Get Mystery Box with random crypto!

ምኞት ክፍል 51 ደራሲ ጥላሁን ተስፋዬ . . . ምኛትን አዲስ አበባ ይዟት መመለስ ፈራ ወ | የፍቅር ጎጆ

ምኞት

ክፍል 51

ደራሲ ጥላሁን ተስፋዬ
.
.
.
ምኛትን አዲስ አበባ ይዟት መመለስ ፈራ ወዴት ወስጄ ልደብቅሽ
ወዴት ይዥሽ ልሽሽ ምኛቴ ?ይዘሀትጥፋ ጥፋ አለው ከዛ በፊት
ግን ነገውኑ ምኛትን እዛው ሀዋሳ እንድትሆን በማድረግ የሆነ
ምክንያት ፈጥሮ ወደ አዲስ አበባ በመሄድ የሚኪን ሁኔታ
ማጣራት ።
ሚኪን አጋጣሚ እንዳገኘው መስሎ አግኝቶት ስሜቱን መረዳት
ፈለገ ። በዚህ ሁኔታ እዚህ መቆየት አልፈልግም ነገውኑ ወደ
አዲስ አበባ ተመልሼ ሚኪን አገኘዋለሁ አለ•••
•••ፅናት ሚኪ ጋር እንደደረሰች የሚኪ ሁኔታ ያልጠበቀችው ነበርና
በጣም ደነገጠች።
ፊቱ ላይ ያነበበችው ተስፋ የመቁረጥ ስሜት እና ልክ እንዳያት
ያሳያት ሁኔታ ለሱ ባትነግረውም በውስጣ አፍና የያዘችው ፍቅር
ላለባት ፅናት በዛ ደረጃ ሚኪን ማየት ከባድ ነበር።
በዛ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ምን ሆነህ ነው ብሎ ለመጠየቅ ድፍረት
አጥታ ዝም ብላ አጠገቡ ተቀምጣ አይን አይኑን ስትመለከተው
ከቆየች ቡሀላ "እባክህ ሚኪዬ መጠጡ ይበቃሀል ወደ ቤት
እንኺድ እያለች ጥያቄ ባዘሉ አይኖቿ ስትመለከተው
ባትጠይቀውም ከሷ ውጪ መከፋቱን ማዘኑን የሚተነፍስበት
የሌለው ሚኪ ግን ከተለያዩበት ቀን አንስቶ ምን እንደተፈጠረ አንድ
ባንድ በንባ እያራሰ አወራት። በንባ እየራሰች አደመጠችው።
ይዛው ከሆቴሉ ወጣች። ወደቤት አስገብታ ካስተኛችው ቡኻላ
አባቷ እንዳያዝኑባት ስለሰጋች እኔ እዛኛው ክፍል ልተኛ ብላው
በመውጣት ወደ ቤታ ኼደች ።በጥዋት ሚኪ ሳይነቃ ተነስታ ወደ
ሚኪ ቤት መጣችና አንዱ ክፍል ውስጥ ጋደም ብላ ማታ ከነገራት
ታሪክ ውስጥ ሚኪን ከሀገር ሀገር ያንከራተተችው በጭራሽ ምኛት
ልትሆን እንደማትችል ውስጧ ጠርጥሮ ስትብከነከን ያደረችበትን
ሀሳብ ለሚኪ ለመንገር እስኪነቃ ትጠብቀው ጀመር። ፅናት።
መሳይ እስከ እኩለ ለሊት በሀሳብ ሲገላበጥ ቆይቶ እኩለ ለሊት
ላይ እንቅልፍ ጣለው። ጥዋት 12:15 ላይ ከእንቅልፉ ነቃ።
አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀምጦ ወደ አዲስ አበባ ግድ የሚያስኬድ
ነገር ስለገጠመው ደርሶ እስኪመለስ ምኛት እዛው ሀዋሳ
እንድትጠብቀው ምን ብሎ ሊሳምናት እንደሚችል እያሰበ
የመጡለትን የተለያዩ የማሳመኛ ምክንያቶች ጭንቅላቱ ውስጥ
ሲፅፍ ሲቀድ ቆየ። የተሻለውን ሀሳብ አፅድቆ ሲያበቃ ተነስቶ
መለባበስ ጀመረ።
ክፍሏን በማንኴኴት ማንነቱን ተናገረ። ተነስታ ከፈተችለትና "
በሰላም ነው መስ? አለችው እንደቆመች።
"አይ•••እምምምም••አዋ ደላላው ነዋ •••ደላላው በለሊት ደውሎ
ቤቱን እግኝቻለሁ ነገር ግን በጥዋት መጥተህ ክራዩን ቅድሚያ
የሶስት ወር ካልከፈልክ ለሌላ ሰው አሳልፎ ያከራይብናል ፈጠን
ብሎኝ። ደርሼ ልምጣ ምኛቴ አንቺ እዚሁ እስከማታ እመለሳለሁ
።" ሲላት•••
ከድሬ እንደመጣች ሚኪ ቤቱ እስኪታደስ በሚል ሰበብ እዛ
ኮንደሚንየም ውስጥ አስቀምጧት መጣሁ ጠብቂኝ ብሎ የውሀ
ሽታ ሲሆን ውስጣ የተፈጠረው መጥፎ ስሜት መጣባት። ውስጣ
ተገለባበጠባት። "አይሆንም። በፍፁም መሄድ ካለብንም አብረን
እንሄዳለን እንጂ ለሰከንዶች እዚህ ብቻዬን አልሆንም ብቻዬን
ትተከኝ አትህዲ መስዬ እኔ ብቻዬን መሆን እፈራለሁ እባክህ
ጥለከኝ አትሂድ!" ብላ ተጠመጠመችበት መሳይ የሚይዝ
የሚጨብጠው ጠፋበት ምኛትን ድንገት የቀየራት ስሜት ምን
እንደሆነ ሲገባው "የትም አልሄድም ምኛቴ ምንም ሁኚ ምንም
የኔም ሁኚ የሌላ ወደ መቃብር ካልሆነ ሌላ ወደ የትም ጥዬሽ
አልሄድም የኔ መዳኒት የትም አልሄድም በቃ አብረን ሄደን
እንመለሳለን ። በጭራሽ ጥዬሽ አልሄድም የኔ ምኛት !" አለ
አጥብቆ እያቀፋት።
ወደ አዲስ አበባ ጉዞ እንደጀመሩ "አሁን ቤቱ ተገኝቷል ብያት
ስንደርስ ምን ልላት ነው?" ብሎ እየተጨነቀ ስልኩን አነሳና ወደ
ደላላው ደወለ።
ደላላው ስልኩን አንስቶ "ሀሎ ልደውልልህ ስል ደወልክ አዲሷ
ሙሽራህ እድለኛ ነች ባክህ ምርጥ ቤት ከነ ሙሉ እቃው
አግኝቼልሀለሁ!" ሲለው እሺ ከአንድ ከሁለት ሰአት ቡሀላ
እደውልልሀለሁ "ብሎ ለምክንያት የፈጠረው የቤት መገኘት ሰበብ
እውነት መሆኑ እያስደመመው አዲሷ ሙሽራ የኔ ትሁን የሌላ መች
ለየና እስቲ እንዳፍህ ያድርግልኝ አለ ለራሱ መሳይ በውስጡ።
ብሩኬን ሆስፒታል እንዳደረሱት የኪስ ዋሌቱን እና የጅ ስልኩን ይዞ
የተከተለው ሰው እዛው ለነበረ ዶክተር አስረክቦ ብሩክን
እንደማያውቀውና እሱ በመኪና አደጋ ሚስቱን ስላጣ አዝኖ
እንደተከተለው ተናግሮ ደና ስለሆነ ለቤተሰቦቹ በማታ ደውላችሁ
ባታስደነግጧቸው ጥሩ ነው ብሎ አስተያየቱን አክሎ ከሆስፒታሉ
ወጥቶ ሄደ።
ጥዋት ላይ አንዲት ነርስ ወደተንጋለለው ብሩክ ጠጋ ብላ እባክህን
የስልክህን መክፈቻ እዚህ ላይ ፃፍልኝ ወይ ክፈትልኝና ወደ
ቤተሰብ ልደውል አለችናው። እያቃሰተ ነገራት እና " ትንሹ"
የሚለው ላይ ደውይ ታናሽ ወንድሜ ነው እናቴ ልብ ድካም አለባት
እንዳትደነግጥ " አላት ። ከብሩክ ስልክ ላይ ትንሹ የሚል ስልክ
እየፈለገች ከክፍሉ ወጣች ለመደወል።
ትንሹ ስልክ ላይ ስትደውል ስልኩ አይጠራም ዝግ ነው። ግራ
ገባት። አደጋው ከመድረሱ በፊት ብሩክ ወደ ደወለባቸው ስልኮች
መደወል አሰበች። መጀመሪያ የደወለችው ወደ እነ ፅናት ሰራተኛ
ነበር ። ሰራተኛዋ ስልኳን እክፍሏ ውስጥ ትታው ቁርስ
እያቀራረበች ስለነበር አላነሳችውም። ወድያው ጨራርሳ ወደ
ክፍላ ስትመለስ ሚስ ኮል አየች ማታ ጥዋት ሚስኮል
እንዳደረኩልሽ እቅድ ሁለትን ቀጥይ ብሏት ነበር ብሩኬ።
ወድያው ወደ ሚኪ ደወለች ሚኪ ከንቅልፉ ባኖ አይኑን እያሻሸ
ስልኩን አነሳው።
ብሩኬ ባስጠናት መሰረት ፅናትና ወንድሟ በምኛት ላይ ምን
እንደፈፀሙ በአሳማኝ ሁኔታ ጋተችው።
ሚኪ ዞረበት። ቢዥ ሲልበት ታወቀው ። ፅናት እንደዛ ታደርጋለች
ብሎ መቀበል ቸገረው። ትንሽ ቆይቶ ከክፍሉ ወጥቶ ሰራተኛዋን "
ፅኑ የት ነች ?" አላት ። በአገጯ ያለችበትን ክፍል አሳየችው።
ዘው ብሎ ሲገባ ፅኑ እንቅልፍ ላይ ነች ተኝታለች ከነ ልብሷ።
ተጠግቶ በመቆም ቁልቁል እየተመለከታት የሰራተኛዋ ስልክ
አልነሳ ያላት ነርስ ዝቅ ስትል ፅናትን አገኘቻት። ፅናት ላይ
ደወለች። ፅናት ብንን ስትል ቁልቁል ያፈጠጠባትን ሚኪን አይታው
ደነገጠች።
"ምንድን ነው ሚኪ?!" አለች ተፈናጥራ በመነሳት።
"አይ ምንም ግን ልትነግሪኝ ፈልገሽ የደበቅሽኝ ሆን ብለሽ ሳይሆን
በስሜት ተገፋፍተሽ እኔን የሚያሳዝን ነገር ሰርተሽ ይሆን ?ፅናቴ! "
በጭራሽ ሚኪ ለምን እንዲህ አልከኝ ?"ስልኩን አንሺው ብሏት"
ወጣ ዳግም ሲጠራ።
ሚኪ ምን እንደሚል ምን እንደሚያረግ ግራ ግብት አለው።
ፅናት ግራ እንደተጋባች ስልኩን አነሳችው ነርሷ የብሩክን በመኪና
አደጋ ሆስፒታል መግባት ስትነግራት ደነገጠች ። ሮጣ በመውጣት
ለሚኪ ነግረችውና ተያይዘው ወደ ብሩክ እየሄዱ ቅድም ለምን
እንደዛ ብሎ እንደጠየቃት እንዲነግራት ስትወተውተው ፈራ ተባ
እያለ ነገራት "ለኔ ተወው ሚኪዬ እሄ የማን ሸር እንደሆነ ይገባኛል
ስላመንከኝ ግን ከልብ አመሰግናለሁ። አለች በንዴት ጣቶቿን ፀጉራ
መሀል ሽጣ እያበጠረችው።
ሆስፒታል ደርሰው ብሩክ ብዙም አለመጎዳቱን እንዳረጋገጡ
የደወለችላትን ነርስ በአይኗ ጠርታት ከክፍሉ ወጣች ወድያው
ቤተሰብ ጋር ለመደወል ስለፈለገች የብሩክን ስልክ ከፍታ
እንድትሰጣት ጠየቀቻት። ሰጠቻት። ወድያው የቤታቸውን ሰራተኛ
ስልክ ላይ የተላኩትን መልክቶች አገኘቻቸው። ደወለችላት። "
እቅድ ሁለትን ለሚኪ ደውዬ ነግሬዋለሁ ጌታው!" አለች ሰራተኛዋ።
ስልኩን ጠርቅማባት። እንደ እብድ እያደረጋት ወደ ክፍሉ
በመግባት " ፈጣሪ

ምላሽ ስለሰጠህ እኔ ምንም አልልህም!" ብላ
ስልኩን ብሩኬ ላይ ወርውራ ሚኪን እየጎተተች ከክፍሉ ይዛው