Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በትግራይ ክልል የነበሩ የኤርትራ ስደተኞች በህወሃት ታጣቂዎች ጉዳት እ | YeneTube

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በትግራይ ክልል የነበሩ የኤርትራ ስደተኞች በህወሃት ታጣቂዎች ጉዳት እንዳይደርስባቸው ሲከላከል እንደነበር ከስደተኞች መስማቱን የስደትና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጄንሲ አስታወቀ፡፡

የኤጄንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ በትግራይ ክልል በሚገኙ የስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ስደተኞች ከጥቃት እንዲጠበቁ መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ ሚና መጫወቱን አስታውቀዋል፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ ራሳቸው ከ15 በላይ ስደተኞችን ማነጋገራቸውን የገለጹ ሲሆን ለህይወታቸው በመፍራት ከሽመልባና ከጻጽ መጠለያ ጣቢያዎች መውጣታቸውንና መከላከያ ሰራዊት ጥቃት እንዳይደርስባቸው እንደተከላከለላቸው እንደገለጹላቸው ተናግረዋል፡፡

አቶ ተስፋሁን የኢትዮጵያ መንግስት “የሕግ ማስከበር ዘመቻ” ከመጀመሩ በፊት በሽመልባ 8ሺ፤ በህጻጽ ደግሞ 11 ሺ 500 ስደተኞች ይኖሩ እንደነበር ገልጸው አሁን ግን በነዚህ መጠለያ ጣቢዎች ውስጥ ምንም ስደተኛ እንደሌለ ተናግረዋል፡፡

በትግራይ በሚገኙ አራት የሥደተኛ መጠለያ ጣቢዎች 92ሺ ስደተኞች ይገኙ እንደነበር የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ ከነዚህ ውስጥ በሁለቱ ጣቢያዎች ውስጥ የነበሩ ስደተኞች አሁን ላይ በአማራ ክልል፣ በአዲስ አበባና በዛው በትግራይ ክልል እንደሚገኙ ገልጸዋል።

በሽመልባና በህጻጽ የስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች ይኖሩ ከነበሩት መካከል አራት ሺ የሚሆኑ ስደተኞች አሁን ላይ ወደ ማይ አይኒ እና አድሀሩሽ መጠለያ ጣቢያዎች መግባታቸውን አቶ ተስፋሁን ተናግረዋል፡፡ በስደተኞቹ ላይ ከፍተኛ ችግር መድረሱን፤መጎዳታቸውንና ሌሎችንም በተመለከተ ወደፊት የማጣራት ስራ እንደሚሰራ አቶ ተስፋሁን ተናግረዋል፡፡
በሱዳን የሚገኙ የኢትዮጵያ ስደተኞችን በተመለከተ መቸ ወደ ሀገር ቤት ይመለሳሉ የሚለውን በትክክል ማስቀመጥ እንደሚያስቸግር ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

ቁጥራቸው ወደ 60 ሺ እንደሚጠጋ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን መግለጹን ያነሱት አቶ ተስፋሁን ሁሉም ዜጎቻችን ወደሀገራቸው እንዲመለሱ እንፈልጋለን ብለዋል፡፡

ሱዳን ያሉት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ ሀገራቸው እንዲመጡ እንፈልጋለን ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ 

Via:- Alian
@Yenetube @Fikerassefa