Get Mystery Box with random crypto!

ምኞት ክፍል 50 ደራሲ ጥላሁን ተስፋዬ . . . 'ምኛትዬ' ወዬ መስ ምነው ? 'ሚኪ እንደ | የፍቅር ጎጆ

ምኞት

ክፍል 50

ደራሲ ጥላሁን ተስፋዬ
.
.
.
"ምኛትዬ" ወዬ መስ ምነው ?
"ሚኪ እንደው ምናልባት ባንቺ ላይ ያደረገው ነገር ስተት እንደነበር
ተረድቶ ይቅርታ ቢጠይቅሽ ይቅርታውን ተቀብለሽ ታርቀሽው
አብረሽው ትኖሪያለሽ?•••
አይጠይቀኝም! ምክንያቱም ይቅርታ የሚጠይቀውን ስተትን ተሳስቶ
የፈፀመ ብቻ ነው። ሚኪ ደሞ ለሱ ትክክል የሆነውን ነገር አስቦና
ወስኖ ስላደረገ በምን ምክንያት ?ዛሬ ምን ተገኝቶ ይቅርታ
ይጠይቀኛል!
መልሷ ያልተዋጠለት መሳይ " ምኛትዬ ሰው በመጀመሪያ ለራሱ
ትክክል ነው ስተት መፈፀሙን የሚያምነው ስተት እንደነበር
መቀበል ሲፈልግ አልያም ስተት እንደነበር ሲረዳ ነው ። ትናንት
ትክክል መስሎን የሰራነው ወይም የወሰነው ውሳኔ ከቆይታ ቡሀላ
ትክክል እንድዳልነበርን ሲገለጥልን ከአንዳንዶቻችን በስተቀር ስተት
እንደሰራን ከተረዳንበት ቅፅበት አንስቶ የህሊና እረፍት እናጣለን
ስተቱን ወደ ዃላ ሄደን ማስተካከል ባይሆነልንም በኛ ስተት የተጎዳ
ሰው ካለ ያንን ሰው አግኝተን ይቅርታ እስከምንጠይቀው እንቅልፍ
የማይወስደን ብዙዎች ነን!" አላትና ምላሿን መጠባበቅ ጀመረ•••
ታድያ ዛሬ ላይ ትክክል እንዳልነበረ ገብቶት የሚጠይቀኝ ይቅርታ
ትክክክል እንዳልነበረ ማመኑን እንጂ ታርቆኝ ከኔ ጋር አብሮ
የመኖር ፍላጎት እንዳለው አያመለክትም እኮ።
አየህ መስዬ የጥፋተኝነት ስሜት እና አብሮ የመሆን ፍላጎት
የተለያዩ ነገሮች ናቸው።
ለዚህ ነው አንዳንድ ፍቅረኛሞች ሀምሳ ግዜ እየተጣሉ ሀምሳ ግዜ
ይቅርታ እየተባባሉ የሚታረቁት። ይቅርታ አብዛኛውን ግዜ ያለፈን
ስተት የማመን ጉዳይ እንጂ መጪውን ሒወት ለማቅናት በፍቅር
እና በደስታ ተሳስቦ ለመኖር የመወሰን ወይም የመለወጥ ጉዳይን
ያካተተ ነው ብሎ ማሰብ ከባድ ነው።ምክንያቱም አንዳንድ
ይቅርታዎች ስላለፈው ጉዳይ እንጂ ስለመጪው ሒወት የመወሰን
አቅማቸው ምንም ነው። ያንን የመወሰን ሙሉ አቅም ያለው
እውነተኛ ፍቅር ብቻ ነው ስለዚህ ሚኪ እኔ ላይ የፈፀመው በደል
አላስቀምጥ ሲለው ከኽሊና ወቀሳ ለመዳን ይቅርታ ጠየቀኝ ማለት
ከኔ ጋር ታርቆ ደስተኛ አርጎኝ ለመኖር የሚያስችል ፍቅር በውስጡ
መኖሩን አረጋገጠልኝ ማለት አይደለም። አለችው።
መሳይ ምኛት ለነገሮች ያላት ጠለቅ ያለ ምልከታ ከገመተው በላይ
ሆነ በትና ታድያ ምን ብሎ ቢጠይቃት ነው ይቅርታው በፍቅር አብሮ
የመኖር ዋስትናንም የሚያካትተው እያለ ሲያሰላስል•••
እሱ ዝም በማለቱ ምኛት ግዜ አገኘች። እሷም በተራዋ የመልስ
ምት የሚሆን ሚሳኤል የሆነ ጥያቄ ወደ መሳይ አስወነጨፈች•••
ናርዶስ ጥላህ ለመጥፋቷ በቂ ምክንያት ይዛ ዛሬ ብትመጣ ይቅር
ብለሀት አብረህ ለመኖር የማሰቢያ ግዜ ያስፈልግኻል?መስዬ?
አለችው•••
በመሳይ በኩል ትንፋሽ ጠፋ። እኼውልህ መስዬ መልሱን
ስለማውቀው አትንገረኝ እስካሁን እየሆነ ያለው ነገር እኔ ወይም
አንተ ቀድመን ያቀድነው ሳይሆን መኾን ያለበት ነው እየሆነ ያለው
ስለዚህ መሆን ያለበትን ነገር ለነገ እንተወው።
ኑሮ ወይም ሂወትን በቅድ ለመምራት ይቻል ይሆናል ፍቅርን ግን
በእቅድና ቀድሞ በተናገረው መንገድ የመራ ሰው የለም ፍቅር
ስሜት ነውና በእቅድ አይመራም ።
እኔ አንተን ከሚኪ ፍቅር መሸሸግያ ላደርግህ አልፈልግም! አንተም
የናርዶስን ፍቅር በኔ ውስጥ እንድትደበቀው አልፈልግም።
ግንኮ እኮ እኔ እየወደድኩሽ ነው ምኛቴ? አላት እጅግ በሚያሳዝን
ሁኔታ።
ግን መቸኮል የለብንማ መስዬ!! ውስጣችን ማለት የኔም ያንተም
ልብ ያልደመሰሰው ፍቅር አለ። ግኑኝነታችን የእውነት እንዲሆን
አሁን ባለንበት ከነገሮች ነፃ በሆነ እና መተሳሰብ በሞላበት
ፍቅራችን ትንሽ እንቆይ ግን መስዬ እንዳትናደድብኝ! ካንተ
የተደበቀ ምክንያት ኖሮኝ ሳይሆን ቸኩሎ መጣዱን ፈርቼው ነው
እባክህን ግዜ ስጠኝ ! አለችው።
ላንቺ ያለኝን ሁሉንም ስሜት አልነግርሽም አንቺ ዝግጁ
እስከምትሆኚ ብቻዬን አጣጥመዋለሁ ። እንዳልሽውም አንዱን
ስሜት ለመሸሽ ዘለን ገብተን ዘለን የምንወጣበት የወረት ፍቅር
እንዲሆን እኔም አልፈልግም። ነገር ግን የኔ ብትሆኝም ባትሆኝም
እንደነብሴ ከምወዳት ታናሽ እህቴ ከራሴ አስቀድሜ የማይሽ!
ተጎድቼ ባስደስህሽ ቅር የማይለኝ! በስስት እና በናፍቆት
የምጠብቅሽ ዳግም ለመኖሬ ምክንያት እንድትሆኚ መርጦ የላከሽ
የፈጣሪ ስጦታዬ እንደሆንሽ እወቂ!
ብሏት ቀና ሲል የሱ ብቻ ሳይሆኑ የሷም አይኖች በእምባ
መሞላታቸውን አስተዋለ ተያዩ እንባ ባጠለሉ አይኖቻችው ዝም
ብለው ተያዩ " ግን አሁንም የመጀመሪያው ጥያቄዬ
አልተመለሰልኝም አጠር አድርገሽ እንድትመልሽልኝ ጥያቄዬን
አስተካክዬ በድጋሚ እጠይቅሻለሁ••
ሚኪ ካንቺ ጋር በፍቅር ለመኖር ፍላጎት እንዳለው አረጋግጦ
ይቅርታ ቢጠይቅሽ ትቀበይዋለሽ?ምላሽሽ ምን ይሆናል?
መልሼልሀለሁ። አለችው።
አልመለሽልኝም ምኛቴ አላት።
አቦ ተወኛ አንተ ደረቅ የሆንክ ነገር አለችው። ተሳሳቁ እንባ ካዘሉ
አይኖች ስር የፈለቀ ንፁህ የፍቅር ሳቅ። ተነስቶ እንባዋን ጠረገና
ጉንጯን ሳማት ። ተያይዘው ጎን ለጎን ወደያዟቸው ክፍሎች
አመሩ። ሁለቱም ቁልፎቻቸውን እበሩ ቀዳዳ ውስጥ አስገብተው
በሩን ከመክፈታቸው በፊት ተያዩ ። ደና እደር መስ። አለችው። ደና
እደሪ ምኛቴ አላት ቁልፉን ዘወሩት። በሩን ከፍተው ከመግባታቸው
በፊት በድጋሚ "ደና እደሪ መልካም እንቅልፍ አላት። አሜን ብላው
ወደ ክፍሏ ገባች።
ትንሽ ቆመና እሱም ወደ ክፍሉ ገባ ።
አንቺ ትችይ ይሆናል እኔ ግን አልችልም ምኛት አለ አልጋው ላይ
ተደፍቶ። መሳይ በቀላሉ ፍቅር የሚያጠቃው አይነት ሰው ነው
ምኛት በዚች አጭር ግዜ ውስጥ ውስጡ ገብታ ልትነግስ
ተደላድላ ለመቀመጥ የሚሆናትን የልቡን ዙፋን ለመቆጣጠር ልቡ
ላይ ተሰንቅራ የቆየችውን ናርዶስን ጠራርጋ ለማስወጣት ናርዶስ
በመሳይ ልብ ለመንገሷ ፣ ለመፈቀራ ፣ በናርዶስ ለመሸነፉ
ምክንያት የሆኑትን ነገሮች በሙሉ በተሻለ ኹኔታ እየተካቻቸው
መኾኑን ሲረዳ ልቡ ፈራ።
" ቸኩሎ መጣዱን ፈርቼው ነው" ያለችው ነገር ደጋግሞ
ያቃጭልበታል እኔኮ ተጥጄ በፍቅርሽ መሞቅ ጀምሬአለሁ ምኛቴ !
አለ ጮክ ብሎ ምኛት አጠገቡ የለችምና አልሰማችውም።
ምኛትን አዲስ አበባ ይዟት መመለስ ፈራ ወዴት ወስጄ ልደብቅሽ
ወዴት ይዥሽ ልሽሽ ምኛቴ ?ይዘሀት ጥፋ ጥፋ አለው ከዛ በፊት
ግን ነገውኑ ምኛትን እዛው ሀዋሳ እንድትሆን በማድረግ የሆነ
ምክንያት ፈጥሮ ወደ አዲስ አበባ በመሄድ የሚኪን ሁኔታ
ማጣራት ።
ሚኪን አጋጣሚ እንዳገኘው መስሎ አግኝቶት ስሜቱን መረዳት
ፈለገ ። በዚህ ሁኔታ እዚህ መቆየት አልፈልግም ነገውኑ ወደ
አዲስ አበባ ተመልሼ ሚኪን አገኘዋለሁ አለ..........

#ሊጠናቀቅ ሁለት የመጨረሻ ክፍሎች ብቻ ይቀሩታል!! ቀጣዮቹን ክፍሎች የLike ተሳትፏችሁን አይቼ በፍጥነት እለቃለሁ እስኪ ታሪኩን ስንቶቻችሁ ወዳችሁታል? እየገጫችሁ።

.............ይቀጥላል............

ቀጣዩን#ክፍል እንዲቀጥልLike ማድረግ እንዳይረሳ ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
አሰተያየት ካላችሁ