Get Mystery Box with random crypto!

ኢጎ እና ደስታ ብዙውን ጊዜ ደስታ ሠዎች የሚላበሱት ሚና እየሆነ ነው። ከሚስቅልህ ፊት ጀርባ | የኛ ሳይኮሎጂ||🇪🇹

ኢጎ እና ደስታ

ብዙውን ጊዜ ደስታ ሠዎች የሚላበሱት ሚና እየሆነ ነው። ከሚስቅልህ ፊት ጀርባ ከፍተኛ ስቃይ አለ። የደስታ እጦት በፈገግተኛ ፊት እና በሚያምሩ ነጭ ጥርሶች ጀርባ ሲደበቅ ወይም ደስታ ማጣትህን ለራስህም ጭምር ሳትቀበል ስትቀር ድብርት ውድቀት ፣ጉስቁልና እና ግልፍተኝነት የተለመዱ ከስተቶች ይሆናሉ።

“ደህና ነኝ” የሚለው ኢጎ የሚላበሰው ሚና፣ "የተጎሳቆሉ መምሰል " የተለመደ በሆነባቸውና በማህበረሰቡም መደበኛ ከሆነባቸው ከሌሎች አገሮች ይልቅ በአሜሪካ ጎልቶ ይታያል። ምናልባት ግነት ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን በአንደኛው የኖርዲክ አገር መዲና ውስጥ መንገድ ላይ ለማታውቀው ሠው ፈገግ ካልክ፣ ሰከረሃል ተብለህ ልትታሰር እንደምትችል ሰምቻለሁ።

መከፋት በውስጥህ ካለ በመጀመሪያ መኖሩን ልትቀበል ይገባል። “ደስተኛ አይደለሁም” ግን አትበል። ደስታን ማጣት ከማንነትህ ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር የለም። ይልቁንም “መከፋት በውስጤ አለ” ብለህ ከዚያ ነገሩን ለመመርመር ሞክር። ምናልባት ያለህበት ሁኔታ፣ ለዚያ ምክንያት ሊሆን ይችላል።

ስለዚህ ሁኔታውን ለመቀየር ወይም ከሁኔታው ለመውጣት እርምጃ መውሰድ የማትችል ከሆነ ደግሞ ያለውን ነገር ተጋፍጠህ “ደህና፣ በዚህ ሰዓት ነገሩ እንዲህ ነው፤ ልቀበለው ይገባል ” በል። የደስታ እጦት ዋነኛ ምክንያቱ የተከሰተው ነገር ሳይሆን፣ ለሁኔታው ያለህ ሃሳብ ነው። ስለዚህም ሃሳብህን አስተውል። ሁልጊዜ ገለልተኛ እና እንደነበር ከሚሆነው ክስተት ሃሳብህን ለይተህ ተመልከት። ስለሁኔታው ሃሳቦች እየጨማመርክ ነገር ከማወሳሰብ፣ክስተቱ ወይም እውነታው ይሄ ሲሆን ለሁኔታው ያለኝ ሃሳብ ደግሞ ይሄ ነው፤ ብለህ በእውነታው ላይ አተኩር።

ለምሳሌ “አለቀልኝ” ካልክ አንተን የሚገድብና ተገቢ እርምጃ እንዳትወስድ የሚያደርግህ ታሪክ ነው። “በአካውንቴ የቀረኝ ሃምሳ ሳንቲም ብቻ ነው” ብትል ግን እውነታ ነው። እውነታውን መጋፈጥ ደግሞ ሁልግዜም ቢሆን ሃያል ያደርጋል። የምታስበው ነገር ስሜትህን ለማወክ ትልቅ ድርሻ እንዳለው ልብ ብለህ አስተውል። በሃሳብህና በታወከው ስሜትህ መሃል የሚኖረውን ቁርኝት ተመልከት። ሁልጊዜ ታድያ፣ ሃሳብህንና ስሜትህን ከመሆን ይልቅ ከባሻገራቸው ያለውን አስተውሎ ሁን።

ደስታ ለማግኘት አታፈላልገው፤ ካፈላለግከው አታገኘውም፤ ምክንያቱም ማፈላለግ በራሱ የደስታ ጸር ነው። ደስታን ለመጨበጥ አዳጋች ነው። ከደስታ እጦት ነፃ መውጣት ግን፣ አሁኑኑ ማሳካት የምትችለው ነገር ነው።

ይህ የሚሆነውም ለሚፈጠረው ሁሉ፣ ታሪክ ከማበጀት ይልቅ ነገሩን እራሱን በመጋፈጥ ነው። የደስታ እጦት ተፈጥሮአዊውን የደህንነት፤ የውስጣዊ ሰላምንና የእውነተኛ ደስታን ምንጭ ይጋርዳል።
ኤካህርት ቶሌ

ከንባብ ዳርቻ ለህይወት ጠአም!
#share and # join for more
@KenibabDaricha
@KenibabDaricha