#በውስጥ_መስመር_ከተላኩ_ጥያቄዎች ሶላትን ወቅቱ እስኪወጣ ድረስ አውቆ ሳይሰግድ ያሳለፈ ቀዷ (ድጋሜ መስገድ) አለበትን? #መልስ ዑለሞች ሶላትን ወቅቱ እስኪወጣ ድረስ አውቆ ሳይሰግድ ባሳለፈ ሰው ላይ ስለሚኖርበት ቀዷ ሁለት የተለያዩ ንግግሮችን ተናግረዋል። #አንደኛው አራቱም አኢማዎች ወቅቱ እስኪውጣ ድረስ አውቆ ሶላትን ያሳለፈ ሰው ቀዷ ማውጣት (ድጋሜ መስገድ) እንዳለበት ተስማምተዋል። #ሁለተኛው ኢብኑ ተይሚያ፣ ኢብኑ ባዝ፣ ኢብኑ ኡሰይሚን፣ ኢብኑ ረጅብና ሌሎች ኡለሞች ደግሞ አውቆ እስካሳለፈ ድረስ ወንጀለኛ ነው የሚሆነውንጂ ቀዷ (ድጋሜ መስገድ) ግዴታ እንደሌለበት ተናግረዋል። @Mohammedjud @yeilmkazna 1.3K viewsMohammed Jud, 15:48