Get Mystery Box with random crypto!

በጉራጌ ዞን ለአራተኛ ጊዜ የስራ ማቆም እየተደረገ ነው! በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተ | YeneTube

በጉራጌ ዞን ለአራተኛ ጊዜ የስራ ማቆም እየተደረገ ነው!

በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ፣ ጉብሬ፣ ሙህር አክሊል፣ ሃዋሪያት፣ እዣ እና አገና አካባቢዎች በዛሬው እለት የስራ ማቆምና ከቤት ያለመውጣት አድማ እየተደረገ መሆኑን አዲስ ዘይቤ አረጋግጣለች።

ለአራተኛ ጊዜ እየተደረገ የሚገኘው አድማ ዛሬ ጥር ከማለዳዉ 12:00 ሰዓት የጀመረ ሲሆን ለአንድ ቀን እንደሚቆይ የአዲስ ዘይቤ ምንጮች ገልፀዋል።

እንደ ምንጮቻችን ገለፃ ከዚህ ቀደም እንደተደረገዉ በማህበራዊ ሚዲያ እና በበራሪ ወረቀት ጥሪ መደረጉን አስረድተዋል። በዚህም ከማለደማዉ ጀምሮ የንግድ ሱቆች ተዘግተዋል፣ መደበኛ እንቅስቃሴም እንደወትሮው የለም ሲሉ አክለዋል።

ነሐሴ 3፤ 2014 የመጀመሪያው አድማ ሲደረግ በተመሳሳይ ወር ነሐሴ 2014 ዓ.ም፣ በዚህ ዓመት ህዳር ወር ለሶስተኛ ጊዜ እንዲሁም ዛሬ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ለአራተኛ ጊዜ የስራ ማቆምና ቤት ዉስጥ የመቀመጥ አድማ ተደርጓል።

ትላንት ጥር 28 ቀን 2015 ዓ.ም የጉራጌ ዞን አስተዳደር በሰጠዉ መግለጫ "ጥር 29 ህዝበ ዉሳኔ ከእኛ ዞን ጋር የሚያገናኘው ምንም ነገር የለም" በማለት ማንነታቸዉን ይፋ ያላደረጋቸዉ ኃይሎች ክልል ወይም ዞን የሚመሰረትበት ቀን በማስመሰል በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ቅስቀሳ እያደረጉ ይገኛሉ ብሎ ነበር።

በዚህ ተግባር ላይ የሚሳተፉ ማለትም የመደበኛ የመማር ማስተማር ስራን እንዲስተጓጎል፣ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲቋረጥና የህዝብን ሰላም ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ህገ ወጥ ቡድኖች ላይ መንግስት እርምጃ ለመዉሰድ ይገደዳል ሲል አሳዉቋል።

[Addis Zeybe]
@YeneTube @FikerAssefa