Get Mystery Box with random crypto!

የተሸነፍኩት በጠይም ቆንጆ ፊቷ አይደለም፤ የተማረኩት በጥቁር ዞማ ፀጉሯ አይደለም ፤ ያሸነፈችኝ | የፍቅር ጎጆ

የተሸነፍኩት በጠይም ቆንጆ ፊቷ አይደለም፤ የተማረኩት በጥቁር ዞማ ፀጉሯ አይደለም ፤ ያሸነፈችኝ በየዋህነቷ ነው ።

ለመድመቅ አለመፍጨርጨሯ ነው ፤ ተፈላጊነቷን ለማሳየት አትዳክርም ፤ ያላትን ለማጉላት አትታከክም ።

የምወዳት ፍቅሯን ለመግለፅ አውላላ መንገድ ላይ በነፃነት ስለምትጠመጠምብኝ ነው ፤ የገዛኝ ብቻዬን ስለምትወደኝ ነው።

ሲሳካልኝ እና ስወድቅ ከጎኔ እንደምትሆን ስለምታሰማኝ ነው።

የምወዳት ከወዳጆቻችን ጋ ስንሰባሰብ እኔ ሳወራ ከሁሉም በላይ ቀልቧን ስለምትሰጠኝ ነው ፤ የነገርኳትን ወሬ ደገምከው ሳትለኝ ስለምትሰማኝ ። የወደድኩትን ነገረ ስለምትወድልኝ ነው ።

የምወዳት ተስፋ ቆርጬ ፤ ተናድጄ ፤ አዝኜ ሳወራ በዝምታ እረጋ ብላ ስለምታፅናናኝ ነው።

የምወዳት ተቀይማኝ ተናዳብኝ አንገቷ ስር ስስማት በዝምታ ስትሳምልኝ ፤ ተናዳ በትንሽ ልፋት ስለምትረጋጋልኝ ነው ።

የምወዳት ልቧ አምኖኝ ፍለጋ ስላቆመች ነው። ከመታመን በላይ ሃላፊነት የት አለ ?

የምወዳት ስታናድደኝ እና ስናደድ በፍቅር ይቅርታ ስለምጠይቀኝ ነው ።

የምትፈልገውን እንዳደርግላት የምታደርገኝ ትህትና በተጠቀጠቀበት ልምምጥ ነው ። ስትለማመጥ በትሯ አይኗ ነው አይኗ ያሳዝናል፤ እሷ ላይ ስልጣን እንዳለኝ ይሰማኛል እንደምትታዘዘኝ ስታስዳስሰኝ ፍፁም ታዛዥ እሆናለሁ ።

@yefiker_gojo