Get Mystery Box with random crypto!

የማለዳ ብስራት

የቴሌግራም ቻናል አርማ yemaledabisrat — የማለዳ ብስራት
የቴሌግራም ቻናል አርማ yemaledabisrat — የማለዳ ብስራት
የሰርጥ አድራሻ: @yemaledabisrat
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.14K
የሰርጥ መግለጫ

👉 ካነበብኳቸው የብእር ትሩፋቶች፣ ከሰማኋቸው መረጃዎችና ካየኋቸው እውነቶች ምርጥ ምርጡን የማቀርብበት ቻናል ነው። ቤተሰብ ይሁኑ!

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-09 01:16:15
933 views22:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 12:42:42 ከታሪክ ማኅደር ለፈገግታ

መንጌና የደሴ ሕዝብ

መንግስቱ ኃ/ማርያም ወደ ሥልጣኑ መጨረሻ አከባቢ ደሴ ሄዶ ህዝቡን ሰብስቦ ነበር:: እናም የደሴ ሰው የባህል ልብስና የባህል ጫማ ይሰጡታል― ስጦታ:: መንጌም ጫማውን ሲሞክረው ተለክቶ እንደተስራ ግጥም ይላል::

መንጌም “የጫማ ቁጥሬን እንዴት አወቃችሁት?” ሲል በአግራሞት ጠየቀ::

በደሴ ነዋሪ የነበሩ አንድ ሽማግሌ “አስራ ሰባት አመት ሙሉ ከላይ ሆኖ የረገጠንን ጫማ/እግር እንዴት ቁጥሩ ይጠፋናል!” አሉት ይባላል::

@yemaledabisrat
@yemaledabisrat
@yemaledabisrat
921 views09:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 11:33:44 የነጠፉ ብእሮች

አመለካከት

አዎንታዊ አመለካከት ያላቸው ሰዎች ለእያንዳንዱ ችግር መፍትሔ አላቸው። አሉታዊ አመለካከት ያላቸው ሰዎች ደግሞ ለእያንዳንዱ መፍትሔ ችግሮች አሏቸው። አሉታዊ አመለካከት ካለቸው ሰዎች ራቁ።
አልበርት አንስታይን

ብቸኝነት

ብቸኝነት ሌላ ሰውን የምታጡበት ሁኔታ ሲሆን፣ ለብቻ መሆን ግን ራሳችሁን የምታገኙበት ሁኔታ ነው!
ኦሾ

የ"ዛሬ" ምሥጢር

ልትኖር እየተዘጋጀህ ከሆነ፣ ጨፍነሃል ማለት ነው። ህይወት ከፊትህና ወደፊት ያለ ከመሰለህ ያኔም ጨፍንሃል፤ ምክንያቱም ወደፊት የሚባል ነገር የለም። ያለው ዛሬ ነው። አብዛኞቻችን ጊዜያችንና ህይወታችን የሚያልፈው አንድ ቀን ያልፍልኛል፤ አንድ ቀን የተሻለ እኖራለሁ ብለን ዛሬን ችላ በማለት ነው። ነገ የለም። ያሉት ተከታታይ ዛሬዎች ናቸው። ዛሬን ስትኖር ማየት ትጀምራለህ፤ ልትጨፍን አትችልም።

ዶ/ር ዳዊት ወንድማገኝ

ነጻነት

ይህ ነጻነት ደግሞ ከሰው ልጅ ፍላጎት ውጪ የሚሆንበት አንዳች ምክንያት የለም... ከዚህ በተጨማሪ ሕይወትን ያለአንዳች የሞራልና የወግ ገደብ የሚኖራት ሰው ደስታውም እንዲሁ ሙሉ እንደሚሆንና እንዲህ ዓይነቱ ደስታ ደግሞ ለጊዜው አስደስቶ የሚሰወር ሳይሆን በምድራዊ ሕይወት እስካለ ድረስ የሚከተል ነው ።

ፍሬድሪክ ኒቼ

ለቻናሉ አዲስ የሆናቹ Join በማድረግ ተቀላቀሉ

@yemaledabisrat
@yemaledabisrat
@yemaledabisrat
839 viewsedited  08:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 00:14:55 የምትፈልጉትን ፎቶ በእንጨት ላይ ለማሳተም እና በቆዳ ላይ የወዳጅ ዘመዶን ፎቶ እንዲህ በሚያስደንቅ መልኩ Engrave ለማስደረግ በ 0973169617 ላይ በመደወል ያነጋግሩን
407 viewsedited  21:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 00:14:26
595 views21:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 21:20:01 ከፈላስፋዎች ጉያ

ሊቁ ኮንፊሽየስና ደቀ መዝሙሩ ትዙሉ

ታላቁ የቻይና ፈላስፋና መምህር ኮንፊሽየስ በተራራ ላይ ተቀምጦ ድንኳን ዘርግቶ እያስተማረ በነበረበት አንድ ቀን ደቀ-መዝሙሩ ትዙሉን ውሃ እንዲያመጣለት አዘዘው። ትዙሉም ውሃ ሊያመጣ ወደ ወንዝ ሲወርድ ነብር ያጋጥመውና ነብሩን ጭራውን ይዞ ይገድለዋል። በሰራው ጀብድም ኩራት ስለተሰማው የነብሩን ጅራት ቆርጦ ኪሱ ከቶ አምጣ የተባለውን ውሃ ቀድቶ ወደ ኮንፊሽየስ ድንኳን ይመለሳል። ኮንፊሽየስንም እንዲ ሲል ይጠይቀዋል ፦

ትዙሉ አንድ ታላቅ ሰው ነብርን እንዴት አድርጎ ይገድለዋል አለው?

ኮንፊሽየስም፦ አንድ ታላቅ ሰው ነብር የሚገድለው ጭንቅላቱን ይዞ ነው አለው።

ትዙሉ፦ተራ ሰውስ?

ኮንፊሽየስ፦አንድ ተራ ሰው ነብር የሚገድለው ጆሮውን ይዞ ነው ።

ትዙሉ፦የማይረባ ከንቱ ሰውስ?

ኮንፊሽየስ፦የማይረባ ከንቱ ሰው ነብር የሚገድለው ጭራውን ይዞ ነው ።

ትዙሉ የኮንፊሽየስን ምላሽ በሰማ ጊዜ ከድንኳኑ ርቆ በመሄድ የነብሩን ጭራ ከኪሱ በማውጣት ወረወረው ፤ በንዴት ውስጥም ሆኖ መምህሬ ከወንዝ አጠገብ ነብር እንዳለ እያወቀ የላከኝ በነብር ተበልቼ እንድሞትና እንድገደል ስለሚፈልግ ነው አለና ኮንፊሽየስን ለመግደል በኪሱ ድንጋይ ይዞ ሄደ። ኮንፊሽየስ ጋር በደረሰም ጊዜ በድጋሚም እንዲ ሲል ጠየቀ፦ አንድ ታላቅ ሰው ሰው ሊገድል የሚችለው እንዴት ነው አለ ትዙሉ ?

ኮንፊሽየስም፦ታላቅ ሰው ሰው ሊገድል የሚችለው የሚፅፍበትን ብዕር ተጠቅሞ ነው አለ።

ትዙሉም፦ተራ ሰውስ ሰው ሊገድል የሚችለው እንዴት ነው?

ኮንፊሽየስም፦ተራ ሰው ሰው ሊገድል የሚችለው ምላሱን ተጠቅሞ ነው አለው።

ትዙሉ ፦የማይረባ ከንቱ ሰውስ እንዴት ነው ሰው ሊገድል የሚችለው አለ?

ኮንፊሽየስም ፦ የማይረባ ሰው ከሆነ ሰው ሊገድል የሚችለው ድንጋይን በመጠቀም ነው አለ።

ትዙሉ የኮንፊሽየስን መልስ በሰማ ጊዜ አሁንም እንደ ቀድሞው ከድንኳኑ ርቆ በመሄድ መምህሩን ሊገድልበት የነበረውን ድንጋይ ወረወረው።

ትዙሉም ከዚያ ግዜ ጀምሮ የኮንፊሽየስን የእውነት ታላቅ ሰው መሆን አምኖ ተቀበለ ፤ መምህሩን የሚያከብር ተማሪም ሆነ።

አንድ ታላቅ ሰው በነብር የተመሰለውን የሱን ሀሳብ ተቃራኒ የሆነ ጠላት በጭንቅላቱ ይዞ ወይም በሀሳቡ በልጦት ያሸንፈዋል። ተራ ሰው ግን በነብር የተመሰለውን የሱን ተቃራኒ የሆነ ጠላት በጆሮ ይዞ በጣፋጭ ቃላት ደልሎ ያሸንፈዋል። በማይረባ ከንቱ ሰው ደግሞ በነብር የተመሰለውን የሱ ተቃራኒ የሆነ ጠላት በጭራው በመያዝ ከጀርባው ሆኖ በሀሜትና ስሙን በማጥፋት ያሸንፈዋል ።

በሀሳብ ለማሸነፍ እንሞክር

ለቻናሉ አዲስ የሆናቹ Join በማድረግ ተቀላቀሉ

@yemaledabisrat
@yemaledabisrat
@yemaledabisrat
812 views18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 07:51:27 ጠብታ

እውነተኛ ፍቅር

አንድ ሰው ቆንጆ ልጃገረድ አገባ። እሱም በጣም ይወዳት ነበር፡፡ አንድ ቀን የቆዳ በሽታ ያዛት፡፡ ቀስ እያለች ውበቷን ማጣት ጀመረች፣ ያሰጨንቃትም ጀመር፡፡

አንድ ቀን ባልዋ ለጉብኝት ራቅ ወዳለ ስፍራ ሄደ፡፡ በሚመለስበት ጊዜ አደጋ አጋጠመውና ማየት አቃተው፡፡ ሆኖም የጋብቻ ሕይወታቸው እንደተለመደው ቀጠለ፡፡ ቀናት እያለፉ ውበቷ ደረጃ በደረጃ እየባሰ፣ ሙሉ ወበቷን አጣች፡፡ ዓይነ ስውር ባል ይህንን አያውቅም እናም በትዳር ሕይወታቸው ውስጥ ምንም ልዩነት አልነበረም፡፡ እሷም እሱን መውደዷን ቀጠለች እሱም በጣም ይወዳት ነበር፡፡

አንድ ቀን በድንገት ሞተች፡፡ ድንገት መሞቷ ታላቅ ኀዘን አመጣበት፣ ኀዘኑም ሲበረታበት ከዚያች ከተማ ለመልቀቅ ፈለገ፡፡ በአካባቢው ይኖሩ የነበሩ ሰዎች “አሁን እንዴት ብቻውን መሄድ ይችላል? ሚስቱ ነበር የምትረዳው፡፡” ብለው ይወያዩ ነበር፡፡ ሰውየውም “አይነስውር አይደለሁም ብሎ መለሰ፡፡ ይህን ያህል ጊዜ የማላይ መስዬ ነበር የቆየሁት፣ ምክንያቱም የቆዳ በሽታ እንዳለባት አውቅ ስለነበር የሷን ስሜት እንዳይጎዳ ብዬ ነው፡፡ ውበቷ ሲጠፋ መጨነቅ ስለጀመረች ምንም እንዳልሆነ እንዲሰማት ነበር፡፡ ስለዚህ እንደማላይ ነገርኳት፡፡ እሷ ለኔ በጣም ጥሩ ሚስት ነበረች፡፡ እሷን ደስተኛ ማድረግ ብቻ ነበር የምፈልገው አላቸው!

አንዳንድ ጊዜ አይተን አውቀን እንዳላየን ልናልፋቸው የሚገቡ ጉዳዮችን ስናልፋቸው፤ በዙሪያችን ካሉ ሰዎችን ጋር ያለን መልካም ግንኙነት እንዲጠነክር ይረዳል፡፡

ለቻናሉ አዲስ የሆናቹ Join በማድረግ ተቀላቀሉ

@yemaledabisrat
@yemaledabisrat
@yemaledabisrat
761 viewsedited  04:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-15 20:32:59 ጠብታ

የሕይወት ትምህርት

አንድ ወጣት የዩንቨርሲቲ ተማሪ ከፕሮፌሰር መምህሩ ጋር መናፈሻ ውስጥ ቁጭ ብለው ያወራሉ፡፡ ፕሮፌሰሩ ከተማሪዎች ሁሉ ይህን ተማሪ በጣም ስለሚወደው እንደ ጓደኛው አድርጎ ነው የሚያየው፡፡ ፊትለፊታቸው ጫማውን አውልቆ የመናፈሻውን ፅዶችና ሳሮችን የሚያስተካክል ሰራተኛ አለ:: ተማሪው የጽዳት ሰራተኛውን እያየ ለፕሮፌሰሩ:- “ፕሮፍ ዛሬ አንተም እኔም ደብሮናል፤ ለምን ያኛውን ሰውዬ ‹ትሪክ› አንሰራውም? ያወለቀውን ጫማ እንደብቅበትና ጫማዎቹን ሲያጣቸው እንዴት እንደሚበረግግ እዛ ጋር ደበቅ ብለን እንመልከተው” ይለዋል። ፕሮፌሰሩም፡ “ወጣቱ ጓዴ ምንም እንኳ ቢደብረን ድሃዎችን እያሰቃየን እኛ መደሰት የለብንም፡፡ ባይሆን እኛ ገንዘብ አለን በገንዘባችን የበለጠ ደስታን ማግኘት እንችላለን፤ ሂድና ቀስ ብለህ ሰውዬው ሳያይህ ባወለቀው ጫማዎች ውስጥ ገንዘብ ከተህበት ና፤ ከዛም ተደብቀን የሚሆነውን እናያለን” አለው፡፡ ተማሪው ፕሮፌሰሩ እንዳለው ቀስ ብሎ የሰውዬው ጫማ ውስጥ በርካታ ገንዘብ ከቶበት መጣና ከእሱ ጋር ደበቅ ብለው የሰውዬውን ሁኔታ መከታተል ጀመሩ፡፡

ሰውዬው ፅዳቱን ጨርሶ ኮቱን ለበሰና ጫማውን ለማድረግ ሲታገል ይቆረቁረውና ጎንበስ ብሎ ጫማውን ሲያራግፈው ብሮችን ያገኛል፡፡ ደነገጠ!! ዙሪያውን ቢያይ ማንም የለም፤ ደግሞ ደጋግሞ ቀኝና ግራ ሲመለከት ማንም ሰው የለም፡፡ በአግራሞት አንገቱን እየነቀነቀ ገንዘቡን ኪሱ ውስጥ ከከተተው በኋላ ሁለተኛ እግሩ ጫማውን ለማድረግ ሲያነሳ በተመሳሳይ ገንዘብ ያገኛል፤ አሁንም አላመነም!! በጉልበቱ ተንበረከከ አንገቱንም ወደ ሰማይ ቀና አደርጎ ጮክ ብሎ...“ጌታዬ የሚስቴን መታመም አውቀህ ነው አይደል? ካንተ ሌላ ማንም እንደማይረዳት አውቀህ ነው አይደል? የልጆቼን ዳቦ ማጣት አይተህ ነው አይደል? ምስጋና ይግባህ ጌታዬ” አለ፡፡

ተማሪው የሰውዬውን ሁኔታ ሲመለከት ልቡን ነካው:: አይኑ እንባ አቀረረ፡፡ ፕሮፌሰሩም “ቅድም ካሰብከው ‹ትሪክ› ይልቅ አሁን የተሻለ ደስታ እንዳገኘህ አልጠራጠርም” አለው:: ተማሪው እንባውን እየጠረገ... “ፕሮፌሰር እስከዛሬ ካስተማርከኝ ሁሉ እንደዚህ ያለ ትምህርት አስተምረኸኝ አታውቅም፤ በህይወቴ የማልረሳውን ትምህርት ነው ያስተማርከኝ፤ ለካ እውነትም ከመቀበል ይልቅ መስጠት የተሻለ ነው” በማለት መለሰለት፡፡

በሕይወት ጉዟችን ከማን ጋር እንደምንገናኝ አናውቅም፡፡ በመንገዳችን ሁሉ ብዙ የሕይወት ዘመን ትምህርት የሚሰጡን ሁኔታዎች ሊያጋጥሙን ይችላሉ፡፡ የማንንም የሕይወት መንገድ በእርግጠኝነት ማወቅ አንችልም፡፡ ሰዎች ምን አይነት ሕይወት እያሳለፉ እንደሆነ በእርግጠኝነት ማወቅ አንችልም፡፡ ስለሆነም በአገኘንው አጋጣሚ ሁሉ የሰዎችን ቁስል እየነካካን ሰዎችን ከመጉዳት ይልቅ ቀርበን እንረዳቸው፡፡ ከዚያ ምን ማድረግ እንዳለብን እንወስናለን፡፡ በሰዎች ሕይወት ለመቀለድና ለመሳለቅ አንሞክር። ሰዎችን ለመፈረጅ አንቸኩል!!

ለቻናሉ አዲስ የሆናቹ Join በማድረግ ተቀላቀሉ

@yemaledabisrat
@yemaledabisrat
@yemaledabisrat
855 viewsedited  17:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-15 20:32:16
263 views17:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 22:03:20 ከፈላስፋዎች ጉያ

ያለምጥ መልካም ነገር አይወለድም

የሰው ልጅ ለአምላኩ ያለው ጥያቄ ብዙ ነው። አንደኛው ዛሬ ዝናቡን አዝንብልን ሲለው ሌላኛው ዛሬ መንገድ አስቤያለሁና አደራህን ያን ዝናብ ያዝልን ይለዋል። ታድያ አንድ ቀን አንድ ጎበዝ ገበሬ እግዚአብሔርን ሃሳቡን እንዲህ ሲል አማከረው ፦ "ይኸውልህ ጌታዬ እኔ እድሜዬን ሙሉ የግብርና ስራ የሰራሁ ብዙ ልምድ ያለኝ የታወቅኩ ጎበዝ ገበሬ ነኝ። ብዙ ጊዜ እንደዚህ አስባለሁ ፦ አምላካችን ስንዴ ከዘራን በኋላ በተገቢው ሰዓት ዝናብ ቢያዘንብልን ሃይለኛ ንፋስ ባይነፍስ እና የስንዴ ሰብላችንን በሐይል እየነቀነቀ ባይሰባብርብን ባያስቸግርብን ፤ አንዳንዴም ውርጭና ብርዱ ሰብላችንን ባያበላሽብን በአንድ አመት የምንሰበስበው ብቻ ለሚቀጥሉት አስር ዓመታት አለስጋት ያኖረን ነበር። ታድያ ደጉ ጌታ ሰብላችንን እስክንሰበስብ ሁሉን ነገር ምቹ ለምን አታደርግልንም " አለው

እግዚአብሔርም የገበሬውን ንግግር አዳምጦ "እሺ እንደፈለግህ ይሁን " አለው። አመቱን ሙሉ የተዘራው ስንዴ ዝናብ ሳያጣ ንፋስ ሳያስቸግር ሁሉ ነገር እንደተደላደለ ሰብሉ በምቾት አደገ። ገበሬው እንዳለው ስንዴው ረጃጅም እና በጣም ብዙ ሆኗል እርሻው ላይ የሚያጓጉና ለዓይን ያማረ ነው ። ገበሬውም ይኸው ያልኩት ደረሰ አለ ።

በመጨረሻ የመሰብሰብያው ጊዜ ደርሶ ገበሬው ሰብሉን መሰብሰብ ሲጀምር በተመለከተው ነገር ከፉኛ ደነገጠ። ስንዴው ምንም ዘር የለውም። ገበሬው ግራ ተጋባና እግዚአብሔርን ጠየቀ "እንዴት ሊሆን ቻለ ?" እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ "አንተ አኮ በጭራሽ ስለ ንፋስ ስለውርጭ ስለማዕበል አልጠየክም ፤ አንተ የጠየከው ምቾትን ብቻ ነው ፤ የትኛውንም ነገር ፍሬ እንዲያፈራ የሚያደርጉት ጠንክሮ ዘርን አንዲይዝ የሚያደርጉት ተግዳሮቶች ናቸው ። መከራ ነው ስሩን ጠንካራ የሚያደርገው መነቅነቅ ነው ግንዱን የሚያፀናው በምጥ ነው ያማረ ነገር ሀሉ የሚወለደው" አለው።

ኦሾ /OSHO/

ወርቅ ተፈላጊነትን ያገኘው በእሳት ተፈትሎ ነው። እናም ፈተና ህይወታችንን ያጠነክረዋል እንጂ አያላላውም ተስፋችንን ያገዝፈዋል እንጂ ህልማችንን አያጨናግፍም ስለዚህ በህይወታችን ውስጥ የሚገጥሙን ፈተናዎች ፍሬያማ ሊያደርጉን ነውና ትኩረታችንን ዓላማችን ላይ ማድረግ ያስፈልጋል።

@yemaledabisrat
@yemaledabisrat
@yemaledabisrat
879 views19:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ