Get Mystery Box with random crypto!

#ምህረት_እሻለሁ! ××××××××××××× መሄድሽን ተከትሎ… ሌተ ቀን ሳይመርጥ ቤታችን በዝናብ ያ | 💖የኔ ፍቅር 😘



#ምህረት_እሻለሁ!
×××××××××××××

መሄድሽን ተከትሎ…
ሌተ ቀን ሳይመርጥ ቤታችን በዝናብ ያምፃል
ልክ እንደ ጨለማ በጉም ይሸፈናል
እንደ ሙዚቃ ምት በመብርረቅ ይና'ጣል
እንደ ተራበ ሆድ ነጎድጓዱ ይጮሃል

መሄድሽን ተከትሎ…
ቤቱ በጥቁር ዳመና በብርድ ተከለለ
ዉስጥጤ እንዳለው ስሜት እንባን አዘለ
ከቤት እደወጣሽ ክረምት ያለወቅቱ
ቤታችን ዉስጥ ~ ነግሶብኛል እቱ

የክረምቱ ቋንቋ ይህ ነው…

ዝናቡ ፍቅርሽ ነው ነጎድጓዱ አንደበት
መብረቁ ፀፀት ነው የመሄድሽ ዉጤት
ብርዱ ናፍቆት ነው ጉሙ ያንች ትዝታ
ዳመናው ተስፋ ነው የህልም ገበታ

ክረምቱ ቋንቋ ነው ሌተ ቀን ወቃሼ
መብረቅ ዳኛ አቁሙ በብርድ ከሳሼ
ዝናብ አቃቤ ህግ ነጎድጓድ ምስክር
ጉሙ ታዛቢ ነው ዳመናው ያንች ፍቅር

ጥፋተኛ በዳይ ግፍ ሰሪ ነኝ እኔው
ነጎድጓድ ስለኔ ያለው ትክክል ነው
ዝናብ የጠየቀኝ ጥያቄ በጉሙ ፊት
ብርዱ ልክ ነው መልስ የለዉም የኔ አንደበት
መብረቁ ጥፋቴ ያስቆጣው ይመስላል
ዳመናው ስህተቴን በማመኔ ማቅለያ ጠይቋል…
ዳመናው ለጠየቀልኝ ማቅለያ አመሰግናለሁ
እባኮዎን መብረቅ ምህረትን እሻለሁ!?




የመብረቁን ፍርድ ለናንተ ተውኩ:: U can Inbox Me!!

┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir