Get Mystery Box with random crypto!

በትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት አለፈ። ዛሬ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት በምስራቅ ጎጃም አስተዳደር ዞ | YeneTube

በትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት አለፈ።

ዛሬ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት በምስራቅ ጎጃም አስተዳደር ዞን በሞጣ ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሦስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የሞጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

መነሻውን ከአዲስ አበባ ወደ ባህር ዳር የሆነ የህዝብ ማመላለሻ ንብረትነቱ የቻይና መንገድ ስራዎች ከሆነ ፒካፕ መኪና ጋር በመጋጨቱ ነው አደጋው የተፈጠረው።

በህዝብ መኪና ውስጥ ያሉ አራት ሰዎች ላይም ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

የግጭቱ መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑን ከሞጣ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@YeneTube @FikerAssefa