Get Mystery Box with random crypto!

👑የፍቅር_ደብዳቤዎች 💏

የቴሌግራም ቻናል አርማ yefikir_debdabewoch — 👑የፍቅር_ደብዳቤዎች 💏 የ
የቴሌግራም ቻናል አርማ yefikir_debdabewoch — 👑የፍቅር_ደብዳቤዎች 💏
የሰርጥ አድራሻ: @yefikir_debdabewoch
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8.34K
የሰርጥ መግለጫ

FOR COMMENT
@ABIRIHANN

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-10 21:28:05 "ቃሌ ቃል ባይመስላት ስቀርባት ብትርቅም
ለወጉ ነው እንጂ ጠልታኝ እኮ አታውቅም
"
ብዬ ስነግራቸው ሰዎች ይስቃሉ
ይንከተከታሉ
በማላቀው ምክንያት
እስቲ ዞረህ እያት
ሲሉኝ አያታለው
መች መልስ አገኛለው
ምንድነው? እላለው
መልሰው ይስቃሉ
ይንከተከታሉ
"ስከተላት ብትሸሽ ስቀርባት ብትርቅም
ኮርታብኝ ነው እንጂ
ጠልታኝ እኮ አታውቅም "
የሚል ቃል ሲወጣኝ ሳቃቸው ይገናል
አሁን በእናና ሞት ይሄንን ማን ያምናል
እነሱ ያሳቃቸው
እኔ ያስተዋልኩትን መሆኑን ባላውቅም
ጥርሷ ይርገፍና
አብረን ባለን ጊዜ ስቃልኝ አታውቅም

*------------------*
3.5K viewsᴬᴮᴵᴺᴱᵀ, 18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 16:23:32 #ያሜናዳብ


#ክፍል_አስራ አምስት(የመጨረሻ ክፍል)


በዚህ መሀል ግን ያልጠበኩትን ነገር አየሁ ፌቨን ከጓደኛዋ ጋር ፊቴ ላይ ቁማለች
ደነገጥኩ እንዴት ሊሆን ቻለ አልኩ በቃ ደስታዬ ወደር አጣ የምወዳት ጓደኛዬ ፊቴ ላይ
ሳገኛት ሁሉም ነገር የተሳካልኝ መሰለኝ ዘልዬ ተጠመጠምኩባት በዚህ መሀል ጆን ት/ት
እንድማር አደረገኝ ሁሌም ጆንን ከአይኔ ተለይቶ እስካየው እጓጓለሁ አንድ ቀን በዚህ እንዳለ
ፌቨን ጋር ቁጭ ብለን እያወራን ሁሉንም ነገር ትነግረኝ ጀመር እኔ አፌን ከፍቼ ቀረሁ ጆን
ከወንድም ጋ የተጣላበት ምክንያት አባታቸው ሲሞት ሙሉ ውሩሱን ለጆን ብቻ ነበረ
ያወረሰው የጆን አባት በጣም ብዙ ግዜ ታሟል ተሰቃይቷል ሁሉም ሰለቸው ጆን ግን
ህይወቱ እስኪያልፍ ድረስ ከአጠገቡ አልተለየውም ነበር በዚህ ምክንያት ጆንን አስበልጦ
ሰለ ሚወደው ሁሉንም ሀብቱ በእሱስም አዞረለት ከዛን ቀን ጅምሮ የጆን ወንድም
ቂመኛ ሆነ ጆንን በሚፈልገው ነገር ሁሉ ጎዳሁ ስንት አመት የተማርበት የደከመበትን ፋይል
ሳይቀር አቃጠለበት ጆን ይሄንም ችሎ ዝም አለ ይሄ አልበቃ ብሎት ጆንን ለማስገደል
ለቅጥረኛ ነፈስ ገዳይ ብር ሰጣቸው የጆን አባት ሁሉንም ነገር ሲሰማ አስጠራው ያሜናዳብ
እና አንተ ለእኔ ልጆቼ ናቹ ግን ምግባራቹ ባህሪያቹ ለየቅል ነው አይኔን በመርፌ እየነካህብኝ
ነው እጆችህን ሰብስብ አለ በለዚያ መቼም ይቅር አልልህም አለው በዚህም የተነሳ ደነገጠ
አባቱ ጆንን ያሜናዳብ ብሎ ነው ሚጠራወ በእምነቱ በጣም ጠንካራ ነው ሁሌም ስለ ጆን
ሲጠየቅ የእሴይ ስር ያሜናዳብ ሰረገላ የዳዊት መሰንቆ የሰለሞን አክሊል የታጠረች ተክል የተዘጋጀ የውሀ ጉድጓድ አንቺ ነሽ እመቤቴ ይላል እና የ እኔ የምድር ያሜናዳብ እሱ ነው ይላል ልክ አባቱ እንደዚህ ባለው
ማታውን ነፍሰ ገደዮች ጆንን ደብድቦ ሊገሉት ሲሉ ደውሎ ካልነካቹት ተውት አላቸው እንደ
ደበደቡት ሲነግሩት ከአከባቢው ጥፉ አላቸው እነሱም እንደ ተባሉ አደረጉ መጨረሻ ለይ
ጆን በወደቀበት ሰው አይቶት ሆስፒታል አስገባው በጣም ስለ ተጎዳ ወደ ውጭ ሀገር ሂዶ
እንዲታከም ተነገራቸው በዚህ ግዜ ልዩ ደውላ አሜርካ ላለው ሀያታቸው ነገረችው ለረጅም
አመት አሜርካ ነበር ሚኖረው እንደዛ እንደ ሆነ ሲሰማ በጣም ነበር ያዘነው ወዲያው ወደ አሜርካ እንዲልኩት አደረገ ጆን ከዛን ቀን በኋላ አባቱ ሲሞት ብቻ ነው ወደ ኢተዮጲያ
የመጣ እሱንም አልቆየም አባቱ ለእሱ ያወረሰውን ሙል ሀብት በወንድሙ ስም አዞረለት
በሰአቱ የጆን ወንድም ማመን ነበር ያቃተው ያን ካደረገ በኋላ ሁለት እህቶቹን ወደ አሜርካ
ይዞ ወጣ በሰአቱ የወንድሙ ሁኔታ ምንም ስላል ተመቸው ያን ሁሉ አመት አሳልፎ ከአመታት በኋላ ወንድሙ ጋር
ሊታረቅ ወደ ባ/ዳር መጣ ወንድሙም ለብዙ አመት ጆን ለይ የፈፀመውን ነገር እያሰበ
ብቻውን ነበር ሲያለቅስ የኖረው ጆንን ለመጀመርያ ግዜ ሲያየው በጣም ደንግጧል ይቅር
በለኝ ብዬ መሄድ ያለብኝ እኔ እንጂ እሱ አደለም ብሎ በጣም አዝኖ ነበር በራሱ እናንተ
ቤት ዶርም ሊይዝበት የቻለው ደግሞ ከእናተ ቤት ዶርም ተከራይቶ የነበረው የጆን ጓደኛ
ነው ጀን ወደ ኢትዮጲያ ከመምጣቱ በፊት ስለ ወንድሙ እንዲያጣራለት ነግሮት ነበር
በሰአቱ እኔ አንቺ ኤልሲ እና ኪያ ወይም የጆን ወንድም አብረን ነበረ ምንጓዝ ያሰለሆነ
ወንድሙን ለማግኘት ባንቺ መጣ አለችኝ እኔ ደርቄ ቀረሁ ጆን ይሄን ሁሉ ነገር ማሳለፉ
በጣም ገረመኝ ምን አይነት ትዕግስት ነው አልኩኝ በጣም ደነቀኝ እኔም ሁሉ ነገሬን ለጆን
አሳልፌ ሰጠሁት ፍቅርን ከምገልፀው ባለይ አስተማረኝ
ዛሬ ያሁሉ አልፎ ጆን ጋር ልንጋባ ወራት ነው የቀረን ከእኔ በላይ ደስተኛ የለም
ህይወት እንደ ፈለጓት ሳይሆን የህይወታችን ደራሲ የሆነ ፈጣሪ ያሰበልንን ሲሰጠን ብቻ ነው ልባችን የሚያርፈው ማንም ሰው የሚመኘው ነገር
ይኖራል በዛ ነገር ላይ ተስፋ መቁረጥ የለባቹም እኔ አሜርካ መሄድ የምፈልገውን ያክል ማንም
ፈልጎ አያውቅም
ነገሮች እንደ ማይሆኑ ባውቅም ተስፋ ግን አልቆረጥኩም ይሄው ፈጣሪ መሻቴን አይቶ
አልከለከለኝም ሁሌም ተስፋ አትቁረጡ አመሰግናለሁ


ተፈፀመ
3.5K viewsᴬᴮᴵᴺᴱᵀ, 13:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 19:55:30 #ያሜናዳብ

#ክፍል_አስራ አራት

ልክ በሳምንቱ ጆን ወደ አ/አ ነይ አለኝ እናቴን ለመጀርመርያ ግዜ ስለያት ልቤ ተረበሸ ግን ህይወት መቼስ እንደ ፈለጉት አይኖር አ/አ ስገባ ጆን ተቀበለኝ ሳየው በቃ ነፍሴን ያገኘውት ያህል ነበር ደስ ያለኝ ውበቱ ለጉድ ነው በጣም አምሮበታል አቅፎ ሰላም አለኝና ሻንጣዬን መኪና ውስጥ ከተተልኝ መኪና ውስጥ እንደ ገባን ሹፌሩ ሰላም አለኝ ሳየው ከዚህ በፊት ከሀዋሳ ስንመጣ የተቀበለን ሹፌር ነው ሰላም አልኩት ካፒታል ሆቴል ነበር ክላስ የያዘው እኔ የገረመኝ እና ጥያቄ የፈጠረብኝ ነገር ጆንን እስካየሁት ድረስ ትላልቅ ሆቴል ነው ለማረፍም ለመመገብም የሚይዘው ታድያ እንዴት እኛ ቤት ዶርም ሊይዝ ቻለ ብዬ በተደጋጋሚ ራሴን እጠይቃለሁ በዚህ መሀል ከሁለት ቀን በኋላ ዛሬ በረራ ታደርጊያለሽ አንቺ ሲለኝ ደነዘዝኩ በጣም ግራ ተጋባሁ ወዴት ነው ብቻዬን የምሄድ አልኩት ወደ ምትፈልጊበት ነዋ አለኝ ጀን አትቀልድ አልኩኝ እየሳቀ ባክሽ አብረን ነው ምን ሄድ እንዴት ብቻሽን እለቅሻለሁ አለኝ ተመስገን አምላኬ አልኩኝ ሁሉም ነገር ከአቅሜ ባለይ ሁኖብኛል ጆን ያደርገልኝን ሳስብ ለመናገር አቅም ያንሰኛል በቃ ጆን ማለት ለእኔ ሁሉ ነገሬ ነው ማታ ሁለት ሰዓት ላይ ቦሌ ዓለምአቀፍ ኤርፖርት ሄድን ውስጤ ምን እንደ ሆነ ባላውቅ በፍረሀት ተንዘፍዝፏል ልክ ወደ ፍተሻ እስክን ደርስ ምንም የማውቀው ነገር የለም ፖስፖርቴን እና ቪዛዬን የያዘው ጆን ነው ልክ Backgroundu ላይ ሳየው ወደ አሜርካ መሆኑን አወኩ በድንጋጤ ውሀ ሆንኩ
ፍተሻው ላይ ፖስፖርቴን ሰጠኝ ጆን አልኩኝ ደንግጬ ትዙ አለኝ መልሶ እዛው ላይ ተጠመጠምኩበት ያቀን ለእኔ ከምንም በላይ ነበረ በልቤ ደስታዬን እንደበዛከው ፈጣሪ ደስታህን ያብዛልህ ጆን አልኩኝ ብቻ ሁሌም በሱ ደስተኛ ነኝ በዚህ መሀል ስንት ነገር አልፌ texas ገባሁ እድሜ ልኬን አልሜ ያልተሳካልኝን ጆን ህልሜን አሳካልኝ በቃ ሁሉም ነገር ብርቅ ሁኖብኛል ከምንም በላይ የገረመኝ ግን ጆን የሚኖርበት ቤት ነው አሜርካ ላይ እንደዚህ አይነት ቤት ውስጥ የሚኖር ልጅ ሳይቸግረው እንዴት እኛ ዘንድ ዶርም ሊይዝ ቻለ ብዬ በጣም ጥያቄ ፈጠረብኝ አሁን በዚህ ሰዓት ከእኔ በላይ ደስተኛ የለም በርግጥ አይደለም የሚፈልጉት ሰው ጋር በአንድ ቦታ መኖር ይቅርና ቀጣይ ህይወታችን የምንወደው ሰው ጋር እንደ ምናሳልፍ ስናውቅ ራሱ በተሰፋ
እንሞላለን በዚህ መሀል ጆን አዲስ ሲምካርድ ና ሞባይል ሰጠኝ አመስግኜ ተቀበልኩ ቶሎ የደወልኩ ለእናቴ ነበረ ድመጿን ስሰማ በጣም ደስ አለኝ ዛሬ ብሞት አይቆጨኝም አለችኝ ሁሌም ምኞቴ አንቺ የምትፈልጊውን ነገር ላደርግልሽ ነው ልጄ ዛሬ ይሄው የፈጣሪ ፍቃድ ሆነና ተሰካልሽ አለችኝ እናቴ ምንም ከሀገር እንድወጣ ከአይኗ እንዳልርቅ ብትፈልግም ፍላጎቴ ስለ ሆነ ብቻ መቃወም አልፈለገችኝም እናቴን አውርቼ እንደ ጨረስኩ አክስቴ ስልኩን ተቀብላ እንዳትዘጊው አለችኝ ቆይኝ እዳሪ ልውጣ ብላ እንደ ልማዷ እዳሪ ወጣች ማንም ይሁን ሰው ጋር ተቀምጣ ስልክ ማውራት አትወድም አክስቴ ጋረም ብዙ አዋራን በደቂቃዋች ውስጥ የሰጠችኝ ምክር ለነገሮች ቦታ እንድሰጥ አድርጎኛል በዚህ መሀል የጆን አህት ልዩ ስታየኝ ጨወች በጣም ነበረ ደስ ያላት አቅፋ አለቀኝ አለች ወይኔ አምላኬ አውቀህ መስሎኝ ነበር እኮ አለችው ጆንን በዚህ መሀል ግን ያልጠበኩትን ነገር…

ይቀጥላል
3.1K viewsᴬᴮᴵᴺᴱᵀ, 16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 21:16:56 #ያሜናዳብ

#ክፍል_አስራ ሶስት

ወደ ሰፈር እየሄድን እያለ የጀን ወንድም ክላክስ አደረገ ጆን ወንድሙን ሲያየው ፈገግ አለ ከመኪና ወጦ መጣና ጆን እግር ስር ተደፋ እኔ ደነገጥኩ ጆን ምንም አልመሰለውም ከፈ አደረገውና ተቃቀፉ ወንድሙ እንባውን እንዴት ይቻለው ግራ ብጋባም ምንም አላልኩም እቤት ድረስ አደረሰን ጆን በኋላ እደውልልሀለው ሲለው እኔ ራሴ እመጣለው ብሎት ተለያየን በጣም አሞኝ ስለነበር ተኛሁ ልክ ከዛን ቀን በኋላ ለሁለት ሳምንት ያህል እንደ ቱሪስት ጆን ጋር ዞርን ያልሄድንበት ሀገር የለም እናቴ የማትመክረኝ ምክር የለም ነገሩ ግራ ገብቶኛል በቃ ህይወቴን ከአሁን በኋላ እንዴት መምራት እንዳለብኝ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ከአሁን በኋላ ህፃንነት እንደሌለ ህይወትን ራሴ መኖር እንደምችል አስቀምጣ ነገረችኝ ምን እንደ ሆነ ባላውቅም ውስጤ ፍረሀት ፍረሀት
ብሎኛል እናቴ በህይወቷ አቋም የሌለው አንዱን ሚጥል እንዱን ሚያነሳ ሰው አትወድም እኔ ደግሞ የእሳት ልጅ አመድ እንደሚባለው ሁሉም ነገር አይናዋጅ ይሆንብኛል ቢሆንም ግን እስከዛሬ ከኖርኩት በላይ ጆንን ካገኘው በኋላ ውስጤ ላይ ያለው ደስታ ልዩ ነው በዚህ
መሀል ጆን ወደ አ/አ ልሄድ ነው አለኝ ደነገጥኩ አሁንም ሊጠፋብኝ ነው አልኩ እንባዬ መጣ ይሄውልሽ ትዙ በአንድ ሳምንት ውስጥ ጓደኞችሽን ተሰናበቺ ሲለኝ በጣም ደነገጥኩ ምይዘውን አጣሁ ወዴት ለመሄድ አልኩት እሱን ስትደርሺ ታውቂዋለሽ አለኝ በቃ ደስታዬን አልቻልኩም ሁሉም ነገር ከአቅሜ በላይ ሆነ እሱም ወደ አ/አ ሊሄድ ብሎ ቦርሳውን ሲያወጣው እንደ ማይመለስ አወኩ አንዳለ ቤት ውስጥ ያለውን ዕቃ እናቴን እንደ ነገርኩሽ አድርጊው አላት እሷም እሺ አለችው ልክ ሊወጣ ሲል አክስቴ ቡና ደርሷል ጆን ግባ አላችው ቦርሳውን በረንዳ ላይ አድርጎ ገባ እኔ እስካሁን ምንም አልተናገርኩትም ግራ
ተገብቻለሁ ወደ ቤት ሲገባ ተከትዬው ገባሁ ከምንም በላይ ሀሳብ የሆነኝ አይኑን ሳላየው እንዴት አድርጌ ሳምንት እቆያለሁ የሚለው ነገር ነው የያዘኝ ጆን ልክ አንድ ቡና እንደ ጠጣ ሹፌሩ ደርሻለሁ አፍጥነው ሰዓት እያለፈ ነው አለው ቶሎ ወጣ እኔም ልሸኝህ ብዬ
አብሬው ወጣሁ በቃ እንባዬ እየተናነቀኝ ነው ትዙ አለቃስላው ብትይ የእውነት
አቀይምሻለሁ አለኝ እኔም እኮ ትናፍቂኛለሽ አንቺ ብቻ አደለሽም ለእኔ ምታስቢው እኔም እኔም እነዳንቺው ለስሜትሽ እጨነቃለሁ አለኝ በቃ ይሄን ከእሱ በመስማቴ ብቻ ደስ አለኝ
በዚህ መሀል ጆን ከሄደ በኋላ ማስተካከል ያለብኝን ሁሉ አስተካከልኩ ጆን በየደቂቃው ይናፍቀኛል ሚገርመው እንደዛ በቀን ስንቴ እየደወልኩ አስለቸውት ይሆን እላለሁ ግን ከእኔ ብሶ አረፈ እኔ ጋር ያለ እስኪመስለኝ ድረስ ሙሉ ጓደኛቼን ተሰናበትኳቸው ብዙም ወከባ ስለ ማልወድ ባሉበት ሂጄ አዲስ አበባ ለተወሰነ ግዜ እቆያለሁ አልኳቸው ለኤልሲ ብቻ ነው እውነቱን የነገርኳት የእውነት ለመናገር ወዴት እንደ ምሄድ አላውቅም ልክ በሳምንቱ ጆን ወደ አ/አ ነይ አለኝ እናቴን ለመጀርመርያ ግዜ ስለያት ልቤ ተረበሸ ግን..........

ይቀጥላል
2.7K viewsᴬᴮᴵᴺᴱᵀ, 18:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 20:47:10 #ያሜናዳብ

#ክፍል_አስራ ሁለት



እሺ እመዬ ትምጣ እና ልንገራት አልኩት ሳቅ አለና እሺ አለ እናቴ ከደጀ ሰላም እንደመጣች ስነግራት አዋ ነግሮኛል ሂዱ አለች ምን ግዜ ነገረሽ አልኳት ማታ ላይ ነግሮኝ ነበር ልነግርሽ ነበር ተኝተሻል አለችኝ እናቴ ጆን ላይ የጣለችው እምነት
ይሄ ነው ለማለት ይቸግረኛል ከምንም በላይ ታምነዋለች ስድስት ሰዓት እንደ ሆነ ባህር ዳር ኤርፖርት ደረሰን ሰላሳ ደቂቃ አላቹ ሲባል ቁጭ አልን አንድ ያልተመለሰልኝ ነገር ቢኖር በቃ የሆነ ነገር ለማድረግ ደቂቃ አይፈጅ በትም ምንም ነገር ሲያደርግ ለማንም አይናገርም
አድርጎት ወይም ፍፅሞት ነው ማገኘው ማያደርገውን ይቅርና የሚያደርገውን እንኳ መናገር አይፈልግም ከደቂቃዋች በኋላ በረራ አደረግን ልክ ከአርባ ዲቂቃ በኋላ አ/አ ደረስን ምሳ በልተን ወደ ዘጠኝ ሰአት አከባቢ ላይ ወደ አሜርካ ኢንባሲ ሄድነ በቃ ኢንባሲውን ሳየው ትዝ አለኝ ለአመታት አሜርካ ለመሄድ ስል ከጣልያን እስከ ሱዳን ድረስ የሄድኩት ስንት ብሬን
የጨፈጨፍኩበት ፊቴ ላይ ድቅን አለ ግን ጆን ለምን መጣን አልኩት ሳቀብኝ ምትፈርሚው ነገር አለ አለኝ ምን አልኩ በቃ ውስጤ ይሄ ነው ከሚባለው በላይ ደንግጫለሁ ልክ እንደ ገባን ፎቶ አነሱኝ በተላያየ ቦታ አስፈረሙኝ ሜድካል ተብሎ ወደ ምርመራ ክፍል ሄድኩ ብቻ ምን ያላረጉኝ ነገር አለ ለምን እንደ ሆነ አላውቅም ብቻ ጆን ከአጠገቤ ስላል ተለየ ምንም ፍረሀት አልተሰማኝም ውስጤ ከመደንገጥ በስተቀር ልክ እንደ ጨረስን ቁጭ ብለን እያለ አንዱ መጣና ጆን በቃ ሂዱ ያለውን ነገር አሳውቅሀለው ሲለው እሺ ብሎ ወጣን አ/አ ውስጥ እየዞርን አመሸን ጆን ጋር አንድ ክፍል ውስጥ እንደ ምናድር ሳስበው ደስ አለኝ

ሀርሞኒ ሆቴል ሩም ይዘናል አለኝ እህ መቼ ስለው ኦንላይን ኢንተርኔት ላይ ነዋ አለ እየሳቀ አንቺ ከዚህ ነገር ነፃ ነሻ አለ እያፌዘብኝ እንኳን ሆንኩ አልኩት ሰአቱ እየመሸ ሲሄድ ወደ ሆቴሉ ሄድነ ደብል አልጋ ነበር የያዘው እራት ሰዓት እስኪ ደርስ ሻወር ወስደኩ ምናምን ልክ ራታችንን በልተን እንደ ጨርሰን ሩም ገባን
ትንሽ ሚጠጣ ነገር ቀምሼ ስለ ነበረ ወሰወሰኝ ጆንን የቅድሙ መጠጥ አማረኛ አልኩት አረ አንቺ ልጅ እያለ ሩም ድረስ አስመጣ በቃ ማታ ምን እንደ ተፈጠረ አላውቅም ጥዋት ስነሳ ከጆን ደረት ላይ ተለጥፌ ተኝቻለሁ በቃ በድንጋጤ ውሀ ሆንኩ በቃ ምን እንደ ተከሰተ ማወቅ አልቻልኩም ራሴን በጣም አሞኛል የሞት ሞቴን ከደረቱ ላይ እንደምንም ብዬ ተነሳሁ በጣም ራሴን ይዞኛል እንደ ምንም ብዬ ቀና ለማለት ሞከርኩ ልብሴ አልወለቀም የጆን ልብስም አልወለቀም ታድያ እንዴት እሱ ጋር ልተኛ ቻልኩ ብዬ በጣም ነበር ግራ የገባኝ ነገሩ ግርምት ፈጥሮብኛል ማታ በጣም የጠጣሁ መሰለኝ ራሴን በጣም አሞኛል ስንቀሳቀስ ጆን ነቃ አንቺ ሰከራም አለኝ ምንድ ነው የሆንኩት አልኩኝ ለካስ እንደዚህ ሰከራም ነሽ አለኝ አፈርኩኝ እየሳቀብኝ ተነስቶ ሻወር ገባ በጣም ስላመመኝ ሻወር መግባት አልፈለኩም እስኪ መጣ ልብሴን ቀያየርኩ ልክ ሲመጣ አይኔ ደረቱ ላይ አረፈ ይሄ ደረት ላይ ተኝቼ ነዋ የሆንኩትን ሁሉ የረሳው አልኩ በልቤ እረ አይንሽን ንቀይ አለኝ ባክህ ዝምበል የግልህ አደረከውሳ አልኩት ሳቄን አያፈንኩት በለው ማነው የልብ ልብ የሰጠሽ አለኝ እእ አንድ ጢባራም አለ አንድቀን አስተዋውቅሀለው አልኩት እየሳቀብኝ ከሆቴሉ አቅፎኝ ወጣ ልክ ባ/ዳር ገብተን ወደ ሰፈር እየሄድን እያለ የጀን
ወንድም ክላክስ አደረገ ጆን ወንድሙን ሲያየው ፈገግ አለ ከመኪና ወጦ መጣና ጆን እግር ስር ተደፋ...........

ይቀጥላል
2.7K viewsᴬᴮᴵᴺᴱᵀ, 17:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 21:56:11 #ያሜናዳብ

#ክፍል_አስራ አንድ

ስልኬ ሚሴጅ ሲገባልኝ አይቼ ከወንበሩ ላይ አነሳሁት እረ አትናደጂ ትዙሻ ይላል ጆን ነው ቀና ብዬ ሳያው ጠቀሰኝ በቅፅበት ያሁሉ ንዴቴ ጠፋ ሰአቱ እየመሸ ስሄድ ጆን እኛ እንሂድ ሲል እንዴ ፍቅር ጥለክን ልትሄድ አለች ቅብጠቷ ቅጥ
የለውም ምን ትመስላለች ሞልቃቃ አልኩ በልቤ ልዩ በቃ ሂዱ ስትል ልንሄድ ስንነሳ ቆንጂዬ አደራ ፍቅርን አለችኝ አታስቢ አልኩ ጥርሴ ነክሼ ግን ለጆን ጓደኞቹ ይሁኑ ምኑ ይሁኑ ማውቀው ነገር የለኝም እሱም አልነገረኝም ግን በቃ ጆንን ከሆቴሉ ይዤው ስወጣ በቃ ከነጣቂዋች እጅ አውጥቼው ጉያዬ ውስጥ ያስገባሁ
መሰለኝ ጆን መንገድ ላይ ትንሽ ለው ላድርገሽ ብሎኝ ወደ ባህል ምሽት ቤት ጎራ አልን የተወሰነ ተጫወትን እየመሸ ስለ ሆነ ብዙም አልቆየንም ልክ እቤት እንደ ደረስን አክስቴ እና እናቴ በረንዳ ላይ ቁጭ ብሏል እናቴ ስታየን ፈገግ አለች በቃ እኔ ጆን ጋር ስላለኝ ቀረቤታ ደስተኛ ናት አክስቴ ጠቀሰችኝ ፈገግ አልኩ
የእውነት ለመናገር በረንዳ ላይ ባይቀመጡ ደስተኛ ነበርኩ እንደ ሚስመኝ እርግጠኛ ነበርኩ ብቻ አመለጠኝ አልኩ በልቤ ግን ያቺ የልዩ ጓደኛ ፍቅር ብላ ስለጠራችው ውስጤን ከነከነኝ በዚህ እንዳለ ሰፈር ላይ በጆን ታማሁኝ መቼም ቢሆን በሚወዱት ሰው መታማትን የመሰለ ነገር የለም እሁድ ቀን ላይ ወደ ጢስ አባይ ጆን ጋር ልንዝናና ሄድነ ብዙ አዋራን በቃ ሰላሳለፋቸው ፈተናዋች ሲነግረኝ እንባዬን እንዴት ልቻለው እሱ ያሳለፈውን ህይወት እኔ
ለመስማት ከበደኝ ወንድሙ ጋር እንደ ታረቀ ሲነግረኝ ግን ከምንም በላይ ደስ አለኝ ወደ ኢትዮጲያ የመጣበትን ጉዳይ እንደጨረሰ ሲነግረኝ ልቤ ተረበሸ ፍረሀት ፍረሀት አለኝ ባይነግረኝ አልኩ ግን ትዙ ባለፎው ልዩ ጋር ሳስተዋውቅሽ ጥሩ ስሜት እንዳልተሰማሽ አውቂያለሁ ይቅርታ ግን አንድ ያልነገርኩሽ ነገር አለ ሲለኝ ተቀምጬ እንኳ ጉልበት አጣሁ
በቃ ደንዝዣለሁ ምን መሰለሽ ትዙ ልዩ እኮ ለእኔ እህቴ እኮናት ሲለኝ በቃ ደስታዬ ወደር አጣ እሺ ቲቲ ያልካትስ ስለው እሷም እህቴ ናት ልዩ ጋር የእንድ አባት የአንድ እናት ነን ቲቲ ጋር በአባት ብቻ ነው ምንገናኘው ሲለኝ ተመስገን አልኩ በልቤ በቃ የዛን ቀን ደስታዬ ወደር የለውም ከሳምንት በኋላ ፌቨን ከሀዋሳ መጣ አየኋት በጣም ነበር ደስ ያለኝ በቃ እቤት አብረን ሂደን ብዙ አዋራን ጆን ሚኪ ጋር እንዳስታረቃቸው ነገረችኝ ከምንም በላይ ደስ አለኝ እስቲ ንገሪኝ ጆን ፍቅረኛሽ ነው አለችኝ ደነገጥኩ ምን እንደ ነካኝ ባላውቅም እረ አይደለም ኖርማል ጓደኛዬ ነው አልኳት ነው እንዴ ፍቅረኛሽ መስሎኝ ነው አለች በራሴ በጣም ተናደድኩ በጆን አፍሬ ወይስ በራሴ አፍሬ ነው አይደለም
ብዬ የተናገርኩት እያልኩ ራሴን ወቀስኩ እሁድ ቀን ከኤልሲ ጋር ከጓደኞቻችን ጋር ውለን ወደ ቤት እየተመለስን እያለ ጆን ደወለልኝ ሳነሳው ወደ ጎን ተመልከቺ አለኝ ዞር ስል ወንድሙ ጋር ካፌ ላይ ቁጭ
ብሏል ሻይ ቡና ብሎ ጠራን ቅድሙንም ናፍቆኝ ነበር ሄድን የእውነት ለመናገር የእናት ሆድ ዝንጉርጉር ሚባለው በጆንና በወንድሙ ላይ በሚገባ ሰርቷል እንኳን ወንድማማች ሊመስሉ ሆድና ጀርባ እንኳ አይሆኑም በፊትም የጆንን ወንድም ፌቨን ጋር እያሉ ድንገት ሳየው ማነው ግን ውቃቤውን የገፈፈው እላለሁ ቢነኩት እጅ ላይ ሰበብ ሚሆን ነው ሚመስለው ጀን
ትክሻዬን ነካ ሲያደርገኝ ከሀሳቤ አነቃኝ በሁለተኛው ቀን ጥዋት ላይ ጆን አ/አ ደረሰን እንምጣ አለኝ ትንሽ ልቤ ደነገጠ እሺ እመዬ ትምጣ እና ልንገራት አልኩት ሳቅ አለና እሺ አለ እናቴ ከደጀ ሰላም እንደመጣች ስነግራት......

ይቀጥላል
2.5K viewsᴬᴮᴵᴺᴱᵀ, 18:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 21:14:09 #ያሜናዳብ

#ክፍል_አስር

ምን ማለት ፈልጎ ነው እንዴ እኔስ አልኩ
በልቤ ማወራው ጠፋኝ ምነው ደነገጥሽ አለኝ ልክ ከምሽቱ ሁለት ሰአት ላይ ከቀኑ በተለየ በሩ ተንኳኳ ዝም አልኩ አሁንም ተንኳኳ ዝም አልኩ እረ ትዙ ምንሼ ነው አለኝ የጆን ድምፅ ነው በመብረቅ የተመታሁ መሰለኝ በቃ ለመናገርም ከበደኝ
በልቤ ማወራው ጠፋኝ ምነው ደነገጥሽ አለኝ ራሴን አለመሳቴም እኔ ሁኜ ስለው ስቆ ስቀልድሽ ነው ብሎ ግንባሬን ሳመኝና ከተቀመጥኩበት አስነሳኝና ወደ ቤት
አስገባኝ እኔም ልቤ ቅር እያለኝ ገባሁ ግን በቃ ማታውን አልተኛሁም ሚስቴ ያለው ነገር ሲከነክነኝ አደረ ወደ ጥዋት አከባቢ እንቅልፍ ጣለኝ ወደ አምስት ሰአት ላይ ተነሳሁ ልክ እንደ ነቃው ወደ ጆን ክላስ ነበር የሄድኩ ግን ዝግ ነው ቅር አለኝ አክስቴ ካኋላ እያየችኝ ነበር ሳቀችብኝ ፎንቃ ይሉሻል ይሄን ነው አለች እየሳቀችብኝ እኔም ሳቄ አመለጠኝ ቀን ላይ ደውዬለት ትንሽ ስራ ይዤ ነው እንደ ጨረስኩ እመጣለሁ አለኝ እኔም ቀኑን ሙሉ ስጠብቀው ዋልኩ ማታ ላይ እቤት እራት አብረን በላን ልክ በዚህ መሀል ከሳምንት በኋላ ነገ አንድ ማስተዋውቅሽ ሰው አለ አለኝ ደስ ይለኛል አልኩ ነገውን ልክ ወደ ማታ አከባቢ ደውሎ ግራንድ ሚባል ሆቴል ጠራኝ እኔም ለባብሼ ሄድኩ ሆቴሉ እንደ ደረስኩ እንግዳ ማረፍያ ክፍል ውስጥ ሁኜ ደወልኩለት እንደ መጣ ይዞኝ ወደ ላይ ወጣ ቦታው በጣም የሚያምር ግራፊክስ አለው የሆነች ልጅ ጀርባዋን ሰጣ ተቀምጣለች ልዩ አላት ወዬ ብላ ዞር አለች እረ በፈጣሪ አልኩ በልቤ ደነገጥኩ በጣም ቆንጆ ልጅ ናት ይሄ ነገር እንዴት ነው አልኩ በልቤ
የዘር ነው ወይስ ተፈላልገው ነው የተገናኙ አልኩ ትዙ ያልኩሸ እሷ ነው ሲላት የምርህን ነው ብላ ተነስታ ሳመችኝ እኔም ውስጤ ትንሽ ደስ አለኝ ሁሌም የማያውቁን ሰዋች ስለ እኛ በተነገራቸው መጠን ነው በህሊናቸው ሊስሉን የሚችሉት ጫዋታዋ ደስ ይላል ልክ እንደ
ስሟ ልጅቱም ልዩ ናት ከሰአታት በኋላ እራት በልተን ጆን ወደ መታጠብያ ክፍል ሲሄድ እንድ ጓደኛዋ መጣች አንቺ እንቅልፋም ተነሳሽ አለቻት ሰላም ብላኝ ቁጭ አለች ከእንቅልፏ እንደ ተነሳች ያስታውቅባታል ፍቅር የት ሄደ አለች አለ ይመጣል አለቻት ግራ ገባኝ ማንን ነው
ፍቅር ብላ የጠራችው እልኩ በውስጤ ጆን እንደ መጣ ፍቅር አለችው ቲቲ ተነሳሽ አላት እናቴ ድረሽ አልኩ እንዴት እንደዛ ብላ ትጠራዋለች ፍቅረኛዋ ቢሆን እንጂ ብዬ በቃ ተረበሽኩ ስልኬ ሚሴጅ
ሲገባልኝ አይቼ ከወንበሩ ላይ አነሳሁት እረ አትናደጂ ትዙሻ ይላል ጆን ነው ቀና ብዬ ሳያው ጠቀሰኝ በቅፅበት ያሁሉ ንዴቴ ጠፋ ሰዓቱ እየመሸ ስሄድ ጆን እኛ እንሂድ ሲል.....

ይቀጥላል
2.7K viewsᴬᴮᴵᴺᴱᵀ, 18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 20:53:32 ገጣሚ ∞ እዮብ ዘማሪያም

አቅራቢ ዘመድኩን

@yefikir_debdabewoch
2.7K views., 17:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 18:15:44 #ያሜናዳብ

#ክፍል_ዘጠኝ

ልቤ የሆነ ስሜት ሲሰማኝ ይታወቀኛል ሁሉም ዝም አለ አይንሽን ግለጪ ስትለኝ ቀስ ብዬ አይኔን ስገልጠው ባለፈው ያስተዋወቁኝ ልጅ ፊቴ ላይ ተደቅኗል ነገሩ ግራ ገባኝ ትዙ ወድጄሻለሁ እባክሽን አብረን እንሁን አለኝ አንቺም በብቸኝነት ነው ያለሽው እኔም እንዳንቺው አለኝ በጥፊ ብለው ደስ ባለኝ ነበር እንደ ምንም ራሴን አረጋግቼ እኔ እኮ የራሴ የምወደው እና የማፈቅረው ሰው አለ በዛ ላይ እኔ እና አንተ የተዋወቅ ነው ትናት ነው አልኩት ምንም አለለኝም እንደዛም እያወራሁት
አፍንጫዬን ያወደኝ ጠረን አሁንም አፍንጫዬ ላይ ነው በዚ መሀል የሙዚቃውን ድምፅ ከፍ አደረጉት ሁሉም በየ ራሱ ጥሩ ሙድ ላይ ነው ኤልሲ ከውጭ ስልክ ስታወራ ቆይታ ወደ
ውጭ እንድወጣ በእጇ ምልክት ጠራችኝ
ስሄድ አናግሪው ይፈልግሻል አለችኝ ማነው ልላት ስል ስልኩን ሰጣኝ ዘላ ገባች ደጋግሜ ሄሎ ስል ዝም ነው መልስ የለም ተናድጄ ስልኩን ልዘጋ ስል ትዙ አለኝ ጆን ነው እጄ ስልኩን ለመያዝ ከበደው ማውራው ጠፋኝ ደህና ነሽ ግን አለኝ ምን አድርጌ ነው ግን አልኩት
ጫጫት ነገር አለ እስቲ ትንሽ ተንቀሳቀሺ አለኝ ሩጬ ክላሴ ገባሁ እንኳን ተወለድሽልን አለ በቃ የእውነት ለመናገር ከምንም በላይ ደስ አለኝ እንባዬ ይፈሳል የተወሰነ አወራሁትና ማታ እደውልልሻለሁ ወደ ፕሮግራምሽ ተመለሺ አለኝ ደስታው እጥፍ ሆነልኝ በቃ ጆንን ካገኘሁ በኋላ ያዩኝ ራሱ ምን አገኘሽ እስኪሉኝ ደስ አለኝ
ቀኑን ደስ በሚል ሁኔታ አሳለፍን ግን ሚገርመ ው ቀን ላይ አፍንጫዬን ያወደው መአዛ አስካሁን አልተረሳኝም ማታ ለይ ጆን ደውሎልኝ ብዙ አወራን በቃ የልደቴን ቀን ተከፋሁ ብዬ ነበር ግን ጭራሽ ተስምቶኝ የማያውቅ አይነት ስሜት ተሰማኝ ልደቴን በዚም በዚያም ብዬ አሳለፍኩ ለጆን ግን ከዛን ቀን በኋላ በተደጋጋሚ ብደውልለት ስልኩ አይሰራም በቃ ከአይኔ ከተለየ አርባ አምስት ቀን ሞላው እኔ ግን ለሰከንድ ከውስጤ አላወጣሁትም ብቻ ቀናት ተቆጠሩ እኔም በመሀል ሁሉም ነገር
አስጠላኝ በቃ አምላኬን አማረርኩ ምን ብበድል ነው ብዬ አለቀስኩ ሁሉም ነገር ግራ ገባኝ ሰው የወደዱት ከአይን በራቀ ቁጥር ይረሳል ይባላል ታድያ ምነው የኔ በረታብኝ ተቃራኒ ሆነብኝ እቤት ማንንም ማውራት አስጠላኝ ልክ ጆን ጋር በተለያየን ሁለተኛ ወሩ በቃ ቀኑ ትዝ ሲለኝ እንደ ማበድ አደረገኝ ጥዋት ላይ ክለሴን ዘግቼ ማንም እንዳይጠይቀኝ ብዬ ተኛሁ ቢቆፍ ቁፍ ቢለምኑኝ አልሰማ አልኩ እንባዬ እስኪ ደርቅ አለቀስኩ ቀኑን ሙሉ ክላሴን ዘግቼ ወደ ማታ ላይ አክስቴ በቃ አለቀሰችብኝ አትልፊ ሂጂ አልኳት ልክ ከምሽቱ ሁለት ሰአት ላይ ከቀኑ በተለየ በሩ ተንኳኳ ዝም አልኩ አሁንም ተንኳኳ ዝም አልኩ እረ ትዙ ምንሼ ነው አለኝ የጆን ድምፅ ነው በመብረቅ የተመታሁ
መሰለኝ በቃ ለመናገርም ከበደኝ እንደዛ ተኝቼ የዋልኩትን ከአልጋዬ ላይ ተስፈንጥሬ ተነሳሁ ቀስ ብዬ በሩን ስከፍተው ጆን ከፊቴ ላይ ቁሟል ዘልዬ ተጠመጠምኩበት በቃ በጣም ደስ አለኝ ደረቱ ላይ ማስቲሽ ሆንኩበት በይ ልብስ ቀይሪና እራት ልጋብዝሽ አለኝ ብቻ ደነግጫለሁ እሺ ብዬ እስክ ቀይር በጓሮ እናቴ ዘንድ ሂዶ እግሯ ስር ቁጭ ብሎ
ያወራል በቃ እሱ ካለ ግቢው ሰላም አለው ተያይዘን ወጣን በጣም ነበር ደስ ያለኝ እራት ጋብዞኝ ትንሽ መጠጥ ነገር ጠጥቼ ለው ብያለሁ በተላይ ስጠጣ ሁሌም ይስቅብኛል ምናለ የሱን ሳቅ
ለማየት ስል ሁሌም በሰከርኩ እላለሁ በውስጤ ልክ ወደ አራት ሰአት አከባቢ ተመለስን ጆን ሰላም እደሪ ብሎ ወደ ክፍሉ ገባ እኔ ግን ንፋስ እንዲ ልቀበል ብዬ በረንዳ ላይ ቁጭ አልኩ ሰአቱ እየሄደ ነው ልክ ሳስነጥስ ጆን ወጣ ምነው ምን ሆንሽ ብሎ ወደ እኔ መጣ አጠገቤ ቁጭ አለ እረ ተነሽና ግቢ አለኝ መልስ አልሰጠሁትም ብቻ በስስት አይኑን ነው የማየው አንቺን እኮ ነው ምልሽ አለኝ ፈገግ ብዬ ሳመኝና ልግባ አልኩት እረ ድፍረት ሚስቴ እንዳሰማሽ አለኝ ቆሌዬን ሳይሆን ቆዳዬን ነው ግፍፍ ያለ ምን ማለት ፈልጎ ነው እንዴ እኔስ አልኩ
በልቤ ማወራው ጠፋኝ ምነው ደነገጥሽ አለኝ.....

ይቀጥላል
2.8K viewsᴬᴮᴵᴺᴱᵀ, 15:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 20:14:37 #ያሜናዳብ

#ክፍል_ስምንት

በቃ ጠረኑ ወደ ውስጤ ሲገባ ፈጣሪ የሚያውቀው በቃ እኔ ጋር ያለ መሰለኝ ጆን ይመጣል ብዬ ዛሬ ነገ ብልም የለም ሳምንት ሆነው ሳይመጣ....እብድ ሆንኩ በራሴ ያዘንኩኝ እናቴን ምንም ስትለኝ እሺ ምላትን ዛሬ ግን እሷ ጋር ጭቅጭቅ ሆነ ስራዬ በቃ ያለ እሱ መኖር እንደ ማልችል ውስጤ አምኖ ተቀብሏል ያፈቀሩትን ሰው በቀላል እንዴት ከውስጥ በቀላል ማውጣት ይቻላል የደረሰበት ነው ጉዳትቱን የሚያውቀው ኤልሲ እንደ ምወደው አውቃለች በቃ ልታፅናናኝም ብትሞክርም ውስጤ ግን ይሄ ነው ለማለት ይከብዶኛል ግን ግፍ ይሆን አልኩ በልቤ ስንት ወንድ እንዳል ለመነኝ ዛሬ እኔ በተራዬ እለምናለሁ ለምኜም አላገኘሁ ሁሌም በአንድ ነገር አምናለሁ ግዜ ሁለት ነው አንድ ለእኔ አንድ በእኔ ለእኔ ሲሆን ሰው ላይ ኮራሁ በእኔ ሲሆን
ግን እኔ ራሴ ለመንኩ በዚህ እንዳለ ሁለት ሳምንት አለፈው እናቴ ግን የሆነ የምታውቀው ነገር እንዳለ ልቤ ይጠረጥራል በቃ ሁሌም አትጨነቂ ይመጣል ነው ምትለኝ ከሁለት ሳምንት በኋላ ጓደኞቼ እቤት መጡ ጆን ከሄደ በኋላ ከግቢ አልወጣሁም በግድ ይዘውኝ ወጡ ሁሌም ወደ ምንዝናናበት ባህር ዳርቻ ሄድነ በቃ ሁሌም ወደ ዚህ ቦታ ስመጣ ውስጤ እረፍት ያገኝ ይመስለኛል ብቻ ውስጤን በጣም ደስ ይለዋል በዚህ መሀል ጓደኞቼ አንድ ልጅ አስተዋወቁኝ ሊያወራኝ ዳር ዳር ይላል ከአድናቆት ጀመረ እኔ በህይወቴ ሰው ሲክበኝ አልወድም ስለ ራሱ ሳልጠይቀው
ይለፈልፍ ጀመረ ጓደኞቼ ከእኔ ትንሽ ራቅ ብለዋል ውሀው ውስጥ ይሮጣል እኔ ደግሞ ሁሌም ባህር ውስጥ እግሬን ነክሬ
መቀመጥ እወዳለሁ አጠገቤ ቁጭ ብሎ እያወራ ነው ግን ረስቼዋለሁ ምን አልከኝ ስለው የት ሄድሽ አለኝ ፈገግ እያለ ይባስ በነፃ ሀሳብ በትንሽ ትዝታ በብዙ ፍቅር ሸኘኝ ጆንን ከፊቴ አመጣው ካልተጠየቅ የማያወራው አንቺ በሎ እጄን ነካ አደረገኝ ከሀሳቤ ቀሰቀሰኝ እና ባንክ ቤት ነው ምሰራው እልሻለው አለ ፈገግ እያለ
በምን እንደ ጀመረው ራሱ አላውቅም በዚህ መሀል ብዙም ባይሆን ድብርቴ ለቀቀኝ በሳምንቱ ሁሉም ልደቴን ሊያከብሩልኝ መጡ የእውነት ለመናገር በየ አመቱ ልደቴን ሳከብር ከምንም በላይ
ደስተኛ ሁኜ ነው ዘንድሮ ግን ወደ ህይወቴ መጦ ሳላስበው በሄደ ሰው ትንሽ ተከፍቷል ባለፈው ያስተዋወቁኝ ልጅም
መጧል ነገሩ ትንሽ ግራ ቢገባኝም ምንም አላልኩም ሁሉም ያመጣልኝን ስጦታ ይሰጡኛል የዛሬ አመት ከማልረሳ ውስጥ ኤልሲ በጣም ትልቅ ካርቶን ውስጥ አንድ ደስታ ከረሜላ አድርጋ ሰጣኛለች ክርቶኑን
ላየው ግን ሌላ ነገር ነው የሚያስመስለው ከሁሉም ጓደኞቼ በላይ እሷ የምትሰጠኝ ነገር ይነስም ይብዛም ምንም ይሁን ብቻ
ያጓጓኛል በዚህ መሀል ሁሉም ከሰጠኝ በኋላ የእሷን እየጠበኩ እያለ ትንሽ የተጠቀለለ ነገር በእጇ ይዛ መጣች አይንሽን ክደኚ አለችኝ ልክ እንደ ከደንኩ ከሰከንዶች በኋላ የሆነ ጠረን አፍንጫዬን
አወደው አሁን ለመጨሁ ትንሽ ቀረኝ በቃ ውስጤ በሰከንድ ውስጥ ልቤ የሆነ ስሜት ሲሰማኝ ይታወቀኛል ሁሉም ዝም አለ አይንሽን ግለጪ ስትለኝ ቀስ ብዬ
አይኔን ስገልጠው.......

ይቀጥላል
2.7K viewsᴬᴮᴵᴺᴱᵀ, 17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ