Get Mystery Box with random crypto!

ምኞት ክፋል 52 ደራሲ ጥላሁን ተስፋዬ . . #የመጨረሻ ክፍል . . ድንገት እመካከላቸው | የፍቅር ጎጆ

ምኞት

ክፋል 52

ደራሲ ጥላሁን ተስፋዬ
.
.
#የመጨረሻ ክፍል
.
.
ድንገት እመካከላቸው ወጣ ገባ ስትል የነበረች አንዲት መኪና
አቅጣጫ ቀይራ ከመሀላቸው ስትወጣ ሚኪ ዞሮ መኪናዋን
የሚያሽከረክረው መሳይ መሆኑን ሲመለከት በድንጋጤ እየጮኽ
ፅናት መንገድ መንገድ ዘግታ እንድታስቆመው አደረገ። መሳይም
በሁኔታው እየተደነባበረ ከመኪናው ወርዶ ሮጦ ከመጣው ሚኪ
ጋር ተቃቀፈ። ተያይዘው ወደ አንድ ሆቴል በማምራት እንዴት
ነገሮች ተቀይረው ለዚህ እንደበቃ እየጠየቀው በመሀል የፅናት
ስልክ ጠራ ። ከቦርሳዋ ውስጥ አውጥታ ተመለከተችው። ፊቷ
ተለዋወጠ።
" እኼ የማያፍር ሰይጣን ደግሞ ስልኬ ይደውላል እንዴ!" ብላ
ስልኩን በመዝጋት በንዴት ስትንጨረጨር ከመሳይ ጋር የጀመረውን
ጫወታ አቋርጦ•••
"ማነው ፅኑዬ?
" ያ ብሩክ ተብየው ነዋ!"
"ተይው አትበሳጪ ስራው ካንቺ በላይ እኔን ማበሳጨት
እንደነበረበት አውቃለሁ። ግን ደነዘዝኩ ባንዱ ጉዳት የተሰበረው
ልብሽ ሳይጠገን በጉዳት ላይ ጉዳት ሲደራረብብሽ የመበሳጨትም
አቅም ያጥርሽና ትደነዝዣለሽ። እንደ ብሩኬ አይነት ሰዎች ብዙ
ናቸው። ሲበዛ እራስ ወዳዴች ከመሆናቸው የተነሳ አንቺ ችግር
ውስጥ ስትገቢ ከዛ ችግር እንድትወጪ ከመርዳት ይልቅ
-በችግርሽ
-በእጦትሽ
-በስጋት እና በፍርሀትሽ
ሁሉ ተጠቅመው አንቺን እንዴት አድርገው ለፍላጎትና ለጥቅማቸው
መሳካት እንደሚጠቀምቡሽ ነው የሚያስቡት።
ብሩኬም እንደዚሁ ነው ያደረገው። በምኞት ላይ በፈፀምኩት
ክህደትና በደል ከባድ ፀፀት ውስጥ መውደቄን በፀፀት ውስጥ
ባገረሸው ፍቅሯ መጎዳቴንና የትም አለች ቢሉኝ እሷን ለማግኘት
የማልወጣው ተራራ የማልፈነቅለው ድንጋይ አለመኖሩን ሲረዳ
ሰው ቢሆን ኖሮ አጠገቤ ሆኖ ጉዳቴን በተጎዳ። ፍቅሬን ምኛቴን
ፀፀቴን እንዳገኛት ከጎኔ ሆኖ በደከመ። ግን እሱ ሰው ቢሆንም
እንደሰው እየኖረ አልነበረምና የኔን መጥፎ አጋጣሚ እራሱን
ጠቅሞ እኔን ለመጉዳት ተጠቀመበት አንድ ያለችኝ መፅናኛ እህቴን
አንቺን ሊያሳጣኝ ተሯሯጠ። ፈጣሪም ሩጫውን ገታው። ሀሳቡ
ሳይሳካ መንገድ ላይ አስቀረው። የኔ ምኛት ግን ጠፍታ አትቀርም!"
አለና እንባ ያቀረሩ አይኖቹን ጨምቆ አቀረቀረ።
መሳይ ሚኪ ያወራውን ሲሰማ በተቀመጠበት ልቡ መምታት
ያቆመች መሰለው ምድርና ሰማዩ ተገለባበጠበት።
በዛች ቅፅበት ምን እንደሚያወራ ፣ምን እንደሚል፣ ምን ማድረግ
እንዳለበት ማወቅ ተሳነው!።
ምኛት ታየችው የሚያጣት ሚኪ የሚወስድበት መሰለው። ብድግ
ብሎ ወደ ሽንት ቤት ለመኼድ አሰበና ጭንቅላቱ ውስጥ
የተፈጠረው ውጥረት፣ፍጭት እና ጩኸት ገና ከወንበሩ ሲነሳ
አዙሮ የሚደፋው መሰለውና መነሳቱን አልደፈረም።
እዛው በተቀመጠበት በሁለት እጆቹ ፊቱን ሸፍኖ እሱም እንደሚኪ
አቀረቀረ።
መሀላቸው ቁጭ ያለችው ፅናት ብሩክ ሲደውል የተንቀለቀለው
ንዴቷ ጠፍቶ በረዶ ሆነች።
የሁለቱንም ስሜት በየተራ እየተመለከተች ነበርና ሚኪ ባውራው
ነገር መሳይ ለእብደት የዳረገውን ያለፈ መጥፎ የፍቅር ሂወቱን
አስቦ የተረበሸ መሰላት ።
"እባክህ ሚኪ እንደዚህ አትሁን እሱንም ረበሽከው እኮ! እባክህ
ተረጋጋ!"
ብላው ደሞ ወደ መሳይ ዞራ "ድንገት አግኝተንህ ማሰብ
የማትፈልገውን መጥፎ ትዝታህን ስለቀሰቀስንብህ ይቅርታ እባክህ
አትረበሽ።
መሳይ ለፅናት መልስም አልሰጣትም። ቀናም አላለም።
ግራ ሲገባት ወደ ሚኪ ተጠግታ ገና ሚኪዬ ብሏ እንደተጣራች
ሚኪ ካቀረቀረበት ቀና ብሎ ድፍት ያለውን መሳይን
እየተመለከተ•••
"ከሁሉም ነገር በፊት ትልቅ ይቅርታ እጠይቅሀለሁ መሳይ
ወንድሜ! ይቅርታ የምጠይቅህ ግን ዛሬ ስለረበሽኩ ሳይሆን ለቆየ
በደሌ ነው። በደሌ ምን እንደሆነና ለምን ይቅር በለኝ እንዳልኩህ
ኑዛዜየን ስጨርስ ትረዳዋለህ።
"አዋ ዛሬ ትክክለኛው ቀን ነው ከዚህ በፊት ብዙ ግዜ አግኝቼህ
ሊሆን ይችላል። ፍቅርህን ናርዶስን ከማጣትህ በፊትም እሷን
አጥተህ ልክ እኔ ዛሬ ቀን እንደጨለመብኝ በቀን ጨለማ
ተውጠኽም እንዳገኘሁኽ አስታውሳለሁ።
ግን መጎዳትህን አየሁ እንጂ ጉዳትህን አልተጎዳሁትም ነበር።
በፍቅር ህመም ክፉኛ መታመምህን ተመለከትኩ እንጂ ህመምህን
አልታመምኩትም ነበር። ካጠገብህ ዘወር ስል እረሳዋለሁ። ያንተ
እንደዛ መሆን አይገባኝም፣ አያስጨንቀኝም፣ አይቆረቁረኝም።
ዛሬ ግን ሕመምኽን ታምሜዋለሁና ጉዳትህን ተጎድቼዋለሁና ልክ
እንዳየሁኽ ስላንተና ስለናርዶስ የማውቀውን ሚስጥር ሳልነግርህ
ማለፍ አልቻልኩም። አቃተኝ።
ሚኪ ስለፍቅረኛው ናርዶስ እኔ የማላውቀውን ሚስጥር ይነግረኛል
ብሎ አልጠበቀምና ስለምኛት እያሰበ እሱን ከማድመጥ ውጪ
ቀናም አላለም።
"መሳይ ወላጅ አባትህ ጓደኛዬ ነው እሱን ይቅር የማለት እና
ያለማለት ያንተ ፋንታ ነው ለኔ ግን ሁለቱም ጓደኛቼ አንድ አይነት
ሰይጣኖች ናቸው አባትህ እና ብሩኬ!" አለ። እኼን ግዜ እንኳንስ
የመሳይ የፅናት የልብ ትርታ እጥፍ ሆነ ሚኪ ምን ሊያወራ ነው
ብላ ሁሉ ነገሯ ስራ ፈትቶ ሚኪ ላይ ተተከለች።
መሳይ "እኼ ሰው ደሞ ምን ሊያሰማኝ ነው ፈጣሪዬ እባክህ
የምችልበትን አቅም ስጠኝ። አለ አንገቱን እንደደፋ ፍርሀት ከላይ
እስከታች እየናጠው። ሚኪ ቀጠለ•••
" አባትህ ከናርዶስ ጋር የነበረኽን የፍቅር ግኑኝነት በጭራሽ
አይፈልገውም ነበር።
ይኽን አንተም ታውቀዋለኽ። ናርዶስን ያልፈለጋት ያጠፋችው ወይ
ያጎደለችው ነገር ስለነበር አይደለም። ጥፋቷም ጉድለቷም ድኻ
መኾኗ : ከድዃ ቤተሰብ መፈጠሯ ብቻ ነበር።
ባባትህ አይን ይቺ ያንተ ድኻዋ ናርዶስ እሱ ሊድርኽ ለፈለገው
ሰው እንዳይድርኽ መዃል የገባች የፍላጎቱ
መታከሚያ ሆስፒታል ሰው
ለመጠየቅ መጡ። ከሌሎቹ ህሙማን ጋር አልግባባ በማለቱ
ለብቻው ተገሎ በአንድ ሰፊ ክፍል ውስጥ እንዲቀመጥ ወደ
ተፈረደበት አንድ የአይምሮ ህመምተኛ ( እብድ ) ክፍል እንደደረሱ
ወደ መስኮት ተጠግተው ወደ ውስጥ ሲመለከቱ•••
ክፍሉ ሰፊና ባዶ ነው። እክፍሉ ግድግዳ ላይ ሁለት ስእሎች አሉ።
አንደኛው ስእል የሴት ሲኾን ሌላኛው ደግሞ የወንድ ስእል ነው።
ከስእሎቹ ፉት ህመምተኛው ቆሟል። የወንዱን ስእል በቡጢና
በቴስታ ይመታል ግንባሩና እጁ ተጋግጧል ። የሴቷን ስእል
እየደጋገመ በፍቅር ይስማል። ወንዱን ሚኪ ሴቷን ፅናቴ እያለ
ይጠራ ነበር ። ያ ሰው ብሩክ ነው።
                  .
                  .
                  .

**ተፈፀመ**"


#ታሪኩ ይሄን ይመስላል...በትእግስት ስለተከታተላችሁን ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው.....ምን ያህሎቻችሁ ወዳችሁታል...? እስኪ በLike አሳዩኝ

ሀሳብ አ ስተያየት

አድርሱን!! እናመሰግናለን።።

መልካም -ምሽት

ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
አሰተያየት ካላችሁ