Get Mystery Box with random crypto!

👑የፍቅር_ደብዳቤዎች 💏

የቴሌግራም ቻናል አርማ yefikir_debdabewoch — 👑የፍቅር_ደብዳቤዎች 💏
የቴሌግራም ቻናል አርማ yefikir_debdabewoch — 👑የፍቅር_ደብዳቤዎች 💏
የሰርጥ አድራሻ: @yefikir_debdabewoch
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8.34K
የሰርጥ መግለጫ

FOR COMMENT
@ABIRIHANN

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-07-14 20:34:15 ላጤዎቹ PART 1



አሪፍ የፍቅር ታሪክ
513 viewsᴬᴮᴵᴺᴱᵀ, 17:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 17:39:05 ​ ፍቅርጠላቴነው
.

በእርግጥ ለታደለው
አፍቅሮ ላገኘው
ፍቅር ጠላት አይደል
ጓደኛ ወዳጅ ነው…
.

ለኔ ግን ጠላቴ
ባለጋራዬ ነው
አዋዶ ትቶኛል
ልቤን ቀምቶኛል
ገንዘቤን ንብረቴን

ሁሉን ወስዶብኛል
በመውደድ አኑሮ
በናፍቆት ገሎኛል
.

ታዲያ ከዚ በላይ
የቀረው ምንድነው
ተውኝ አታንሱብኝ
ፍቅር ጠላቴ ነው።



የፍቅር ደብዳቤዎች
670 viewsꪖꪉỉ, 14:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 22:17:46 ☞የፍቅር ደብዳቤዎች

​​➢➢ላ’ንዲት የገጠር ሴት➢➢

ስትፈጭ የኖረች ሴት፣
መጁ በመጠኗ፣ ወፍጮውም በልኳ፣
ጓያ ትፈጫለች
ጓያ ሽሮ ሲሆን ያበቃል ታሪኳ !!

አስባው አታውቅም…
ወደ ኦናው ምድር ለምን እንደመጣች፣
ከ’ለታት አንድ ቀን፣ ከና’ቷ ሆድ ወጣች፣
ከ’ለታት አንድ ቀን፣ ጡት አጎጠጎጠች፣
ከ’ለታት አንድ ቀን፣ ለባሏ ተሰጠች……

ተዚያን ቀን ጀምራ፣
ተዚያን ቀን ጀምሮ፣
ድንግል ድንጋይ ወቅራ፣
ትፈጫለች ሽሮ……

አታውቅም፣
ማን እንደሚባሉ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣
አታውቅም፣
ሹማምንት በ’ሷ ስም፣ ምን እንደሚሠሩ፣
አነሳኹት ‘ንጂ፣ እኔም ለነገሩ፣
ፖለቲካ ጥበብ ራስን ማራቀቅ፣
ምን ይጠቅማትና ጓያዋን ለማድቀቅ

ከቶ ማንም የለ, አበባ ‘ሚሰጣት፣
ከቶ ማንም የለ፣ ከተማ ‘ሚያወጣት፣
ከቶ ማንም የለ ፣ በዳንኪራ መላ፣ ወገቧን የሚያቅፋት፣
ልፋቷም፣ ዕረፍቷም፣
ወደዚህ መጅ መሳብ
ወደዚያ መጅ መግፋት……
እንደ ዓባይ ፏፏቴ፣
ሽህ ዓመት ቢንጣለል፣
ቢጎርፍም ዱቄቱ፣
እንደ ሲኦል ወለል፣ ጫፍ የለውም ቋቱ!

ከዘመናት ባንዱ
መስተዋት ፊት ቆማ፣ በተወለወለው፣
ራሷን ለማየት፣
ከጸጉራ ላይ ያለው
ዱቄት ይኹን ሽበት ሲያቅታት መለየት፣
ያኔ ይገባታል
የተሰጣት ዕጣ፣
ከማድቀቅ ቀጥሎ፣ መድቀቅ እንዲመጣ…

የመጅ አጋፋፏ - አምሳለ ሲሲፈስ፣
ከቋት ሥስት እንጅ፣ ሢሳይ አይታፈስ፣
ትቢያ ‘ሚተነብይ ዱቄት በዙሪያዋ፣
ከባርኔጣ አይሰፋም፣ የኑሮ ጣሪያዋ፣
"ስትፈጭ የኖረች ሴት"
ይህ ነው መጠሪያዋ!

➛➛ገጣሚ ፦ በእውቀቱ ስዩም
✰አዘጋጅ ፦ @yefikir_debdabewoch
923 viewsExample, 19:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 23:08:32 #የፍቅር_ደብዳቤዎች

የጠላሁሽ ለታ

የጠላሁሽ ለታ....
ዓለም ትዙርብኝ
ፀሐይም አትውጣ ጨለማው ይምጣብኝ
ጨረቃዋም ትጥፋ ከዋክብት ይርገፉ
ውቅያኖሶች ደርቀው ዕፅዋቶችም ይጥፉ
........……………………
የጠላሁሽ ለታ…
ለክህደቴ ዋጋ ይሁዳ ይበሉኝ
ለጭካኔዬ ልክ ሂትለርን ያድርጉኝ
ነፍስ እንዳጠፋ ሰው ሰዎች ይጠየፉኝ
……………………………………
የጠላሁሽ ለታ…
እግሮቼም እጆቼም
ዓይኖቼም ጆሮቼም ለኔ አይታዘዙ
አፍ ከነፍሴ ጋራ
ተባብረው ተስማምተው
የክህደቴን ቃላት ለዓለም ይናዘዙ
…………………………………
የጠላሁሽ ለታ…
በበድን አካሌ በጨቀየው ነፍሴ
በተነጨው ፀጉሬ በረገፈው ጥርሴ
ባስቀያሚነቴ ሚደርስብኝ ልጣ
በቁሜ ልሰቃይ ልታሰር ልቀጣ
…………………………………
ፍቅሬ……
የጠላሁሽ ለታ እርግማኖች ሁሉ
ወደኔ ይቅረቡ ብዬ የምመኘው
አንቺን የማልጠላ ፍፁም ሆኜ ሳይሆን
ካላንቺ ለመኖር ስለማላስብ ነው
………………………………
ፍቅሬ……
እኔም አንቺም ውዴም ካንድ ወንዝ ተቀድተን
ከስሜቴ ስሜት
ከእምነትሽ እምነት በፅናት ተጋርተን
የተገባባነው ቃል በኑሯችን ፀንቶ
ካኖረን በፀጋው ሁሌም አበርትቶ
………………………………………
የምጠላሽ ለታ…
በጉዞዬ መሃል እንቅፋቴ ይብዛ
ምጠለልበትም ምበላውም ልጣ
በቁሜ ልሰቃይ ልታሰር ልቀጣ
…………………………………
የምጠላሽ ዕለት…
እነዚህ መዓቶች በላዬ ሊዘንቡ
ሊወርዱ ከሆነ
ዘላለም ስወድሽ
ነፍሴ ከስቃዪ ከርግማኑ ዳነ።
1.5K viewsᴬᴮᴵᴺᴱᵀ, 20:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 20:06:47 ይገርማል ስላንተ ልፅፍ ስል ቃላቶች እየሸሹኝ
እነሱ ሲሄዱ እኔ ስከተላቸው ገደል ጋር ደረስኩኝ
ጣርኩኝ ለፋው ሌሎቹ ሲያመልጡ አንዲት ቃል አገኘው
የምትል እወድሀለው !
1.5K viewsᴬᴮᴵᴺᴱᵀ, 17:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 19:50:38 #ገጣሚና_አንባቢ
ቶላዋቅ ኢተፋ

@yefikir_debdabewoch
1.5K viewsᴬᴮᴵᴺᴱᵀ, 16:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 16:00:03 ​​❥ ..........

" ፍቅር የሚጀመረው በልባችን ስንመራ ፣እንደራሳችን ቆጥረን ስለሌሎች ስንጨነቅ ፣ዉለታን ሳንፈልግ ስናገለግል ፣ምላሽ ሳንጠብቅ መስጠት ስንጀምር ነው፡

@YefIkIr_debdabewoch
❥❥⚘❥❥
1.9K viewsᴬᴮᴵᴺᴱᵀ, 13:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 18:19:35 የኔታ ነህ ለኔ


ያ ሸንጋይ ምላስህ ቅቤ የሚያቀልጠው
ፎርጅድ ማንነትህ ከላይ የሚታየው

መታወቂያው ሌላ ማሞው ሌላ ሆነህ
ያንቺ ነኝ ስትለኝ ልብህን ሸሽገህ

ሰው አማኙ ልቤ ለፍቅርህ ሲሸነፍ
ምስኪን ማንነቴ አንተን አምኖ ሲከንፍ

የታሻለ ስታይ አቁስለኸው ልቤን
ትተኸኝ ስትሄድ ንቀኸው መውደዴን

እጅጉን ብጎዳም ባንተ ምክንያት ያኔ
አመሰግናለሁ የኔታ ነህ ለኔ
ስለሰው ማንነት ያዘረፍከኝ ቅኔ

ፅዮን

JOIN & SHEAR

:¨·.·¨: ❀  
 `·.
2.1K viewsᴬᵇⁱⁿᵉᵗ, 15:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 19:44:37 አንተ ማለት ለኔ

ድምፅ:– በ ሰሊና

መልካም አዳር!!!
2.4K viewsᴬᴮᴵ, 16:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 21:32:43 እውነት አንቺ ሴት ነሽ
3.1K viewsᴬᴮᴵ , 18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ