Get Mystery Box with random crypto!

​​━━━━━━━━━━━━━━━━ እናትነት እውነተኛ_ታሪክ | ❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

​​━━━━━━━━━━━━━━━━


እናትነት


እውነተኛ_ታሪክ

ገነት አራት ልጆች አሏት ሁሉም ወንዶች ናቸው የመጀመርያ ልጇ ቢንያም 24 አመቱ ነው ሁለተኛ ልጇ ሱራፌል 22 አመቱ ሦስተኛ ልጇ ሳሚ16 አመቱ የመጨረሻ ልጇ አሜን ግን ገና 3 አመቱ ነው። ገነት ና ባለቤቷ ኪሮስ የሚያስቀኑ ደስ የሚሉ ባል ና ሚስት ናቸው። ኑሮአቸውን የሚያስተዳድሩት አንድ ሬስቶራት ከፍተው እየተጋገዙ በመስራት ነው ። በሳምንቱ የመጀመርያ ቀን ጥዋት ቤታቸው ተንኳኳ ፖሊሶች ነበሩ ኪሮስን ይዘዋቸው ሔዱ ምክንያቱም እሳቸው ትግሬ ስለሆኑ ሰሞኑን በሚሰራው ወንጀል ፓሊሶች ጥርጣሬ ስላደረባቸው ነው። ገኒ ባለቤቷ ስለታሰረባት ብቻዋን ቤት በማስተደደር ተጠምዳለች ለልጆቿ ሚያስፈልጋቸውን ነገር ካሰናዳችላቸው በኋላ ባለቤቷን እስር ቤት ሔዳ ካየችው በኋላ ወደ ሬስቶራንቱ የሦስት አመት ልጇን አሜንን ይዛ ትሔዳለች አሜንም አጠገቧ መጫወችያ ሰታው በአይኗ እየተቆጣጠረችው ሲያለቅስ እያባበለችው ሲተኛ በጀርባዋ አዝላ ስትሰራ ቆይታ ማምሻዋን ወደ ማደርያዋ ትመለሳለች። በባለቤቷ አለመኖር ብትከፋም ብታዝንም ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትል ትሰራለች። ኪሮስ ከታሰረ ሦስት ቀን ሆኖታል ገኒ እደተለመደው ተነስታ ልጇን ይዛ ወደ ስራ ቦታ ሔዳ ለአሜን መጫወቻውን ሰታው በስራ ተጠምዳለች ይሔኔ ነበር አሜን ከ አይኗ የተሰወረው ገኒ ስራዋን ጨርሳ ቀና ስትል ልጇን ታጣዋለች ወዴት እንደሔደ ለማጣራት ተጣራች አሜን አሜን የት ነህ አሜን ግን መልስ የለም ደግማ ተጣራች አባ አባቴ የት ሔድክብኝ አሁንም መልስ የለም ትንሽ ዞር ዞር ብላ ስታጣው ምናልባት ከተስተናጋጅ ጋር ከሆነ ብላ ወደ ፊት ለፊት ሰው ላከች ግን የለም አሁንም ደግማ ተጣራች አሜን አባቴ ግን መልስ የለም። ገነት ደነገጠች ምናልባት ወደ ጓሮ ሔዶ ይሖን ሩጫ ወደ ጓሮ እየተጣራች ገሰገሰች። ጓሮ ቆሻሻውን ለማስመጠጥ ብለም የከፈቱት 5ሜ ያልተከደነ ጉድጓድ አለ ከ ዛሬ ነገ አስከድነዋለው እያሉ ረስተውታል ገነት ሮጣ ከደረሰች በኋላ ወደታች ለማየት ብትሞከርም ሩቅ ከመሆኑ የተነሳ ሊታያት አልቻለም ባትሪ አስመጥታ ስታይ ልጇ በጭንቅላቱ ተደፍቶ ታየዋለች በዕንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ይሉታል እንዲ ነው ። ገነት አልቻለችም ጮኸች ኸረ ልጄ ኡኡኡ ልጄን አድኑልኝ ምትይዘው ምትጨብጠው ጠፋት አብረዋት የነበሩ ሰራተኞች ተደናገጡ ሰፈሩ በጩኸት ተናጋ እናት ግን ደቅቃ መጠበቅ አልቻለችም ከመቅስፈት ዘላ ወደ ጉድጓዱ ገባች በሷ መግባትም እንደገና ሌላ ጩኸት ኡኡኡ ድረሱልን ።ገኒ እንደገባች በፍጥነት ልጇን ከተደፋበት አነሳችው ምታደርገውን አታቅም በደመ ነብስ ልጇን አቅፋዋለች በህይወት ነበር ግን ትንፋሹ ይቆራረጣል ልጄን ልጄን አድኑልኝ ብላ ጮኸች ደጋግማ ልጄን አድኑልኝ ትላለች ልጇ አሜን በትንፋሽ ማጠር ና ቆሻሻም በመጠጣቱ በጣም ደክሟል። አብረዋት ልጇን ሲያፋልጓት የነበሩ ሰራተኞች በናት ና ልጅ ቆሻሻ ጉድጓድ ውስጥ መግባት ቢደናገጡም በፍጥነት ተጨማሪ ሰው ጠርተው እንዲሁም ጩኸቹን የሰሙ ሰዎች ተሰብስበው አሶጧቸውና የህክምና አርዳታ እንዲያገኙ ወደ ሆስፒታል ወሰዷቸው። ገነት በወገቧ ና በእጇ ላይ ጉዳት ቢደርስባትም የሷ መጎዳት አልታያትም ለዶክተሮቹ በልቧ ደሞ ፈጣሪን ልጇን እዲያድኑላት ተማፅናቸዋለች እዳሳቧ ፈጣሪም አላሳፈራትም ልጇ ሰላም ሆኖላታ በእግዚአብሔር ቸርነት ልጇ ተርፎላታል አሁን ደስተኛ ናት ።
በአሁን ሰአት እግዚአብሔር ይመስገን አናትም ልጅም በመልካም ጤንነት ላይ ናቸው።
ምን አይነት መሰዋትነት ነው? ምን አይነት እናት ናት ነብስ እስከመስጠት ልጇን የምትወደው? ፈጣሪ ለናቶች የሰጣቸው ልብ ምን አይነት ነው? ይሔ የኔ ጥያቄ ነው። ድንቅ እናት የምትወደድ ለነብሷ ያልሳሳች እኔ መቼም አረሳትም ፈጣሪ አድሜሽን ያርዝመው።
ክብር ፣እድሜ ና ምስጋና ለእናቶች



━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን

አዘጋጅ፦ የፍቅር ክሊኒክ

➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢

Join us  @yefikrclinic