Get Mystery Box with random crypto!

አንችን_ጥበብ ድርሰት ጥበብ ነው ነጋሪት ግጥም ጥበብ ነው ነጋሪት ሙዚቃ ጥበብ ነው ነጋሪት ስዕል | 💖የኔ ፍቅር 😘

አንችን_ጥበብ

ድርሰት ጥበብ ነው ነጋሪት
ግጥም ጥበብ ነው ነጋሪት
ሙዚቃ ጥበብ ነው ነጋሪት
ስዕል ጥበብ ነው ነጋሪት

ትልቅ አቅም ያለው
ጥበብ ነው…

እዉነትን የሚገልፅ መስካሪ
ስሜትን የሚያሳይ ነጋሪ
ያለዉን አቅም ድርሰት ላይ ተጠቅሞ
ልቦናዉን ከፍቶ ግጥምን ለቃቅሞ
በጥዑም ለመናገር ሙዚቃ አቀናብሮ
በጥልቅ ለማሳየት ወረቀት ከእርሳስ ሸራ ከቀለማት አፋቅሮ
የብዕሩ ጠብታ አንደበት አዉጥቶ እራሱ እስኪናገር
ምንም ቅኔ ቢዘርፍ ምንም ቃል ቢጠቀም ስላች ሊናገር
ሊገልፅሽ ሞክረ ይባላል እንጂ ስላች ሲጠበብ
ገልፆሻል ማለት አይቻልም እማ አንችን ጥበብ።

I love you mom!

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir