Get Mystery Box with random crypto!

ምኞት ክፍል 47 ደራሲ ጥላሁን ተስፋዬ . . . ሲላት ያየችው እና የሰማችው ነገር በህልሟ | የፍቅር ጎጆ

ምኞት

ክፍል 47

ደራሲ ጥላሁን ተስፋዬ
.
.
.
ሲላት ያየችው እና የሰማችው ነገር በህልሟ እንጂ እሷ ለወራት
በኖረችበት በተረሳው በዛ ኮንደሚንየም እቃ ቤት
ውስጥ ከተኛችበት ፍራሽ አጠገብ የተቀመጠው እብዱ መሳይ
መሆኑን ማመን ተሳናት በማይክሮ ሰከንዶች ውስጥ ጭንቅላቷ
ውስጥ ብዙ ጥያዌዋች ተፈጠሩባት።
በፍርሀት ቀና ለማለት አቅም ብታጣም እንደምንም በጀርባዋ
ከተንጋለለችበት ፍራሽ ቀና ብላ ግድግዳውን ተጠግታ በመቀመጥ
በፍርሀት እና በዝምታ የመሰይን አይኖች ስትመለከት•••
"አይዞሽ አትደንግጪ አትፍሪኝም እኔ አንቺን የሚጎዳ እጅም ልብም
የለኝም። የዳንኩት ለዚህ የበቃሁትኮ ባንቺ ነው። አንቺ በህልሜ
የምትመጭዋ የኔዋ ናርዶስ እንዳልሆንሽ የገባኝ ያንቀን ከዚህ
አባቴ እና እህቴ በግዱ ይዘውኝ የኼዱ እለት ለሊት ነው።
ያን ቀን ለሊት ናርዶስ ጥላኝ ከመሄዳ ከቀናት በፊት ለብሳው
የነበረውን የምወድላትን ልብሷን ለብሳው መጣች።
ስትመጣ ደስ አለኝ ግን ወድያው ደስታዬ ወደ ሀዘንና ወደ ጭንቀት
ተቀየረ ምክንያቱም ያቺ ናርዶስ አንቺ ያስለመድሽኝን ነገር
ሳታደርልኝ ተመልሳ መሄድ ጀመረች ።
እንዳንቺ መድሀኒቴን አላዋጠችኝም፣ እንዳንቺ ፀጉሬን እየደባበሰች
አላስተኛችኝም። እንደልማዳ የማትያዝ የማትጨበጥ መንፈስ ሆና
ስታሰቃየኝ ቆይታ ልትሄድ ስትነሳ እባክሽ መድሀኒቴን ሳታውጪኝ
አትሂጅብኝ እባክሽ! እያልኩ ስጮህ ከእንቅልፌ ነቃሁ። ያኔ ሁሉም
ነገር ድብልቅልቅ አለብኝ እዚህ እያለሁ ናርዶስ የመሰለችኝ
ከዚችኛዋ ጋር አንድ ይሁኑ ይለያዩ ተምታታብኝ።
ወደ ቀልቤ ለመመለስ ሞከርኩና ሳሰላስል አንቺና የኔዋ ናርዶስ
ብትመሳሰሉም አንድ አይነት ወይም አንድ ሴት ሳትሆኑ ሁለት
የተለያያችሁ ሴቶች መሆናችሁ ገባኝ። እሄ ሲገባኝ ሌላ ግራ
የሚያጋባኝ ጥያቄ ውስጤ ተነሳ እዛ ኪንደሚንየም ማታ ማታ
የምትመጣውና ናርዶስን ስትመስለኝ የቆየችው ሴት ማነች?
እዛስ ምን ትሰራለች ?
ጭንቅላቴ ጋለ። ለዚህ ጥያቄዬ መልስ ሳላገኝ ለደቂቃዎች ስቆይ
ተለወጥኩ ማንም መውጣቴን ሳያውቅ በዛ ፅልመት ባልገፈፈለት
ውድቅት ለሊት ከግቢ ወጥቼ እግሬ ወደመራኝ መጓዝ ጀመርኩ።
ከአዲስ አበባ ወጣሁ በደብረብርሀን መስመር ዋናውን አስፖልት
ይዤ መጓዜን የማውቀው ነገር አልነበረም ነበር ።
ለስምንት ሰአታት ያክል ከተጓዝኩ ቡሀላ ወደ እመቤታችን ወደ
"ሰሚነሽ ኪዳነ ምህረት" ፀበል በቤት ምኪናቸው ሲጓዙ የነበሩ
የቤተሰብ አባላት ከውኻላ ሲመለከቱኝ አረማመዴ መድከሜን
አሳወቃቸው መሰል •••
አጠገቤ እንደደረሱ መኪናውን በማቆም ወዴት እንደምሄድ
ጠይቀውኝ መልሴን ሳይጠብቁ እነሱ ወደ ሰሚነሽ ማርያም ፀበል
እየኼዱ እንዱኾነና ወደዛው ከኾንኩ አብሪያቸው መኼድ
እንደምችል ሲነግሩኝ ጥሪው የሷ ነበርና አዎ ወደዛው ነው
የምሄደው ከማለት ውጪ ሌላ ነገር ከአንደበቴ ማውጣት
አልቻልኩም።
እሄን እንዳልኩ የመኪናውን በር ከፈቱልኝ አብሪያቸው ሄድኩ
ሲጠመቁ ተጠመኩ የመኪናው ብቻ ሳይሆን የተዘጋው የጭንቅላቴ
በርም ተከፈተ።
አባቴ እዚህ ቤት አምጥቶ የጣለኝ ልበጎ መሆኑን ያወኩት እዛ
ለሶስት ቀን ብቻ ቆይቼ የድሮውን መሳይ ሳገኘው ነው።
ሁሉም ነገር ተቀይሮ የድሮውን መሳይ ብሆንም ኖርዶሴን ማፍቀሬ
እና መናፈቄ ግን ዛሬም ህያው ነው።
ጨርቁን ጥሎ የለየለት እብድ ስላልነበርኩ ያለፈው ነገር
በከፊልም ቢሆን ትዝ ይለኛል። አንቺ ትዝ አልሽኝ በናርዶስ ቅዥት
ከእንቅልፌ ስነቃ ስላንቺ ለተፈጠረብኝ ጥያቄ መልስ ለማግኘት
ከሰዎቹ ጋር አብሬ ወደአዲሳባ እንደተመለስኩ ወደቤት ሳልኼድ
ቀጥታ ወደዚህ መጣሁ አዝነሽ እንድታስገቢኝ እብዱን መሳይ
መምሰል እንዳለብኝ አሰብኩ። ስመጣ በሩ ዝግ የሆነው እቤት
ስላልሆንሽ መስሎኝ እስክትመጪ በረንዳ ላይ ቁጭ ብዬ ስጠባበቅ
በመሀል ሽንት ቤት ገብተሽ ስትወጪ ስለሰማሁ ውስጥ እንደሆንሽ
ተረዳሁ። አንቺን የማወቅ ጉጉቴ ጨመረ። መስኮትሽ ስር ሆኜ እንደ
እብድ መለፍለፍ ጀመርኩ።
የጠበኩት ሆነ። በሩን ከፈትሽልኝ። ገባሁ ።እብዱን መሳይ
እንደመሰልኩ ማንነትሽን ለማጣራት ብሞክርም አልቻልኩም
ምክንያቱም•••
- ከማንም ጋር አታወሪም፣ከማንም ጋር አትደዋወይም፣ቀኑን ሙሉ
በተዘጋ ቤት ሊያውም በቤቱ አንድ ቆሻሻ ክፍል ውስጥ ነው
እምትውይው፣ እኔን ካስተኛሽኝ ቡሀላ ስታለቅሺ ሰምቼሻለሁ።
እንቅልፍ አጣሁ። በለሊት ተነስቼ እዚህ ክፍል በመግባት
እስክትነቂ መጠባበቅ ጀመርኩ። እባክሽ ድጋሚ ከማበዴ በፊት
ማን እንደሆንሽና ለምን በዚህ እድሜሽ እሄን የመሰለ ውበት ይዘሽ
እዚህ ቤት ውስጥ ሊያውም በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ
እንድደምትኖሪ ንገሪኝ እባክሽ?"
ከምኛት አይኖች የሚረግፈው እንባ ማቆሚያ አልነበረውም ታሪኳን
በአጭሩና በሚያሳዝን ሁኔታ ነገረችው።
"አይዞሽ ሁሉም አልፋል አሸንፈነዋል ከእንግዲህ ምንም ችግር
አታይም ከጎንሽ ነኝ!" እያለ እንባዋን ከጉንጮቿ እየጠረገ የሱ
ጉንጮች በእንባ ራሱ።
ከዚህ ቤት ዛሬውኑ ይዤሽ እወጣለሁ ቤት እከራይልሻለሁ እቤት
ደርሼ እስክመጣ ጠብቂኝ ብሏት ከወጣ ቡሀላ ሲመለስ
የሚያጣት የምትጠፋበት መሰለውና ፈራ ።
ተመለሰ።" ፈራሁ አንቺም እንደናርዶሴ ጥለሽኝ የምትጠፊ መሰለኝ
እባክሽ አብረን እንሂድ ሲላት ስሜቱ ከባድ ነበርና ሁለቱንም በእንባ
አራጫቸው ተያይዘው አነቡ ።ተቃቅፈው አለቀሱ።
እንደምትጠብቀው በናቷ ስም ቃል ገብታለት ወደቤት ኼዶ
ተመልሶ ሲመጣ ስላገኛት ደስታው ወደር አልነበረውም።
መኪና ይዞ ነበርና የመጣው "ከእንግዲህ ወደዚህ ሲኦል ወደ ሆነ
ቤት አትመለሽም በጣም የሚያስፈልጉሽን ያዢ ። አላት።
ዳግም ላይመለሱ ከዛ ኮንደሚንየም ተያይዘው ወጡ ። " ጥሩ
ቤት እንዲፈልግልኝ ላንድ በቅርብ ለማውቀው ደላላ ነግሬዋለሁ
እስከዛው ላንድ ሶስት ቀን ከከተማ ወጣ ብለን እንቆያለን አላት።
መስማማቷን ፈገግታ ባደመቀው ፍቷ ገለጠችለት። ከመኼዳቸው
በፊት ወደ አንድ ዘመናዊ የሴቶች ልብስ መሸጫ ጎራ ብለው
በምርጫዋ ሻንጣ ሙሉ ልብስ ገዛላት ።
ምኛት ደመቀች ።ልክ እንደፅጌሬዳ ዳግም አበበች ። ያ የድሬው
ውብ ማንነቷ የተመለሰ መሰላት ።
መሳይ እየነዳ ምኛት አጠገቡ ጋቢና ውስጥ ተቀምጣ ፈንዲሻ
እየበላች ወደ ሀዋሳ ነጎዱ...

.............ይቀጥላል............

150 ከገባ#ክፍል 48 ዛሬ ይለቀቃል

ቀጣዩን#ክፍል እንዲቀጥልLike ማድረግ እንዳይረሳ ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
አሰተያየት ካላችሁ