Get Mystery Box with random crypto!

የሱዳን ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት በምዕራብ አርማጭሆ ሰላም በር ከተባለ አካባቢ የተፈናቀሉ ሰዎች እ | YeneTube

የሱዳን ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት በምዕራብ አርማጭሆ ሰላም በር ከተባለ አካባቢ የተፈናቀሉ ሰዎች እስካሁን ተገቢ መጠለያ አላገኘንም ሲሉ አማረሩ።

እንደተፈናቃዮቹ ከወራት በፊት በተፈጠረው ወቅታዊ ሁኔታ መኖሪያ አካባቢቸውን ቢለቁም ተገቢ የመጠለያ ድጋፍ አልተደረገላቸውም፡፡የከተማ አስተዳደሩ ከዚህ በፊት መጠለያ ሰትጫቸዋለሁ ቢልም ተፈናቃዮች ግን በቂ እንዳልሆነ ተናግረው ነበር፡፡ የአማራ ክልል አደጋ መከላከል፣ ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያና ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ኮሚሽነር ዘለዓለም ልጅለም በበኩላቸው 1ሺህ 800 ያህል ተፈናቃዮች መኖራቸውን የሚያመለክት መረጃ እንደደረሳቸው አመልክተው አጠቃላይ ጉዳዩን የሚያጠና ቡድን ነገ ወደ ቦታው እንደሚሄድም ተናግረዋል፡፡

[DW]
@YeneTube @FikerAssefa