጥ፤ አስነዋሪ እና ጭካኔ የተሞላበት የአደባባይ ግድያ እና የሕዝብ ፍጅት ያልጠቀሰና ሐዘኑን እንኳን መግለጽ ያልቻለበትና ያላወገዘ መሆኑ” የመንግሥትን ግልጽ ሚና በቀላሉ ለመረዳት እንድንችል ያደርገናል ብላለች።

ስልጣንን ተገን በማድረግ የቤተ ክርስቲያንችንን ሕጋዊ ጥያቄ በግድያ፤ በእስር፤ በማዋከብ እና በማስፈራራት ሊፈታ አይችልም የተባለ ሲሆን “ይልቁንም መንግሥት የተጣለበትን መንግሥታዊ ኃላፊነት ያለ አድሎ መፈጸም ሲችል ብቻ መሆኑን” ቤተ ክርስቲያኗ አሳስባለች።

[Addis Zeybe]
@YeneTube @FikerAssefa