Get Mystery Box with random crypto!

ጠብታ የእይታ አድማስ አንድ ንጉስ ሶስት ማየት የተሳናቸውን ሰዎች ጠርቶ መሀላቸው አንድ | የማለዳ ብስራት

ጠብታ

የእይታ አድማስ

አንድ ንጉስ ሶስት ማየት የተሳናቸውን ሰዎች ጠርቶ መሀላቸው አንድ ዝሆን አቆመና ሁሉም ዝሆኑን በመንካት (በመዳሰስ) ዝሆን ማለት ምን አይነት እንስሳ እንደሆነ እንዲናገሩ አዘዛቸው።
የዝሆኑን ጭራ የነካው ማየት የተሳነው "ዝሆን ማለት እንደ አባብ አይነት ያለ እንስሳ ነው" ሲል ተናገረ።

ሆዱን ሲዳስስ የነበረው ሁለተኛው ማየት የተሳነው ደግሞ "ዝሆን ማለት እንደ ቤት ያለ ሰፊ መጋዘን ነው" ሲል ተናገረ። እግሩን ሲዳስስ የነበረው ሶስተነኛው ሰው "ዝሆን ማለት እንደ ዛፍ ያለ እንስሳ ነው" ሲል አሰበ። በዚህም መቋጫ የሌለው ክርክር ውስጥ ገቡ።

ማንኛችንም ዓለምን የምንረዳት እንድትሆንልን በምናስበው ልክ ነው። ለአንደኛው ሚዛን የደፋለት ለሌላኛው ይቀልበታል። የሰው አስተሳሰብ በአከባቢው ተፅኖ ስር የወደቀ በመሆኑ የመረዳት አቅማችን ጥልቀት የሚወሰነው ባለን ተሞክሮና በማሰብ ምጥቀታችን ልክ ስለሆነ እያንዳንዳችን የሀሳብ ሙግታችን ይቀጥላል።

ለቻናሉ አዲስ የሆናቹ Join በማድረግ ተቀላቀሉ

@yemaledabisrat
@yemaledabisrat
@yemaledabisrat