Get Mystery Box with random crypto!

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት⚽

የቴሌግራም ቻናል አርማ yemaledasport — Maleda Sport ማለዳ ስፖርት⚽ M
የቴሌግራም ቻናል አርማ yemaledasport — Maleda Sport ማለዳ ስፖርት⚽
የሰርጥ አድራሻ: @yemaledasport
ምድቦች: ስፖርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.02K
የሰርጥ መግለጫ

⚽ዓለም ዓቀፍ የእግር ኳስ ክስተቶችን በተለየ መልኩ ወደ እርስዎ የምናደርስበት ለእግር ኳስ መረጃዎች ትክክለኛው ቻናል👍👌
⚽ ጥልቅ እይታና ሚዛናዊ አቀራረብ መለያችን ነው! በአማራ ኤፍ ኤሞችና አማራ ራዲዮ ላይ በኮሜንታተርና መደበኛ ፕሮግራም በቀጥታ ስርጭት መከታተል ይችላሉ⚽
Amazing channel on telegram 👏🙌

👇Admin👇
👉 @alrightmama 👉 @Hello_CJ

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-08-22 20:30:08
የእንግሊዝ ታላቁ ደርቢ ማንቸስተር ዩናይትድ ከሊቨርፑል በኦልድትራፎርድ ስቴዲየም በማለዳ ስፖርት ይከታተሉ።

ሀሳብና አስተያየት አሁን ይላኩልን።

በኦልድትራፎርድ ስቴዲየም ማንቸስተር ዩናይትድ ከሊቨርፑል የሚያደርጉትን ታሪካዊ ፍልሚያ በማለዳ ስፖርት በቀጥታ ኮሜንትሪ በአሚኮ በአሉበት እናደርሳለን።

አብረውን ስለሚያመሹ እጅግ አድርገን እናመሰግናለን።

የጨዋታ ግምትና አስተያየት ያድርሱን።
ዩናይትድ ወይስ ሊቨርፑል የመጀመሪያውን ድል በኦልድትራፎርድ ማን ያስመዘግባል ?!

ይጻፉልን።

የፕሮግራሙ ስፖንሰር 6655 አጭር የጽሁፍ መልእክት ነው።

ለስፖርትና ጤና መረጃዎች 6655 ላይ ok ብለው ይላኩ ይመዝገቡ መረጃዎችን ያግኙ።

መልካም ምሽት
1.4K viewsDear Mama, edited  17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 14:22:35
በሁኔታዎች የማይወሰነው ታላቁን የደርቢ ጨዋታ በማለዳ ስፖርት በቀጥታ ኮሜንትሪ ወደ አድማጮቹ ይደርሳል።

የክለቦች ወቅታዊ ብቃት ከደርቢነቱ የማይገድበው የእንግሊዝ የምንግዜም ትልቁ ደርቢ ነገ አመሻሹን 4:00 በኦልድትራፎርድ ሲከናወን ማለዳ ስፖርት ትንቅንቁን በቀጥታ በአሉበት ያደርሳል።

ማንቸስተር ዩናይትድ ከሊቨርፑል ከማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትስስሮች ጋር ቁርኝት ያለው ፍልሚያ ደጋፊዎች እና ተጫዋቾች አንዱ የሌላኛውን ደስታ ፍጹም የማይቀበሉት ደርቢ በማለዳ ስፖርት በቀጥታ ኮሜንትሪ በአሚኮ ነገ ምሽት ይጠብቁን።
1.4K viewsDear Mama, edited  11:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 16:26:56
ሀሪ ኬን ሁለት ክብረወሰኖችን ባስመዘገበበት ጨዋታ ቶትንሀም ወልቭስን 1-0 በማሸነፍ የፕሪሚየር ሊጉ መሪነቱን ተረክቧል።

በሰሜን ለንደን ወልቭስን ያስተናገደው የአንቶኖ ኮንቴው ቶትንሀም በሀሪ ኬን ብቸኛ ጎል በማሸነፍ የደረጃ ሰንጠረዡን መሪነት ተረክቧል።

ባለሜዳው ክለብ አንጻራዊ ፈተናዎችን ባስተናገደበት ጨዋታ ሀሪ ኬን ለአንድ ክለብ 185 የፕሪሚየር ሊግ ጎሎችን በማስቆጠር የሰርጂዮ አጉዌሮ ክብረወሰንን የግሉ አድርጓል።

እንግሊዛዊው ኮከብ ከዚህም በተጨማሪ በነጩ መለያ 250 ኛ ጎሉን ያስቆጠረበትን አስደናቂ እንቅስቃሴ አድርጓል።

ወቅታዊ መረጃዎችን በማለዳ ስፖርት ዩቲዩብ ቻናል ይከታተሉ።

የዝውውር ዜናዎች አጫጭር ጉዳዮች ይዳሰሳሉ።

ቻናሉን ሰብስክራይብ በማድረግ የማለዳ ስፖርት ቤተሰብ ይሁኑ!

https://youtube.com/channel/UC2CpNXbHM1FUTjH7gn3Cbcg

መረጃዎችን በድምፅ ለማግኘት በቴሌግራም ይቀላቀላሉን።

https://t.me/yemaledasport

አጫጭር ጉዳዮችን በቲክቶክ ለመመልከት

https://vm.tiktok.com/ZMNxytXRU/
1.5K viewsDear Mama, edited  13:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 12:04:29 የዛሬ ፕሮግራም የውጭ ዝውውሮች እና አጫጭር ጉዳዮች
1.8K viewsDear Mama, edited  09:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 12:04:12 የዛሬ ፕሮግራም የሀገር ውስጥ መረጃዎች
1.7K viewsDear Mama, edited  09:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 09:39:12
ማለዳ ስፖርት ዛሬ ረፋድ ከ 5:00-6:00 በሚኖረው ቆይታ የመሀመድ ሳላን በጎ ተግባር እናነሳለን።

በግብፅ ጊዛ ከተማ በእሳት የተቃጠለውን ቤተክርስቲያን እንደገና እንዲገባ እና አገልግሎት እንዲጀምር 155,000 ዶላር ለግሷል።

ከሌሎች የሀገር ውስጥና የውጭ መረጃዎች ጋር በአሚኮ ወደ እርስዎ እንደርሳለን።

የፕሮግራሙ ስፖንሰር ዶክተር ክንድዬ እንድሪስ የጥርስ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ ነው።
1.8K viewsDear Mama, edited  06:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 20:03:43
በአንፊልድ ስቴዲየም የውድድር አመቱ የሊቨርፑል የመጀመሪያ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ በማለዳ ስፖርት ይከታተሉ። አብረውን ያምሹ የጨዋታ ግምትና አስተያየት አሁን ይላኩልን።

ሊቨርፑል በአንፊልድ ስቴዲየም አዲሱን የውድድር አመት የመክፈቻ ጨዋታ ምሽት 4:00 የደቡብ ለንደኑን ክርስቲያል ፓላስ በማስተናገድ ይጀመራል።

የርገን ክሎፕ በሊቨርፑል የመጀመሪያ ጨዋታቸው በሽንፈት እንዲጀምሩ ምክንያት የሆነው ክርስቲያል ፓላስ ዛሬስ በአዲሱ የውድድር አመት የመጀመሪያ ድል ለማስመዝገብ ወደ ሜዳ ለሚገባው ሊቨርፑል ፈተና ሆኖ ይቀርብ ይሆን?

የሳምንቱ የመጨረሻ ጨዋታ ሊቨርፑል ከፓላስ በማለዳ ስፖርት ይከታተሉ። ማለዳ ስፖርት ስቱዲዮውን አንፊልድ ስቴዲየም ገጥሞ በአሚኮ በአሉበት ያደርሳል።

አስተያየት ይላኩልን።
ከእኛ ጋር ስለሚያመሹ እናመሰግናለን
መልካም ቆይታ!
1.8K viewsDear Mama, edited  17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 17:58:11
በሴካፋ የቻምፒየንስ ሊግ የማጣሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋሪዬርስ ኩይንን 9-0 አሸነፈ።

ለሴቶች የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫ ለመሳተፍ በሴካፋ ዞን ማጣሪያ ጨዋታ ወደ ታንዛኒያ አቅንቶ በመጀመሪያው ጨዋታ ዋሪዬርስ ኩይንን የገጠመው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሴቶች ቡድን 9-0 በማሸነፍ አመርቂ ድል አስመዝግቧል።

በኢትዮጵያ ሴቶች እግር ኳስ በዙፋን ላይ የተቀመጠችው ሎዛ አበራ አምስት ጎሎችን ስታስቆጥር መዲና ዐወል አራት ጎሎችን በስሟ አስመዝግባለች።
1.5K viewsDear Mama, edited  14:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ