Get Mystery Box with random crypto!

ወላጅነት ብዙ ጎልማሶች ህጻናትን ሲያዋሩ ሚና ይላበሳሉ። አስቂኝ ቃላትና ድምፆችን ይጠቀማሉ። | የኛ ሳይኮሎጂ||🇪🇹

ወላጅነት

ብዙ ጎልማሶች ህጻናትን ሲያዋሩ ሚና ይላበሳሉ። አስቂኝ ቃላትና ድምፆችን ይጠቀማሉ። ህፃኑን ቁልቁል እያዩ ያወሩታል። ህፃኑን እንደ ሰው አይመለከቱትም ለጊዜው የበለጠ ማወቅህና የበለጠ ግዙፍ መምሰልህ ህፃኑ ጋር እኩል ያልሆንክ አያደርግህም። ብዙ ጎልማሶች በህይወታቸው የሆነ ውቅት ላይ አለማቀፋዊ የሆነውን የወላጅነት ሚና ይቀላቀላሉ።

መሰረታዊ የሆነው ጥያቄ ታዲያ፣ የወላጅነት ተግባርን ከተግባሩ ጋር ራስህን አንድ ሳታደርግ ወይም ሚናን ሳትላበስ ለመወጣት ብቁ ነህ ወይ? ልጁ የሚያስፈልገውን ነገር ማሟላት፣ ልጁን ከአደጋ መጠበቅ እንዲሁም አልፎ አልፎ ማድረግ ያለበትንና የሌለበትን መምከር ለልጁ ልታደርግላቸው ከሚገቡ ነገሮች ውስጥ የሚጠበቁ ናቸው፡ ነገር ግን ወላጅነት ራሱ ማንነትህ ሲሆን የማንነት ስሜትህ በጥቅሉ ወይም በዋናነት ከዚሁ ተግባር የተቀዳ ከሆነ፣ ተግባሩ በራሱ ከተገቢው በላይ ይሆንና ሙሉ በሙሉ ይቆጣጠርሃል::

የወላጅነት ሚናን መጫወት ማንነታቸው አድርገው የያዙ እናቶች ወይም አባቶች፣ ምሉዕነታቸውን በልጃቸው በኩል ለማግኘት ይሞክራሉ። ኢጎ የጎዶሎነት ስሜቱን ለመሙላት ሲል ሌሎችን የመጠቀም ፍላጎቱን ወደ ልጆች ያነጣጥራል። ወላጆች የማያስቡትና የማይቆጣጠሩት ልጃቸውን የመዘወር ስሜት ቢገለጥና ሲናገር እንዲህ የሚል እንድምታ አለው፤ “እኔ ያላሳካሁትን እንድታሳካ እፈልጋለሁ፣ በሌሎች ዘንድ ሠው ሆነህ እንድትታይ እፈልጋለሁ፣ እኔም ባንተ በኩል የሚገባኝን ክብር አገኛለሁ፤ አታስቀይመኝ። ለአንተ ስል ብዙ መስዋዕትነት ከፍያለሁ። የምቆጣህም ሆነ የምቀየምህ ፀፀት እንዲሰማህና ወደ ራስህ ተመልሰህ ፍላጎቴን እንድትፈፅምልኝ ነው። የሚበጅህን አውቃለሁ”
ሲልም ይቀጥላል። “ለአንተ እንደሚበጅህ የማውቀውን ነገር እስከተገበርስ ድረስ እወድሃለሁ፤ እየወደድኩህም እኖራለሁ።”

ለነርሱ ከነበረህ የከረመ ልማድ እና ምላሽ ጀርባ ያለውን የእራስህን አላስፈላጊ ግምትና ፍላጎት ለማስተዋል ሞክር። “ቤተሰቦቼ የኔን ህይወት ሊቀበሉ ይገባል፣ ሊረዱኝና ማንነቴን ሊቀበሉ ይገባል።” የምርህን ነው?ለምንድን ነው የሚገባው? እውነታው ግን አያደርጉትም፤ ምክንያቱም አይችሉም። ገና እያበበ ያለው ማስተዋላቸው ይህን ለመረዳት የሚያበቃቸው አይደለም። ከሚናቸው ለመነጣጠል ገና ብቁ አይደሉም።

“አውቃለው ነገር ግን በእኔነቴ ካልተቀበሉኝና ካልተረዱኝ ደስተኛ መሆን አልችልም፤ ምቾትም አይሰጠኝም።” የምርህን ነው? እነሱ ተቀበሉህ አልተቀበሉህ በእውነተኛ ማንነትህ ላይ ምን ለውጥ ያመጣል? እነዚህ ሁሉ ያልመረመርካቸው ግምቶች፣ ትልቅ አሉታዊ ስሜትና የደስታ እጦት ያስከትሉብሃል።

ንቁ ሁን። “ዋጋ የለህም፣ አትረባም”ን የመሳሰሉት በአዕምሮህ ውስጥ የሚመላለሱ ሃሳቦች የእናትህ ወይም የአባትህ ድምፆች ናቸው። ወይም ደግሞ፣ ሌላ አይነት ግምቶች አልያም አዕምሮአዊ አቋሞች ናቸው። ማስተዋሉ ካለህ ጭንቅላትህ ውስጥ የሚመላለሰውን ድምፅ በትክክል ትረዳዋለህ፤ማለትም ያለፈውን ማመን ታቆማለህ። ያረጀ ሃሳብ ነው። ማስተዋሉ ካለህ በምታስበው በእያንዳንዱ ሃሳብ ማመን ታቆማለህ። ያረጀ ሃሳብ እንጂ ሌላ አይደለም። ማስተዋል ማለት አሁንን መኖር ማለት ነው። በውስጥህ ያለውንም የማታስተውለውን ሃሳብ የሚያከስመውም አሁንን መኖር ብቻ ነው።"

ከንባብ ዳርቻ ለህይወት ጠአም!!
#share and # join it
@KenibabDaricha
@KenibabDaricha