Get Mystery Box with random crypto!

ቤተልሔም የመጨረሻ ክፍል በ ያድ ክፍል 18 ••••••••••••ወደ ውስጥ ደስ እያት | ❤️የፍቅር ክሊኒክ❤️

ቤተልሔም

የመጨረሻ ክፍል

በ ያድ

ክፍል 18
••••••••••••ወደ ውስጥ ደስ እያት ገባች ።
ናሆም ግን በተቃራኒው ህሊናውን አጥቶ ቤቱን እንኳን ፈርቶት ሆቴል ነበር ያደረው ..........

ከ 1 አመት ቦሀላ...

ህሊና 3ኛ አመቷን አጠናቃ ክረምቱንም አሳልፋ ዛሬ መልሳ ወደ ዩኒቨርሲቲ ልትሄድ ጥቂት  ደቂቃዎች ይቀሯት ነበር በነዛ ደቂቃዎች ቤቲን ቀጥራ አግኝታት አንድ አመት ሙሉ በልቧ የተቀመጠ መልስ ያላገኘውን ጥያቄ ጠየቀቻት
"አምና ስለናሆም ስጠይቅሽ ስለሱ በቀል እንደምታስቢ ነግረሽኝ ነበር አሁንም ለረፍት ስመጣ አላገኘሁትም የት እንደሆነም አልሰማሁም ቤቱም ባንኳኳ ማንም አይከፍትም የት እንዳለ ታውቂያለሽ? "
"አዎ"
"የት ነው?"
"እስርቤት"
"ምን? በምን ወንጀል?"
"ያኔ በቀል ያልኩሽ ያለምክንያት ሳይሆን የወንድሜ አስገዳይ እሱ ስለነበር ነው ያንን ያወኩት............................................እና የዛን ቀን ምሽት ቅውስ ብሎ ወጣልሽ ከዛ ቦሀላ ቤቴ ድርሽ ብሎ አያውቅም በየቀኑ ስለ ፊሊ እያስታወስኩ እያነሳሁ አሰቃየሁት እኔ እንደዛ በመሆኔ ተፀፅቶ ብቻ አይመስለኝም እጁን ለፖሊስ የሰጠው አስታውሳለሁ እውነቱን እንዳወኩ የነገርኩት ቀን የሆነውን መቼም አልረሳውም እሱ ቤት ሆነን.
"ሰርፕራይዝ " አልኩት ድንገት በዝምታችን መሀል
"ምን ተገኘ የኔ ፍቅር"አለኝ
"የወንድሜን ገዳይ አገኘሁት "
"ምን?" እየደነገጠ
"አዎ ምነው ደነገጥክ?"  እቅፋን ከትከሻዬ ላይ አስለቅቄ ተነስቼ ፊትለፊቱ ቆምኩ
"ኧረ አልደነገጥኩም"
"ምነው አንተ ነህ እንዳልልህ ፈራህ እንዴ?"
"ቤቲዬ ቀልዶችሽ እኮ...."
"አልቀለድኩም!" ጮህኩበት
" አልቀለድኩም አዎ ናሆም ሁሉንም እውነት ደርሼበታለሁ ፊሊ የስራ ባልደረባህ ነበር እናም በ አንድ ተራ ገንዘብ ያልታመነ ስለመሰለህ ብቻ አስገደልከው"
"አይደለም እኮ ቤቲ"
"እንዳትጨርስልኝ እሺ ቆይ ከኔ ደግሞ ምን ፈለክ እኔንም ልታስገድለኝ ነው? ... ግደለኝ!    ግደለኝ ይኸው ግደለኝ ከዚህ የተመቻቸ ጊዜ አታገኝም ! .... ግን ያ ሁሉ ለምን ? ለምን?" አቅፎኝ ሳለቅስ ለማባበል ሞከረ የዛን ሰአት ግን የምናገረውን አላውቅም ከልቤ የሚሰማኝን ሁሉ ነበር የምናገረው ...
"ልቀቀኝ ! አታስብ አልከስህም አላሳስርህም ሁለተኛ ግን አይንህን ማየት አልፈልግም አጠገቤ እንዳትደርስ አላውቅህም አታውቀኝም!" ብዬ እየጠራኝ ጥዬው ሄድኩ ከዛ ቀን ጀምሮ አጊንቼው አላውቅም ቤት ሁላ ሳይቀር መጥቶ አንኳኩቶ ነበር በወር ከምናምኑ እንደታሰረ ሰማሁ ሄጄ በደምብ ሳረጋግጥ በ ፊሊሞን እና በሌሎች ሁለት ሰዎች ግድያ ወንጀሉን መስራቱን አምኖ ፍርድ ቤት ቀጠሮው በቅርቡ እንደሆነ ሰማሁ ፍርድቤቱ ብያኔ ቀን ላይ በአካል ተገኘሁ እናም የእድሜልክ ፅኑ እስራት ሲፈረድበት በራሴ ጆሮ ሰማሁ እናም ናሆም እስር ቤት ነው"

"ይገርማል በፍፁም ናሆም እንደዚህ አይነት አውሬ አይመስለኝም ነበር ይገርማል ግን ከህግ ያመለጠውን ነገር ያውም በራስሽ መንገድ ማውጣትሽ ያውም ናሆምን ከሚያክል አደገኛ ሰው ላይ " ህሊና ወደ ጅማ የሚወስዳት ቅጥቅጥ መኪና ውስጥ ገብታ ከፊት አለው ወምበር ላይ ተቀምጣ ቤቲ ደግሞ ከስሯ ዝቅ ብላ ቆማ ነበር የሚያወሩት ሰው እየሞላ ነው
"አዎ ፍቅር ከ ጥላቻና ግብግብ የተሻለ ጉልበት እንዳለው አምናለሁ ለዛም ነው ናሆምን መበቀል የቻልኩት ፍቅር ደግሞ የማንም ሰው ድክመት ነው ማንንም ጥፋተኛ ከህግ በላይ ከሆነ ከህግ በላይ በሆኑ መቅጫ አንቀፅ በሌላቸው ህጎች መቅጣት ልምዴ ነው ደምን በደም የምንበቀልበት ዘመን አልፏል የኔ ቆንጆ እነዚህ  አለንጋቸው የሚያርፈው አካል ሳይሆን አእምሮ እና ልብ ላይ ነው "
"ልክ ነሽ ! ይገርማል..."
"እ ማማ ? ትሄጃለሽ ወይስ?" አላት ረዳቱ በሩን ይዞ ቤቲ በ እጇ ጨብጣ ከተሰናበተቻት ቦሀላ ወረደች "እፎይ አሁን የሰላም ህይወት መኖር እጀምራለሁ አለች በውስጧ በረጅሙ እየተነፈሰች" ህሊናን በመስታወቱ ላይ እጇን  እየተሰናበተቻት ... ህሊናም እጇን እያውለበለበችእያውለበለበች  ሳታስበው በተቆጠበ ድምፅ በሹክሹክታ ከራሷ ጋር ታወራለች መኪናው እየተንቀሳቀሰ ነው..
"በዚህ አለም ላይ  አንቀጽ ያልወጣላቸው ጉዳቶች ፍትሀቸው ምን ይሆን " የህሊና የመጨረሻ ቃል ነበር ! ..............


                       ተ ፈ ፀ መ



፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧ፍቅር ለዘላለም ይኑር!!!፧፧፧፧


2015 E.C
•••••••••••••••••••••|  |•••••••••••••••••••••

     ደራሲ = @yaddiii ON @yefikrclinic

━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን

አዘጋጅ፦ የፍቅር ክሊኒክ

➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢

Join us @yefikrclinic

♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⎙ㅤ     ⌲   
  ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ