Get Mystery Box with random crypto!

Maleda Sport ማለዳ ስፖርት⚽

የቴሌግራም ቻናል አርማ yemaledasport — Maleda Sport ማለዳ ስፖርት⚽ M
የቴሌግራም ቻናል አርማ yemaledasport — Maleda Sport ማለዳ ስፖርት⚽
የሰርጥ አድራሻ: @yemaledasport
ምድቦች: ስፖርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.02K
የሰርጥ መግለጫ

⚽ዓለም ዓቀፍ የእግር ኳስ ክስተቶችን በተለየ መልኩ ወደ እርስዎ የምናደርስበት ለእግር ኳስ መረጃዎች ትክክለኛው ቻናል👍👌
⚽ ጥልቅ እይታና ሚዛናዊ አቀራረብ መለያችን ነው! በአማራ ኤፍ ኤሞችና አማራ ራዲዮ ላይ በኮሜንታተርና መደበኛ ፕሮግራም በቀጥታ ስርጭት መከታተል ይችላሉ⚽
Amazing channel on telegram 👏🙌

👇Admin👇
👉 @alrightmama 👉 @Hello_CJ

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-27 21:41:29
መድፈኞቹ 100% የማሸነፍ ግስጋሴያቸውን ባስቀጠሉበት የኤምሬትስ ጨዋታ ፉልሃምን 2-1 በማሸነፍ ጣፋጭ ድል አስመዝግበዋል።

ጋብሪኤል ማጋሊሽ ሁለት የተለያዩ የጨዋታ እንቅስቃሴ ባሳለፈበት ጨዋታ ለመድፈኞቹ የማሸነፊያ ጎል አስቆጥሯል።

ማርቲን ኦዲጋርድ አርሰናልን አቻ ያደረገ ጎል ያስቆጠረ ሲሆን አሌክሳንደር ሚትሮቪች ለፉልሃም ብቸኛ ጎል ከመረብ አገናኝቷል።

አብራችሁን ስላመሻችሁ እናመሰግናለን።
359 viewsDear Mama, edited  18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 19:10:46
አስደናቂ የጨዋታ ውጤቶች የተመዘገቡት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውሎ ቀጥሎ ከደቂቃዎች በኋላ 1:30 ላይ በኤምሬትስ ስቴዲየም የለንደን ደርቢን አሁን በማለዳ ስፖርት ይከታተሉ።

ሀሳብና አስተያየት ይላኩልን።

አርሰናል አራተኛ ተከታታይ ድል ለማስመዝገብ አንድም ጨዋታ ያልተሸነፈውን ፉልሃም በኤምሬትስ ያስተናግዳል።

ጨዋታውን በማለዳ ስፖርት በአሚኮ በኤፍ ኤፍ ኤም ጣቢያዎችን እንዲከታተሉ ተጋብዘዋል።

የዛሬ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ውጤቶችን እንዴት ይገልጿቸዋል።

አርሰናል ወይስ ፉልሃም ?! በውድድር አመቱ ምንም ጨዋታ ያልተሸነፉት ሁለቱ ክለቦች ማን ያሸንፋል።

የጨዋታ ግምትና አስተያየት አሁን ይላኩልን።
አብረውን ስለሚያመሹ ከልብ እናመሰግናለን።
590 viewsDear Mama, edited  16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 18:02:43
ለቻን የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ በታንዛኒያ ሩዋንዳን የገጠሙት ዋሊያዎቹ ያለ ጎል አቻ ተለያይተዋል።

ወደ አልጀርስ ለማቅናት የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ የደረሰው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በመጀመሪያው የደርሶ መልስ ጨዋታ ከሩዋንዳ ጋር ያለ ጎል አቻ ተለያይቷል።

በታንዛኒያ ቤንጃሚን ምካፓ ስቴዲየም ሩዊንዳን ያስተናገደው የአሰልጣኝ ውበቱ አባተው ዋልያዉ ኳስና መረብን ማገናኘት አልቻለም።

ወደ ሰሜን አፍሪካዊቷ አልጀሪያ ለማቅናት ሁለቱ አገራት የመልሱን ጨዋታ የፊታችን ነሀሴ 29 ቀን 2014 ዓ.ም በሩዋንዳ ያከናውናሉ።
974 viewsDear Mama, edited  15:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 10:54:20
የለንደን ደርቢ በማለዳ ስፖርት በቀጥታ ኮሜንትሪ ወደ እርስዎ ይደርሳል።

ቅዳሜ ምሽት 1:30 ላይ በለንደን ደርቢ አርሰናል ከፉልሃም ጋር የሚያደርጉትን ጨዋታ ማለዳ ስፖርት በቀጥታ ኮሜንትሪ በአሚኮ ወደ እርስዎ ያደርሳል።

የመድፈኞቹ 100% የማሸነፍ ግስጋሴ ይቀጥል ይሆን ?!
1.0K viewsDear Mama, edited  07:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 20:10:22
የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የምድብ ድልድል ይፋ እየተደረገ የሚገኝ ሲሆን ባየርን ሙኒክ እና ባርሰሎና ዳግም በአንድ ምድብ ተደልድለዋል።

ሮበርት ሌቫንዶቭስኪ ወደ አሊያንዝ የሚመለስ ይሆናል።

ሳዲዮ ማኔ ከሮበርት ሌቫንዶቭስኪ ጋር ይፋለማሉ።

የ 8_2 አስደንጋጭ ውጤት ዳግም በሁለቱ ክለቦች የምድብ ጨዋታ ይታወሳል።

ሙኒክ ወይስ ባርሰሎና ?!

ኦሊቬር ካህን ድልድሉን ሲመለከት መሳቅ አልቻለም ... ለምን ይሆን ?!
1.1K viewsDear Mama, edited  17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 14:45:45
ከአንቶኒ ጋር በግል ጉዳዮች ዙሪያ ከስምምነት ላይ የደረሰው ማንቸስተር ዩናይትድ ማርኮ አሴንሶን ከሪያል ማድሪድ ለማስፈረም እንቅስቃሴ ጀምሯል።

ከአምስተርዳም ለመውጣት በእጅጉ ፍላጎት ያለውን ብራዚላዊ ኮከብ አንቶኒን ለማስፈረም ሰፊ እድል እንዳለው የሚነገርለት ዩናይትድ ማርኮ አሴንሶን በ $30 ሚሊዮን ወደ ኦልትራፎርድ ለማምጣት እንቅስቃሴ መጀመሩ ተገልጿል።
1.1K viewsDear Mama, edited  11:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 17:53:13
ክለባችሁ መጓዝ ከሚገባው እረጅም እርቀት አንጻር መጓዝ አለመቻሉ ቅር ቢያሰኝም በግላችሁ አስደናቂ እንቅስቃሴ ማድረግ ችላችኋል።

በሴካፋ ዞን የሴቶች የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በግማሽ ፍጻሜው በዩጋንዳው ሺ ኮርፖሬትስ 2-1 ተሸንፎ ከውድድሩ ውጭ ሆኗል።

በክለቡ የምድብ ጨዋታ ድሎች ሂደት ላይ ሎዛ አበራ እና መዲና አወል በተለይም ጎሎችን በማስቆጠር እረገድ ስኬታማ ቆይታን በታንዛኒያ አሳልፈዋል።
1.2K viewsDear Mama, edited  14:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 11:50:14 የመጀመሪያው አጋማሽ
1.3K viewsDear Mama, edited  08:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 00:06:08
የደርቢው ወሳኝ ጨዋታ በማንቸስተር ዩናይትድ 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል።

ኤሪክ ቴን ሃግ በማንቸስተር ዩናይትድ የመጀመሪያውን የፕሪሚየር ሊግ ድላቸው በሊቨርፑል ላይ አስመዝግበዋል።

ማንቸስተር ዩናይትድ በጄደን ሳንቾ እና ማርከስ ራሽፎርድ ጎሎች ድል ሲያስመዘግብ ሞ ሳላ የሊቨርፑልን ብቸኛ ጎል አስቆጥሯል።
1.4K viewsDear Mama, edited  21:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ