Get Mystery Box with random crypto!

#በውስጥ_መስመር_ከተላኩ_ጥያቄዎች ሶላትን ወቅቱ እስኪወጣ ድረስ አውቆ ሳይሰግድ ያሳለፈ ቀዷ ( | ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

#በውስጥ_መስመር_ከተላኩ_ጥያቄዎች

ሶላትን ወቅቱ እስኪወጣ ድረስ አውቆ ሳይሰግድ ያሳለፈ ቀዷ (ድጋሜ መስገድ) አለበትን?

#መልስ

ዑለሞች ሶላትን ወቅቱ እስኪወጣ ድረስ አውቆ ሳይሰግድ ባሳለፈ ሰው ላይ ስለሚኖርበት ቀዷ ሁለት የተለያዩ ንግግሮችን ተናግረዋል።
#አንደኛው
አራቱም አኢማዎች ወቅቱ እስኪውጣ ድረስ አውቆ ሶላትን ያሳለፈ ሰው ቀዷ ማውጣት (ድጋሜ መስገድ) እንዳለበት ተስማምተዋል።
#ሁለተኛው
ኢብኑ ተይሚያ፣ ኢብኑ ባዝ፣ ኢብኑ ኡሰይሚን፣ ኢብኑ ረጅብና ሌሎች ኡለሞች ደግሞ አውቆ እስካሳለፈ ድረስ ወንጀለኛ ነው የሚሆነውንጂ ቀዷ (ድጋሜ መስገድ) ግዴታ እንደሌለበት ተናግረዋል።

@yeilmkazna

@yeilmkazna