Get Mystery Box with random crypto!

ዕቃ ለማውረድና ለመጫን የተጋነነ ዋጋን የሚጠይቁ ጫኝና አውራጆችን የማጣራት ሥራ በማድረግ ሕጋዊ እ | YeneTube

ዕቃ ለማውረድና ለመጫን የተጋነነ ዋጋን የሚጠይቁ ጫኝና አውራጆችን የማጣራት ሥራ በማድረግ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሸን አስታወቀ።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት፣ ለዕቃ ማውረድና መጫን የሚከፈለው ገንዘብ በዕቃ ባለቤትና በአውራጁ መካከል በሚደረገው ስምምነት እንጂ አውራጁ በተመነው ዋጋ ብቻ እዳልሆነ አስታውቀዋል።የዕቃው ባለቤት ከፈለገ እቃውን በራሱ የማውረድና የመጫን ሙሉ መብት እንዳለ ያመለከቱት ሃላፊው ፣ ባለቤቱን የመጫንና የማውረድ መብት የሚከለክሉ እንዲሁም ለመሥራትም የተጋነነ ዋጋ የሚጠይቁ ጫኝና አውራጆች ተጣርተው ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድባቸው አስታውቀዋል።
ከዚህ በፊት በተለይ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 9፣ ወረዳ 10 እና ወረዳ 12 በጎሮ፣ በቡልቡላና በሰሚት አካባቢ እንዲሁም በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ በኮዬ ፈጬና የጋራ መኖሪያ ቤቶችና በመናኸሪያ አካባቢ፣ በጫኝና በአውራጅ ሥራ የተደራጁ 170 የሚሆኑ ሰዎች ለራሳቸው ከቤት ሆነው ሌሎች ሰዎችን በመቅጠር በህብረተሰቡ ላይ የተለያዩ ወንጀሎችን ሲያስፈጽሙ ተደርሶባቸው ህጋዊ እርምጃ እንደተወሰደባቸው ጠቁመዋል።

[EPA]
@YeneTube @FikerAssefa