Get Mystery Box with random crypto!

'እግዚአብሔር አንድ ያደረገውን ሰው ሊለየው አይችልም' ጋብቻን የሚፈቅድ፤ ትዳርን የሚባርክና | የማለዳ ብስራት

"እግዚአብሔር አንድ ያደረገውን ሰው ሊለየው አይችልም"

ጋብቻን የሚፈቅድ፤ ትዳርን የሚባርክና አብሮነትን የሚያፀና የነገሮች ሁሉ ባለቤት ቅዱስ እግዚአብሔር ነው። ጠቢበ ጠቢባን ንጉስ ሰሎሞንም "መልካም ሚስት የእግዚአብሔር ሥጦታ ናት " በማለት የገለፀውም ይኽን እውነት ለማስረዳት ነው!።

ሆኖም እግዚአብሔር ያጣመረውን ሰው ሊለየው አይችልምና በአንድ የገመዳቸው በቃሉ ያጣመራቸው በቅዱስ ቁርባኑ ያዋሐዳቸው ፈቃዱ ሆኖ በዛሬው እለት ሥርዓተ ተክሊልን የፈፀሙት መምህራችን ዲ/ን ሔኖክ ኃይሌና ወ/ሪት ሣምራዊት ደመቀ በጽኑ መሠረት ላይ የታነፀውን የሕይወታቸውን ሌላኛውን ምዕራፍ አሐዱ የሚሉበት፤ ወደ ከፍታው የሕይወት ዘመን የሚሸጋገሩበት፤ ሕይወትን በጣምራ ወደሚመሩበት፤ ሦስት ጉልቻ ወደሚያቆሙበት አዲስ የሕይወት ክፍል ገብተዋልና ሙሽራውና ሙሽሪት መልጋም ጋብቻ እንዲሆንላችሁ። ትዳራችሁ የሰመረ ፍሬአችሁም ያማረ ይሆንላችሁ ዘንድ መልካም ምኞት ተመኘን! እግዚአብሔር ቀሪው ዘመናችሁን የተባረከ ያድርግላችሁ።


@yemaledabisrat
@yemaledabisrat
@yemaledabisrat