Get Mystery Box with random crypto!

#ያሜናዳብ #ክፍል_አስራ ሁለት እሺ እመዬ ትምጣ እና ልንገራት አልኩት ሳቅ አለና | 👑የፍቅር_ደብዳቤዎች 💏

#ያሜናዳብ

#ክፍል_አስራ ሁለት



እሺ እመዬ ትምጣ እና ልንገራት አልኩት ሳቅ አለና እሺ አለ እናቴ ከደጀ ሰላም እንደመጣች ስነግራት አዋ ነግሮኛል ሂዱ አለች ምን ግዜ ነገረሽ አልኳት ማታ ላይ ነግሮኝ ነበር ልነግርሽ ነበር ተኝተሻል አለችኝ እናቴ ጆን ላይ የጣለችው እምነት
ይሄ ነው ለማለት ይቸግረኛል ከምንም በላይ ታምነዋለች ስድስት ሰዓት እንደ ሆነ ባህር ዳር ኤርፖርት ደረሰን ሰላሳ ደቂቃ አላቹ ሲባል ቁጭ አልን አንድ ያልተመለሰልኝ ነገር ቢኖር በቃ የሆነ ነገር ለማድረግ ደቂቃ አይፈጅ በትም ምንም ነገር ሲያደርግ ለማንም አይናገርም
አድርጎት ወይም ፍፅሞት ነው ማገኘው ማያደርገውን ይቅርና የሚያደርገውን እንኳ መናገር አይፈልግም ከደቂቃዋች በኋላ በረራ አደረግን ልክ ከአርባ ዲቂቃ በኋላ አ/አ ደረስን ምሳ በልተን ወደ ዘጠኝ ሰአት አከባቢ ላይ ወደ አሜርካ ኢንባሲ ሄድነ በቃ ኢንባሲውን ሳየው ትዝ አለኝ ለአመታት አሜርካ ለመሄድ ስል ከጣልያን እስከ ሱዳን ድረስ የሄድኩት ስንት ብሬን
የጨፈጨፍኩበት ፊቴ ላይ ድቅን አለ ግን ጆን ለምን መጣን አልኩት ሳቀብኝ ምትፈርሚው ነገር አለ አለኝ ምን አልኩ በቃ ውስጤ ይሄ ነው ከሚባለው በላይ ደንግጫለሁ ልክ እንደ ገባን ፎቶ አነሱኝ በተላያየ ቦታ አስፈረሙኝ ሜድካል ተብሎ ወደ ምርመራ ክፍል ሄድኩ ብቻ ምን ያላረጉኝ ነገር አለ ለምን እንደ ሆነ አላውቅም ብቻ ጆን ከአጠገቤ ስላል ተለየ ምንም ፍረሀት አልተሰማኝም ውስጤ ከመደንገጥ በስተቀር ልክ እንደ ጨረስን ቁጭ ብለን እያለ አንዱ መጣና ጆን በቃ ሂዱ ያለውን ነገር አሳውቅሀለው ሲለው እሺ ብሎ ወጣን አ/አ ውስጥ እየዞርን አመሸን ጆን ጋር አንድ ክፍል ውስጥ እንደ ምናድር ሳስበው ደስ አለኝ

ሀርሞኒ ሆቴል ሩም ይዘናል አለኝ እህ መቼ ስለው ኦንላይን ኢንተርኔት ላይ ነዋ አለ እየሳቀ አንቺ ከዚህ ነገር ነፃ ነሻ አለ እያፌዘብኝ እንኳን ሆንኩ አልኩት ሰአቱ እየመሸ ሲሄድ ወደ ሆቴሉ ሄድነ ደብል አልጋ ነበር የያዘው እራት ሰዓት እስኪ ደርስ ሻወር ወስደኩ ምናምን ልክ ራታችንን በልተን እንደ ጨርሰን ሩም ገባን
ትንሽ ሚጠጣ ነገር ቀምሼ ስለ ነበረ ወሰወሰኝ ጆንን የቅድሙ መጠጥ አማረኛ አልኩት አረ አንቺ ልጅ እያለ ሩም ድረስ አስመጣ በቃ ማታ ምን እንደ ተፈጠረ አላውቅም ጥዋት ስነሳ ከጆን ደረት ላይ ተለጥፌ ተኝቻለሁ በቃ በድንጋጤ ውሀ ሆንኩ በቃ ምን እንደ ተከሰተ ማወቅ አልቻልኩም ራሴን በጣም አሞኛል የሞት ሞቴን ከደረቱ ላይ እንደምንም ብዬ ተነሳሁ በጣም ራሴን ይዞኛል እንደ ምንም ብዬ ቀና ለማለት ሞከርኩ ልብሴ አልወለቀም የጆን ልብስም አልወለቀም ታድያ እንዴት እሱ ጋር ልተኛ ቻልኩ ብዬ በጣም ነበር ግራ የገባኝ ነገሩ ግርምት ፈጥሮብኛል ማታ በጣም የጠጣሁ መሰለኝ ራሴን በጣም አሞኛል ስንቀሳቀስ ጆን ነቃ አንቺ ሰከራም አለኝ ምንድ ነው የሆንኩት አልኩኝ ለካስ እንደዚህ ሰከራም ነሽ አለኝ አፈርኩኝ እየሳቀብኝ ተነስቶ ሻወር ገባ በጣም ስላመመኝ ሻወር መግባት አልፈለኩም እስኪ መጣ ልብሴን ቀያየርኩ ልክ ሲመጣ አይኔ ደረቱ ላይ አረፈ ይሄ ደረት ላይ ተኝቼ ነዋ የሆንኩትን ሁሉ የረሳው አልኩ በልቤ እረ አይንሽን ንቀይ አለኝ ባክህ ዝምበል የግልህ አደረከውሳ አልኩት ሳቄን አያፈንኩት በለው ማነው የልብ ልብ የሰጠሽ አለኝ እእ አንድ ጢባራም አለ አንድቀን አስተዋውቅሀለው አልኩት እየሳቀብኝ ከሆቴሉ አቅፎኝ ወጣ ልክ ባ/ዳር ገብተን ወደ ሰፈር እየሄድን እያለ የጀን
ወንድም ክላክስ አደረገ ጆን ወንድሙን ሲያየው ፈገግ አለ ከመኪና ወጦ መጣና ጆን እግር ስር ተደፋ...........

ይቀጥላል