Get Mystery Box with random crypto!

አስቢኝ_ሳስብሽ አስታዉሽኝ ቻው ልልሽ ብገደድም አስቢኝ ካንች እርቄ ሩቅ ብሆንም በልቤ ይዤሽ እዞ | 💖የኔ ፍቅር 😘

አስቢኝ_ሳስብሽ

አስታዉሽኝ ቻው ልልሽ ብገደድም
አስቢኝ ካንች እርቄ ሩቅ ብሆንም
በልቤ ይዤሽ እዞራለሁ በሄድኩበት
አስታዉሽኝ አስታዉስሻለሁ ሆኘ ካለሁበት
አትርሽኝ ግድ የለም አስቢኝ
ሰው መንገደኛ ነው እንገናኛለን
ተለያይተን በቆየነው ጊዜ
በልባችን ያለው የመዉደድ አባዜ
ከኔ ልብ አይጠፋም እዳይጠፋ ከልብሽ
ምንም ባንተያይ አስቢኝ ሳስብሽ
ይድረስሽ ናፍቆቴ ጫካዉን አቋርጦ
ይሰማሽ መዉደዴ ከንፋስ ተዋህዶ
በከፋሽም ጊዜ አይደለሽም ብቸኛ
እኔም ይከፋኛል ሲከፋሽ ክፉኛ
ያሳለፍነው ጊዜ ያሳለፍነው ደስታ
ዛሬ ቢቋረጥም ቢሆንም ትዝታ
አስቢው ዉብ ነበር አይደለም ቅዠት
ዳግም እንድንገናኝ እሱ አለነ ምክኒያት
ለሰው ሌላ ቀን ይመጣል ሌላም ወር
ሌላም ጊዜ ይመጣል ሌላም ሰው
ግን አንች ለኔ ሁሌም ትኖሪያለሽ ከልቤ
ሁሉም ቢቀያየር አጠፊም ካሳቤ
መቼም አይጠፋም ካይኔ ያንች እና የኔ
ሁሌም አስታዉስሻለሁ ባትሆኝም ከጎኔ
ቦታየን አታጥፊው ከልብሽም ሰፈር
ከኔ ልብ አጠፊም ወድሻለሁ ስኖር
መች ጠገብኩሽ እና
አስቢኝ ሳስብሽ ወድሻለሁ እና…።



┄┅┅┄┅✶ ✶┅┄┅┅┄
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ #Share
@Yenefekir
@Yenefekir