#ሰይጣን_የማይችላቸው_8ቱ_ትምህርቶች
#አንድ- ደጋግማችሁ የምታስቧቸው ሀሳቦች አካላዊ ተጓዳኞቻቸውን/አቻዎቻቸውን እንደሚስቡ አስታውሱ። ስለዚህ ስለምታስቡት ሃሳብ ተጠንቀቁ።
#ሁለት- ሁለት አካላት ሰውነታችንን እንደሚቆጣጠሩት ማወቅ አለብን። ከእነዚህ አካላት አንዱ ለፍርሃት የሚነሳሳና ምላሽ የሚሰጥ ሲሆን፣ ሌላው ለእምነት የሚነሳሳና ምላሽ የሚሰጥ ነው።
በእምነት ትመራለህ ወይንስ ፍርሃት እንዲቆጣጠርህ ትፈቅዳለህ?
#ሶስት- ተስፋ ሳይቆርጡ ውድቀትን አልፎ የመሄድ አቅም በየትኛውም የህይወት ጥሪ ውስጥ የላቀ ስኬት ላስመዘገበ ሰው ሁሉ ዋና ሀብት ነው።
#አራት- ውድቀት ሰው ሰራሽ ነው። ሰው እንደ ቋሚነት እስካልተቀበለው ድረስ ፈጽሞ እውን አይሆንም።
#አምስት- የአንተ ብቸኛ ገደብ በራስህ አእምሮ ውስጥ የፈጠርከው ነው።
#ስድስት- ተፈጥሮ ስራ ፈትነትን ወይም ባዶነትን አይታገስም። ሁሉም ቦታ በአንድ ነገር የተሞላ መሆን አለበት። ግለሰቡ አእምሮውን ለአዎንታዊ እና ለፈጠራ ሀሳቦች መገለጫነት ካልተጠቀመበት ተፈጥሮ አእምሮን በአሉታዊ ሐሳቦች ላይ እንዲሠራ በማስገደድ ክፍተቱን ይሞላል።
#ሰባት- አንድ ሰው እውቀትን እንዲጨምር ወይም ዋናውን የህይወት አላማውን ለማሳካት የሚያስችሉ ልማዶችን እንዲያዳብር ሲያስገድድ ውድቀት ሁሌም በረከት ነው።
#ስምንት እርግጠኛ በሆነ የህይወት አላማ የሚንቀሳቀስ ሰው በጊዜያዊ ሽንፈት እና ውድቀት መካከል ያለውን ልዩነት ይገነዘባል። ዕቅዶቹ ሲከሽፉ ሌሎችን እቅዶች ይተካል እንጂ ዓላማውን አይለውጥም። በፅናት ይቀጥላል!
#የስኬት_ፍልስፍና መጽሐፍ
የናፖሊዮን ሂል መጽሐፍ
የስኬት_ፍልስፍና 10ኛ ዕትም
teklu ጥላሁን