Get Mystery Box with random crypto!

                                    በጣም ተጠግተሽ ብታይው አንቺ እንዳ | ❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

      
          
              


   በጣም ተጠግተሽ ብታይው አንቺ እንዳለሽበት ታውቂያለሽ??
ታውቂያለሽ .. ትናንትና ማታ ከቤቴ ገባሁና እግዚአብሔር ስለሰጠኝ
መልካም ነገሮች ማሰብ ጀመርኩ። ጊዜ አልፈጀብኝም ወዲያው አንቺ
ትዝ አልሽኝና ፈገግ አልኩ...ፈገግ ፈገግ በረጅሙ
ፈገግግግግግግግ... .
ታውቂያለሽ አይደለ ከምንም ነገሮች በላይ የሚያስደስተኝ ጠዋት
ከእንቅልፌ ተነስቼ አንቺ የኔ እንደሆንሽ ማሰቡ። ኡፍፍፍፍፍ ታድየ
ለእያንዳንዱ ሂወት ወይም የህልውና ቅጠላ ቢያንስ አንድ ነገር
ምክንያት ይሆነዋል። ዝናብ እንዲዘንብ ደመና ይኖራል፣ አበባ
እንዲያብብ ዝናብ ያስፈልጋል፣ አንቺም ልክ እንደዚህ ነሽ። ለኔ መኖር
አንቺ እንደምትፈለጊ ታውቂያለሻ? .
እንዲሁ ትናንትና ማታ በሂወቴ ውስጥ ትልቅ ድርሻ ያላቸውን ሰዎች
ልዘረዝር አጀንዳ አወጣሁና በእርሳስ መጻፍ ጀመርኩ። አንቺ ላይ
ስደርስ ግን በእስኪብርቶ መጻፍ እንዳለብኝ ተሰማኝ ምክንያቱም አንቺ
መቼውንም አትቀየሪምና። ታውቂያለሽ አይደለ ምን ያህል
እንደምተማመንብሽ?
ሁልጊዜ ስምሽን ስጠራው እርበተበታለሁ። አንቺም አልሽ!? "ምን ሆነክ
ነው ግን ስሜን ስትጠራው ልብህ እንዲህ በሃይል የሚመታው?" እኔም
ይሄን አልኩ... ፍቅርሽ በልብ ትቦዎቼ ገብቶ እየሮጠ ነው። ታውቂያለሽ
እውነቴን መሆኑን?
ታውቂያለሽ አይደለ ምንግዜም እንደምወድሽ? ምንግዜም
እንደማፈቅርሽ? ምንግዜም የመጀመሪያየ ምርጫየ እንደሆንሽ?
ታውቂያለሽ አይደለ ልትወድቂ ባልሽብኝ ቁጥር እንደምደግፍሽ?
ብዙ ጊዜ እግዜር ለሰዎች የተለያየ ስጦታ ያዘንብባቸዋል። ግን
እግዜር ለምን ስጦታ በመስጠት ይደክማል። ለምን ልክ እንደ ፍቅሬ
ያለ አንድ ሆኖ እንደ ሺ የሚጠቅም ስጦታ ሰጥቶ አይገላገላቸውም!?
     ብይአስቤለሁ 
  ፍቅር ማለት መቀበልን ብቻ ሳይሆን
መስጠትንም ይፈልጋል
☞መፀሀፍ አብቤ እፎይ ባልኩኝ ሰአት
ምነው ዛፍ በሆንኩኝ እያልኩ እመኛለሁ

ወይ ፍሬ አፈራለሁ
ወይ ጥላ እሆናለሁ

☞ቢያንስ አንድት ወፍ በቀን ወዳኝ
ወይም በውል አምናኝ
ጎጆ ቤቷን ሰርታ ልጆቿን ጥላልኝ
ምግቧን ልትፈልግ ስትበር አያለሁ
በውል ተማምናብኝ
እንደምትመካ እተማመናለሁ
ያኔ በትክክል ለአደራ እበቃለሁ፡፡


✦━━━━━━━━

ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን

Join us

@yefikrclinic